ኢዛና ወርቅ ማዕድን በኮነሬል አብይ ኮንትሮባንዲስቶች ወደ አረብ ኢምሬትስ እየተጋዘ ነው! የማሞ ኢኮኖሚ!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

ከትግራይ ኢዛና የወርቅ ማዕድን ወደ አዲስ አበባ እየተጫነ ኩብለላ ተዘረፈ ‹‹መስመር አዩ ኃይልና!››

የወርቅ ምርት የኤክስፖርት ገቢ፡- በኢትዮጵያ የወርቀ ኃብት ለውጪ ንግድ ገቢ ከቡና ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ገቢ በማስገኘት ይታወቃል፡፡በ2018/19 እኤአ ሃያ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ዝቅተኛ ገቢ አስመዝግቦ ነበር፡፡ በ2021 እኤአ 672 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶ ነበር፡፡ በ2022እኤአ 546  ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶ ነበር፡፡ በ2023እኤአ ስድስት ወራቶች ውስጥ የወርቅ ኤክስፖርት ገቢ በጣም በመቀነስ 117.4 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶል፡፡ ከተመሳሳይ አመቶች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ገቢ መሆኑ ታውቆል፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ልማት ገቢ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሮያሊቲ ግብር ጥያቄ በኃላ የወርቁን ኃብት ለእኩል ድርሻ የመካፈል ጥያቄ የተነሳ የወርቅ ምርት እንደቀነሰ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ የወርቅ ኃብት የፌዴራል መንግሥቱ ኃብት ሳይሆኑ መጀመሪያ የህወሓት ወያኔ የኢዛና የወርቅ ማዕድን እና ቀጥሎም የኦነግ ኦህዴድ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በመቆጣጠር የግል ሃብታቸው በማድረግ የወርቅ ኃብቱን ተቀራምተውታል፡፡ በዚህም የተነሳ የሃገሪቱ የወርቅ ኃብት ከኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ወደ ኬንያ ፣ሱዳን፣ ጂቡቲ ወዘተ በህገወጥ ንግድ ድንበር ጥሶ እንደሚሸጥ ታውቆል፡፡ የመከላከያ ሠራዊቱ ከአማራ ክልል ወጥቶ ድንበር በመጠበቅ የወርቅ ማዕድናችንን ከህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶች ይጠብቅ፡፡ ኮንትሮባንድ ማስቆም ያልቻለ መንግስት እራሱ ኮንትሮባንዲስት በመሆኑ ነው፡፡

በዚህም ጥገወጥ ንግድ ሽያጭ የቻይና ዜጎች ዋና ተሳታፊዎች እንደሆኑ ታውቆል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ ብሄራዊ ባንክ የሚገባውና የሚቀመጠው የወርቅ ኃብት መቀነሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በተደጋጋሚ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ በኢኖሚው መውደቅ የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ የተነሳ ሃገር በቀል ኢንቨስተሮች ረብጣ ቢሊዮን ብር ከመያዝ ይልቅ፣ ዶላርና ወርቅ መያዝ፣ እንዲሁም ንብረት ቤትና መኪና በመግዛት ህንፃ ግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ሁሉ አዲስ ዘመናይ ባንኮች የሚገነቡት በብር የመግዛት አቅምና መውደቅና ወደፊት የዶላር ምንዛሪ የብር ዋጋ እንደቅጠል ስለሚረክስና ኪሳራቸውን ለመቀነስ ገንዘባቸውን ሠማይ ጠቀስ ፎቅ ግንባታ ላይ ያዋሉት፡፡ በሌሎች አገሮች የአዲስ ባንክ ግንባታ የለም፡፡ (Brick-and-mortar banks) ግንባታ ጊዜ አልፎበታል፡፡ ዘመኑ ቢሮ አልባ የባንኮችና የደንበኞች ኦን ላይን ግንኙነቶች (online banks) ቴክኖሎጂ ዘመን ነው፣ ሰማይ ጠቀስ የባንክ ፎቆች መገንባት ኪሳራ ነው፡፡ በሰለጠነው ዓለም የባንክ አገልግሎት ወደ ባንክ ቤት ሄዶ አገልገሎት የሚጠይቅ ደንበኛ የለም፡፡ የዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነት በኦን ላይን ባንኪንግ ግንኙነቶች (online banks) መረብ ከአጥናፍ አጥናፍ ተዘርግቷል፡፡

ኢዛና መዕድን ኃብት /// (Ezana Mineral Development Private Limited Company) በ1993እኤአ ኢዛና ማዕድን ልማት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር  በ1.4 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ተመሠረተ፡፡ ካንፓኒው በ 17.8 ሚሊዮን ዩኤስ ዶላር የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ በቱርክ ማንሃተን ኮርፖሬሽን ተገነባ፡፡ ኢዛና የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ ሲገነባ ለአራት ዓለም ዓቀፍ ኮንትራክተሮች ጨረታ ወጥቶ የተሠጠ ነበር፡፡ በህወሃት/ ኢፈርት ባለቤትነት የተቆቆመ ካንፓኒ ሲሆን በትግራይ ክልል ውስጥ የተገኘውን 13 ቶን ወይም ፣13,000 (አስራሦስት ሽህ) ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት በካናዳዊያን የወርቅ ማዕድን ካንፖኒ ኢዛና ወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተገነባ፡፡ ህወሃት/ኢፈርት የኢዛና ወርቅ ኃብትን በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘርፈው የወርቅ ሃብት ነው፡፡ ኢዛና ካንፓኒ 393.7 ሚሊዩን ብር የፕሮጀክት ወጪ 2017 (ሁለት ሽህ አስራ ሰባት) ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶ ይሰራ ነበር፡፡ በ1995እኤአ እቅድ መሠረት 2017 (ሁለት ሽህ አስራ ሰባት)ኪሎ ግራም ወርቅ 2,017,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 69,552 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1218.80 ዶላር ስናባዛ 84,769,977.6 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ በ20.34 ሲባዛ 1,724,221,344.384 ቢሊዩን ብር የህወሃት ጦር አበጋዞች በውጪ ሃገር ባንኮች ያከማቹ ነበር፡፡ (በጊዜው አንድ ዶላር በሃያ ብር ከሠላሳ አራት ሳንቲም ይመነዘር ነበር፡፡)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ - በአብርሃ ደስታ

 

የኢዛና የወርቅ ልማት በትግራይ ኢፈርት ልማት ድርጅት (EFFORT) በሽሬ ከተማ የተመሠረተው የኢዛና የወርቅ ልማት  ካንፓኒ  በጦርነቱ በሻብያ ፋብሪካው ወላልቆ ተወሰደ፡፡ ኢዛና ከጦርነቱ በፊት እስከ ዘጠኝ ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ያደርግ ነበር፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ የወርቅ ማዕድኖች ምንም የወርቅ ኃብት የውጭ ምንዛሪ ገቢ (foreign currency) አያገኝም ፡፡ የወርቅ ኮንትሮባንዲስቶች ለአንድ ግራም ወርቅ አንድ ሽህ ብር ጭማሪ  ስለሚከፍሉ፣ ከብሔራዊ ባንክ በላይ ስለሚከፍል ለባንክ ወርቅ የሚያስረክብ የለም፡፡

በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት 1200 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ) የማዕድን ማውጣት ፍቃድ ያላቸው የነበሩ ሲሆኑ ፣ በፊዴራል መንግሥት ፍቃድ የተሰጣቸው ሠላሳ የሚሆኑት ከፍተኛ ማዕድን ፍቃድ የተሰጣቸው ካንፓኒዎች ነበሩ፡፡ በትግራይ መቶ ሽህ ባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሃያ ኩንታል ወርቅ በየአመቱ በማምረት ለህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶች ንግድ ገቢ ያደርጋሉ፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ ወርቅ በማምረት ይታወቃል፣ ሃያ ስድስት ኩንታል ወርቅ በአመት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስረክብ ነበር ከ2020እኤአ ጦርነት በፊት፡፡ በወርቅ የወጭ ንግድ ገቢ መቶ ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኝ ነበር፣ ከጠቅላላው የሃገሪቱ የወርቅ ኤክስፖርት ገቢ አንድ አምስተኛው እጂ በ2020/21እኤአ ይሸፍን የነበር የወርቅ ገቢው በመቀነስ ዚሮ ደረጃ ወረደ፡፡

The central bank’s supply of gold from mines in Tigray has dried up completely, but artisanal mining continues in the region, extracting an estimated 20 quintals of gold each year for supply to a clandestine market. Tigray Regional State was one of the largest gold-producing regions in Ethiopia next to Oromia, supplying close to 26 quintals to the central bank in the year preceding the outbreak of war in November 2020. It was equivalent to 100 million dollars in export revenues, or close to a fifth of total gold export revenues in 2020/21. The figure has since dropped to zero………… There are 100,000 artisanal miners active in the region, producing an estimated 20 quintals of gold annually, according to Fiseha Meresa, director of licensing and administration at the Tigray Land and Mining Bureau. “However, the volume of gold being supplied to the central bank is zero. The production is all going to the black market,” Fiseha told The Reporter. Artisanal mining mainly goes on in northwestern Tigray, including in places like Chimbla, Asgede, Adi Daero, and Seyemt Adiabo. Rahma Adrbat, Nadier, Kola Tembien, and Hawazen are some of the gold-producing regions of central Tigray. The contraband gold is supplied to a central market in Addis Ababa, according to Fiseha……………………….(1) የትግራይ ሃያ ኩንታል ወርቅ (20 000 ኪሎግራም) ወርቅ በህወሓት ኮንትሮባንዲስቶች  ወደ አዲስ አበባ ተጎጉዞ ይሸጣል፣ የኦህዴድ ብልጽግና ኮንትሮባንዲስቶች  ህገወጥ ወርቅ ንግድ አሰባስበው ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ዓየር በዓየር ይሸጣል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አህያየን የሰረቃት ሌባ - ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

 

የማሞ ኢኮኖሚ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስትራቴጂክ ሠነድ መሠረት አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የኦህዴድ ብልፅግናን የሁለት ቢሊዮን ዶላር የወርቅ ኮንትሮባንዲስቶች ወደ  የኢምሬትስ ህገወጥ ንግድ ዘረፋ ስራን ሳያስቆሙ የውጭ ምንዛሪ አራት እጥፍ እናሳድጋለን ማለት ዘበት ነው፡፡ የውጭ ምንዘሪ መጠባበቂያ ከሁለት ወር ከአስራምስት ቀን ወደ አራት እጥፍ እናሳድጋለን፣ የወጋ ግሽበቱን ወደ ሃያ በመቶ ዝቅ እናደርጋለን፣ የውጭ ገንዘብ ህገወጥ ምንዛሪ መቆጣጠር ወዘተ በማለት የሃገሪቱን ማይክሮ ኢኮኖሚ ፊዚካልና ሞኒተሪ ፖሊሲ ማስተካከል አይቻልም፡፡ በጦርነት ኢኮኖሚ አገር ማሳደግ አይቻልም ጦርነት ሳይቆም፣ የኮንትሮባንድ ንግድ  ሳይወገድና ምርት ሳይመረት በፓርክና ጫካ ፕሮጀክት ብልጽግና አይመጣም፡፡ የትግራይ የወርቅ ኩብለላ በክልሉ የኢዛና የወርቅ ማዕድን ማውጫና ባህላዊ የወርቅ አንጥረኞች ሃያ ኩንታል ወርቅ ወይም (ሃያ ሽህ ኪሎግራም ወርቅ) በአመት ከትግራይ ክልል ተዘርፎል፡፡

በ2020/21እኤአ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ንግድ ገቢ መቶ ሚሊዮን ዶላር ያስገኘ፣ ሃያ ስድስት ኩንታል የወርቅ ማዕድን ከትግራይ ክልል ተገኝቶ ነበር፡፡ በ1998እኤአ የለገደንቢ ወርቅ መዕድን በ172 ሚሊዩን ዶላር ለአላሙዲን በርካሽ በሙስና ሲሸጥ ዘጠና ስምንት በመቶ ለሼኩና ለሚስታቸው ድርሻ ሲሆን ሁለት በመቶ የኢትዩጵያ ህዝብ ድርሻ ሆኖ መለስ ዜናዊ ቸበቸበው፡፡ የትግራዩን ወርቅ ለእራሱ ፓርቲ፣ ለኢፈርት ድርጅት ኢዛና አደረገ፡፡ ማሞ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ከፈለገ የኢትዮጵያን የወርቅ ማዕድን እንደ ሌሎች ሃገራቶች የወርቅ ማዕድን የኃብት ክፍፍል ለምሳሌ፣ የወርቅ ማዕድን በኢንዶኔዢያ 49 በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ነው፣በዚንባዌ 51  በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ነው፣በሞንጎሊያ 49 በመቶ እጅ የህዝብ ኃብት ሆኖ ቀሪው የኢንቨስተሩ ነው፡፡

በቻይናና በህንድ የወርቅና የተወሰኑ ማዕድናት በውጭ ሃገር ሰዎች ንብረት መሆን ሕጉ ይከለክላል፡፡  የማዕድን ኃብትን ከዘረኛ ኮንትሮባንዲስቶች ኃብትነት ወደ ህዝብ ኃብትነት መቀየር ያስፈልጋል፡፡ In related news MIDROC Gold, one of the subsidiary companies of the MIDROC Technology Group, is at loggerheads with the Ministry of Mines over mining royalty payment. When MIDROC Gold bought the Legedembi gold mine in western Oromia for 172 million dollars in 1998 it entered into an agreement with the Ministry of Mines to pay five percent royalty fee to the ministry under the previous law. The agreement signed between the two parties is valid for twenty years.

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፕሬዝዳንት ሙላቱ ሪፖርት እና የፋና ውይይት…. ግርማ ሠይፉ ማሩ

 

ይድረስ ለትግራይ ህዝብ ህወሓት የወርቅ ኃብታችሁን የት አደረሰው፣ ለርሃብተኛው ወገን ቢደርሰው!!! ህወሓት/ ወያኔ የጦር አበጋዞች ‹‹መስመር አዩ ኃይልና!››                                                                                                                                                                             

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ፋይናንስ ቢሮ፣ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን (2010/11-2014/15) መስከረም 2003ዓ/ም የቀረበ ሪፖርት መሠረት፡-በትግራይ ክልላዊ መንግስት የገንዘብና ፕላን ቢሮ በነደፈው የእድገትና ትራንስፎርሜድን ፕላን (2010/11-2014/15) በገፅ 17 መሠረት፤ ከ1999 እኤአ ጀምሮ፤በትግራይ ክልል አጠቃላይ፤የስነ-ምድር ካርታ ጥናት መሠረት፤በዓይነት፣ በሚሸፍነውና በመጠኑ የክልሉን የማዕድን ኃብቶች መለየት ተችሎል፡፡ እስካሁን የስነ-ምድር ካርታ ጥናት እንቅስቃሴ  መረጃ መሠረት 24,780 ሜትር ስኮይር የስነ-ምድር ጥናት ተጠንቶና ተጠናቅሮ ሪፖረቱ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ በትግራይ ክልል የስነ-ምድር ካርታ ጥናት ስብስብ መረጃ 46.2%  ደርሶል፤እናም ክልሉ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀማጭ አድርጎል፡፡ በዚህም ረገድ፤ የተወሰኑ ድክመቶች ስላሉ አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግላቸው ከሚገቡት መኃል፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት፣ የመመርመሪያ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ አገልግሎቶች ማሞላትና ሌሎቹም ነጥቦች ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ መሠረት 850 ኪሎ ግራም ወርቅ 850,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካፍለው 29,310 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1,218.80 ዶላር ስናባዛ 35,773,448 ሚሊዩን ዶላር  የህወሃት ጦር አበጋዞች በብሄራዊ ባንክ አከማችተዋል ማለት ነው፡፡ በጦርነቱ ወቅት አቦይ ስብሃት በቆላ ተንቤን በርሃ ዋሻ ውስጥ ሲያዙ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ ተይዞባቸው ኦህዴድ ብልጽግና ወርሶታል ይባላል፡፡ የትግራይ ህዝብ ወርቁ የት ደረስ? ብሎ በመጠየቅ የወያኔ ሌቦችን ማስወገድ ይገባዋል እንላለን፡፡ ‹‹Since 1999, geological map survey has been conducted so as to identify the type, coverage and amount of mineral resources in our region. Up to now, the activities of collecting geological information from 24,780 meter square and consolidating reports have been finalized. The geological map coverage of our region has reached 46.2% and around 850 kg gold is already deposited in the national bank of Ethiopia. In this regard, there were some limitations which need due attention such as fulfilling enough skilled manpower and inspecting equipments and laboratory services among others.››………………….……….. (2)

 

ምንጭ

(1) Gold rush: Tigray’s bullion driven to shadow market as central bank readies new trade offer/ByAshenafi Endale/January 13, 2024

(2) (Tigray Regional State, Five Years 2010/11-2014/15, Growth & Transformation Plan, Bureau of Plan and Finance, September 2003 E.C, Mekelle, page 17)

 

የኦህዴድ ብልፅጽግና ኮንትሮባንዲስቶች የኢትዮጵያ ወርቅ ማዕድን ወደ አረብ ኢምሬትስ እያጋዙ ነው!!!

 

1 Comment

  1. ትግሬ ህወአት የዘረፈው አይሰማውም ጻድቃንና ደብረጽዮንን ለመጠበቅ የረገፈው ልጁ አያመውም ። መለስ ዘራዊና የባንዳ ልጆቹን ቱልቱላ ሰምቶ እንዳይሆኑ ሁኗል። ጸሀፊው ግን መጻፍህን ቀጠል በዛ በኩል ያለው ተስፋ አስቆራጭ ሁኗል ቄሱ ቀጣፊ ፖለቲከኛውም ቀጣፊ ሁኗል እንግዲህ አይናቸውን መክፈት ከማለት ውጭ ምን ይባላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share