ህይወት እደዋዛ – ቤተልሄም ጌታቸው

ሰው ለሰው መድሀኒቱ ነው የሚባለው አባባል ትዝ አለኝ:: በቀደም ማምሻውን ፌስቡክ ስከፍት “የሀገራችን ሰው እራሱን አጥፍቶ ተገኘ፣ ቤተሰብ ስለሌለው ለሬሳ መላኪያ እርዱ” የሚል አይቼ በጣም አዘንኩ::ልብ ይሰብራል!

ሀገር አቋርጦ  ተሰዶ ህይወቱን ሊለውጥ የቤተሰቡን ህይወት ሊለውጥ የመጣ ሰው ሞቶ ሲገኝ: ምክኒያቱ ምን ይሆን? ኑሮ ከብዶት ይሆን? ብቸኝነት አጥቅቶት ይሆን? ጓደኛ ከድቶት ይሆን? ሀገር እና ቤተሰብ ናፍቆት ይሆን? የአይምሮ ችግር ይኖረው ይሆን? የሚሉ ጥያቄዋች ተንሸራሸሩብኝ::
ስንቱ ሰው ባህር አቋርጦ ተሰቃይቶ ገዘቡን ከስክሶ እና ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ቤተሰቡን ጥሎ የሚመጣባትን አሜሪካ ለምን በቃኝ ብሎ ተሰናበተ:: ይሄን ልፅፍም ያነሳሳኝ ምክኒያት ከላይ የዘረዘርኮቸው ጥያቄዋች ይሄንን ወጣት በህይወቱ እያለ የሚጠይቀው ፣ የሚረዳው ፣ አለሁ አይዞህ የሚለው ፣ የሚያሳክመው ሰው ቢኖር ኖሮ በህይወት በቆየልን ነበር::

ይሄንንም አጋጣሚ ተጠቅሜ ስለ አይምሮ ህመም ትንሽ መፃፍ ፈለኩ :-እዚህ ጋር ልታሰምሩልኝ የምፈልገው በምን ምክኒያት እራሱን እዳጠፋ የሚያቅ የለም እኔም የአምሮ ችግር ነው ለዚህ ያበቃው በጭራሽ እያልኩኝ አይደለም።ነገር ግን የአምሮ በሽታ እራስን ሊያስጠፋ የሚችል በሽታ ስለሆነ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ስለተማርኩት እና ስለማቀው ነገር ላካፍል ብዬ ነው:: በህክምና ሙያ ውስጥ ያለን ሰዋች እንዱ ሀላፊነታችን ማስተማር awareness/ ንቃትን መፍጠር ነው ስለዚህም ያለንን እውቀን ማካፈል ግዴታችን ነው::

ሀገራችን ላይ በmental health/ የአይምሮ በሽታ ላይ ብዙ ጥናት እና መሰራት ያለባቸው ነገሮች አሉ ፣ እንደተረዳሁት ከሆነ Dr Elias Gebru Aimero ኢትዮጵያ ላይ የስልክ እና ኦንላይን ህክምና መስመር ፕሮጀክት ጀምረዋል እና ይሄ በጣም የሚያስደስት ዜና ነው:: እዚህ በውጭ አለም ለምትኖሩ ያለምንም ወጭ 24/7 እርዳታ ይሰጣሉ 988 በመደወል እርዳታ ማግኘትም ይችላሉ::በሜንታል ሄልዝ በሽታ የተነሳ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በውጭውም አለም ብዙ ሂወት እናጣለን  ለምሳሌ በአሜሪካ ውስጥ በየ11 ደቂቃ ውስጥ 1 ሰው በsuicide/እራስን በማጥፋት ይሞታል። ይሄንን ችግር ማቆምና መርዳት የምንችለው ቤተሰብ ፣ ጎደኛ እና የህክምና ባለሙያዋች ነን ትክክለኛውን ህክምና በጊዜ እዲያገኙ በማድረግ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊነት ለሁላችንም የሚሆን መመሪያ!

በእኛ ሀገር የግንዛቤ እና የእውቀትም ጉድለት የባህልም ነገር ተጨምሮ የአይምሮ በሽታ ልክ እንደሚስጥር ወይም እንደ አሳፋሪ ነገር እና እንደ ድክመት ተደርጎ ይቆጠራል።  በተለይ ወንዶች በዝምታ በዚህ ችግር ተጠቂዋች ናቸው:: ባህላችን ወንድ ልጅ ምን ትልፈሰፈሳለህ ጠንከር በል እየተባለ አድጎ ችግሮች ባጋጠሙት ሰአት ብቻውን ይጋፈጣል፣ ችግሩንም ከተናገረ ትዝብት ላይ የሚወድቅ እና እንደደካማ የሚታይ ስለሚመስለው ብቻውን ይታገላል::
የአይምሮ በሽታን ግንዛቤ በማጣት በመድሀኒት እና በቴራፒ መረዳት እና መዳን የሚችሉ ሰዋችን እያጣን ነው:: በተለይ በሀገራችን ላይ ያለው የከፋ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የኑሮ ችግር እንዲባባስ እያረገው ሲሆን ይህንኑ ማሳያ ወጣቱ ውድ ህይወቱን እንደቀልድ እያጠፋ መሆኑ ነው:: የኑሮ ውድነት ስራ አጥነት በተለይ በዚህ አመት ብዙ ልጆች ከትምህርታቸው መውደቅ ወጣቱን depression/ ድባቴ ውስጥ ከቶታል። ወጣቱም ግልፅ ሆኖ ህክምና እና እርዳታ ከመጠየቅ እራስን በመጠጥ፣በድራግ እና በተለያዩ ሱስ ውስጥ ተጠምዶ ችግሩንና ህመሙን ለመርሳት ይዳክራል::

የአይምሮ ችግር ምልክቶችን መገንዘብ ማዋቅ ለራሳችንም ለበቤተሰባችን ለጎደኛችን ለመርዳት ይጠቅማል:: ብዙ አይነት የአይምሮ በሽታዋች አሉ የበሽታዋቹም ምልክቶች እንደበሽታው አይነት ከሰው ሰው ይለያል:: በሽታው የሚያጠቃው የሚቀይረው አስተሳሰባችንን ፣ ስሜት እና ፀባያችንን ነው:: ሲጀመር የአይምሮ በሽታ ከምን ይመጣል? ይሄን ከተገነዘብን በኃላ ስለ አይምሮ በሽታ ያለን ግንዛቤ ይቀየራል። የአይምሮ በሽታ በዘር ይተላለፋል ቤተሰቦቻችሁ ውስጥ የአይምሮ በሽታ ያለው ሰው ካለ የመተላለፍ እድሉ አለ ፣ የዚህ ጅን ተሸካሚ ከሆነ ያሰው የሆነ እድሜ ላይ የበሽታው ምልክቶች መታየት ይጀምራል ብዙ ጊዜ በወጣት እድሜ ላይ የአይምሮ በሽታ ቢከሰትም፣ የትኛውም እድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል::
አንዳንድ ሰው የአይምሮ ችግር የሚከሰትባቸው:- በልጅነት እድሜያቸው ተጨቁነው ተሰቃይተው ከነበረ አሰቃቂ ነገር አይተው ከነበረ ያ ወደ አይምሮ ችግር ሊቀየርባቸው ይችላል። ለምሳሌ ጦርነት ውስጥ የተወለዱ እና የሚያድጉ ልጆች ቀጥተኛ ተጠቂ ሲሆኑ በሀገራችን በአማራ ፣ በትግራይ፣ በኦሮምያ፣ በአፋር ክልል በጦርነት ሳቢያ ልጆች ብዙ ስቃይ መከራ እና አሰቃቂ ነገር ያያሉ ያደሞ አይምሮቸውን ጉድቶት ያድጋሉ ያለህክምና እና ያለ እርዳታ እነዚህ ልጆች የአይምሮ በሽተኛ የመሆን እድላቸው ከፍ ያለ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለኔልሰን ራህላሂላ ማንዴላ!

ሌላው ደሞ የአይምሮ በሽታ ሊከሰት የሚችለው ጭቅላታችን ውስጥ ያሉ መልእክት ከአይምሮችን ወደ አካላታችን የሚያስተላልፍ ኬሚካሎች በደንብ ሳይሰሩ ሲቀር የሚከሰት ሲሆን ይሄ ችግር ሲፈጠር ግለሰቡ ዲፕረሽን/ድባቴ/ ድብርት ውስጥ እንዲገባ ያረጉታል።ይህም በአስተሳሰባቸው በፀባያቸው ላይ ለውጥ ይፈጥራል:: ይሄም ችግር ሊስተካከል የሚችለው በመድሀኒት እና በቴራፒ ነው::

በአይምሮ ችግር ሁሉም ሰው ምልክት ላያሳይ ይችላል ከሰው ሰው ምልክቶቹም ይለያያሉ ግን እነዚህ ምልክቶች መደጋገም:- በፊት ያልነበረባቸው ፀባይ ወይም አመል መቀየር ፣ አዲስ ፀባይ አዲስ አመል ማሳየት፣  ለምሳሌ በፊት ተጫዋች የነበረ ሰው ዝምታን ማብዛት፣ እራስን ከሰው ማራቅ ማግለል፣ ከራስ ጋር ማውራት፣ ጭንቀት ማብዛት ፣ ብዙ መተኛት ወይም አለ መተኛት፣ በትንሽ በትልቁ መበሳጨት ፣ የተስፋ የመቁረጥ ቃላቶች ማዘውተር ፣ መጠጥ ማብዛት ፣ መስከር በአብዛኛው እነዚህ ምልክቶች በተደጋጋሚ የሚያሳዩ ሰዋች ዲፕረሽን ውስጥ ሲሆኑ ነው::
ብዙ አይነት የአይምሮ በሽታዋች ሲኖሩ በጥቂቱ ለመጥቀስ bipolar disorder የፀባይ የመቀያየር፣ anxiety disorder ከመጠን በላይ መጨነቅ ፍራቻን የመሳሰሉ ባህሪዋችን ያካትታል፣ substance abuse disorder በተለያየ ሱሶች መጠመድ በእፅ በመጠጥ፣  post trauma disorder ጦርነት አቢውዝ ከባድ አደጋ የመሳሰሉ ነገሮች ጭንቀት ይፈጥራሉ ፣ schizophrenia እውነት ያልሆነ የራስ አለም ታሪክ መፍጠር ከራሳቸው ጋር ጮክ ብሎ ማውራት  የመሳሰሉ የአይምሮ በሽታዋች ተጠቃሽ ናቸው።

በምን አይነት መገድ መርዳት እንደምንችል ግንዛቤ ማግኝት የመጀመሪያው ሂደት ሲሆን ሲቀጥል ልባችን እና ጆሮችን ክፍት አርገን ሳንፈርድ እድምጠን ለመርዳት መጣር ነው። ነገሮችን አጢነን ከአቅማችን በላይ ከሆነ የሥነ-ልቦናና ሥነ-አእምሮ ብቁ ባለሙያዎችን እንዲያዩ ማድረግ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዞትር ትክክል የመሆን ምኞት እና ያስከተለዉ መዘዝ

ባጠቃላይ ብቻችሁን አትሰቃዩ እርዳታ ጠይቁ ቤተሰብ ጉደኛ አማክሩ በተለይ በውጭ የምትኖሩ ብዙ ሊረዷችሁ የሚችሉ ህክምናዋች ስላሉ ለቤተሰብ ለጉደኛ ማማከር ባትፈልጉ ለሀኪማችሁ ነግራችሁ እነሱ ወደ ትክክለኛው እርዳታ የምታገኙበት መንገድ ሊመሯችሁ ይችላሉ።

በተጨማሪ አፅንኦት ሰጥቼ ላሳስብ የምወደው:- እርስ በራስ በዙሪያችን ካሉ ሁሉ እንረዳዳ፣ እንጠያየቅ፣ እንደጋገፍ እላለሁ። ይህች  አለም ብዙ ፈተና አላት፣ ብዙ ውጣ ውረድ አላት፣ ልንወጣው የምንችለው አንድላይ በመስራት በመደጋገፍ በመረዳዳት በመተዛዘን ነው እና  መግቢያዬ ላይ እንዳልኩት ሰው ነው ለሰው መዳኒቱ::
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይባርክ!!!

2 Comments

  1. Yes, it is deeply sad !!! But the question is why all this extremely tragic situation happened and is happening or why we have miserably failed to stop it ? Why we allowed and keep allowing such a tragedy for so long ? Why we just complain , cry, and blame those whose brutalities are already known more than enough ? Why we allow them to dehumanize us so terribly and for so long and long ? Why we horribly failed to come together and fight against the evil-minded rulers with a very determined slogan of give freedom or death (to be ir bit to be)!!!????

  2. ዶር ቤተልሄም ችግሩን ተመልክተሽ መፍትሄ ሊሆን ይችላል ብለሽ ከስልጠናሽ አንጻር ለሁገር ቤትና ከሀገር ውጭ ላሉት ሁሉ የጻፍሽልን በጣም ጠቃሚ ነው እውቀት ያብዛልን። ወገን ለወገን የሚለውን አሟልተሻል ሌሎችም ያንችን መንገድ ቢከተሉ ተጠቃሚ እንሆን ነበር። TG ለጻፈው ግን ብዙ ቢጻፍበትም ውጤት ግን አልመጣም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከወገኑና ከሀገሩ ይልቅ ለጠላት እየወገኑ እነሱም እንደ በረሮ ያልቃሉ ኢትዮጵያንም ጤና ይነሳሉ። የችግሩ ምንጭ ግን የአድዋ ድልና አባይ ይመስሉኛል በመሀይም ልቦናዬ ። ባጠቃላይ ልባቸው ለጠላት ክፍት ሁኖ በሀገር ጥላቻ ተለክፈው አሁን ደግሞ ሌላ ሀገር ጠይ ፈጥረው ሌላ ተጨማሪ ክፋት እየፈበረኩ ይገኛሉ። በክፉ ስራም ወደር የላቸውም አንዳንዴ የሲኦል በር እዛ አካባቢ ነው የሚሉ ይገኛሉ ። የአእምሮ በሽታ እህታችን በጻፈችው መልኩ መፍትሄ ቢያገኝም የነዚህ ግን ተንኮላቸውን አይቶ ከላይ የሚሆነውን መጠበቅ እንጅ ምን ማድረግ ይቻላል? ችግሩም ይቀጥላል። የላይኞቹ ትግሬዎች በዲሞክራሲ እጦት ( እነሱ እንዳሉት) ተገነጠሉ
    ይኸው ዲሞክራሲያዊ መሪ አግኝተው እያሻቸው ነው በልጽገውም አመታዊ ገቢያቸው ከስካንዲኔቪይን አገሮች በልጧል ችግርና ረሀብም ታሪክ ሁኗል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ የ70 አመት ሰው ብቻ ነው በዚያ የሚኖረው። የታችኞቹ ትግሬዎችን ጉዳይ መቼም ቃል አይገልጸውም ስለ ክፋታቸው ኮምፒተርም ቢሆን ቀለሙ ስለሚያልቅ ቢቀር ይሻላል። አቦይ ስብሀትን የመሰሉ ሙተው በሌላ ቆዳ የተመለሱ ሌባና ነብስ ገዳይ እንደዛ ተበለሻሽተው ጋያ መጠጫቸውን ሳይቀር ጉድጓድ ገብቶ ያወጣቸውን ሰራዊት በዚህ መልኩ መሳደብ ይገባ ነበር? እንደው ሙሶሎኒ ምን አቅምሶብን ነው የሄደው እዛ አካባቢ? መጥኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share