የተገረምሁበት የስብሐት ነጋ ቃለመጠይቅ – መንግስቱ ሙሴ (ዶ/ር) ከዳላስ/ቴክሳስ

ርጓሜው በአንዱ ጓዴ ነጥብ በነጥብ ከተነገረኝ በሁአላ የስብሐት ነጋ እና የ መምህር ገ/ኪዳን ደስታ ህልም አገር እና ሕዝብ ታሪክ የሚያጠነጥነው እና አልፋ እና ኦሞኤጋቸው ጥላቻ ነው። በተመሳሳይ ዘመን መኖራቸው እና ተቀራራቢ እድሜ ያላቸው መሆኑ እንጅ የሩቅ ምስራቅ እምነቶች Reincarnation የሚሉትን በነዚህ ሰወች ሊያሳምኑ በቻሉ ነበር።

ልክ እንደመምህር ገ/ኪዳን አቦይ ስበሀት ነጋም በ89 አመት እድሜው እና በመሰናበቻ በሚመስል ቃለምልልሱ ስለነበረበት የተሳሳተ አቈም ሳይሆን እና ንስሐ መግባቱን ሳይሆን ያየምናውቀውን ደግሞ ሊነግረን ብቅ አለ። አሁንም የትግል ጅማሮውን የቆየ ህወሓትን ሲመሰርቱ የነበረ አቋሙን አንድ ነጥብ ሳያጎድል ጨምሮ እና አክርሮ ተሰናበተን። አጅእብ ያሰኛል!!

 

መምህር ገብረ ኪዳን በ1965 ዓም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኘ ባህርዳር አፄ ሰርጸ ድንግል ሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ አስተማሪየ ሆኖ አስተምሮኝ ነበር። ከእድገት በህብረት የተማሪ ዘመቻ በኋላ እኔና የባሕርዳር ወጣት በሙሉ ማለት ይቻላል ኢሕአፓወች ስንሆን ገብረኪዳን አሮጌዋን ቮልስዋገኑን ሸጦ ደደቢት መግባቱን ሰማን። ልዩ የሚያደርግ መለያው በተማሪው ስለነበረው (እኛ የማይገባን ጥላቻ) የገብረኪዳንን ደደቢት መውረድ ፈልጌ ሳይሆን አንዱ እንደነገረኝ ትዝ ይለኛል። ከዚያን ግዜ ጀምሮ ወያኔ ሲሉን የሚታየኝ ገ/ኪዳን ይመስለኝ ነበር። ሁሉም ማለት ይቻላል የእርሱ ተማሪወች የነበርን በዚያ ዘመን መምህር በሚከበርበት እና እንደወላጅ አባት በሚቆጠርበት ዘመን መምህር ገብረ ኪዳንን ማክበር አስቸጋሪ ነበር መከበር የሚያስችል ባህርይ ስላልፈጠረበት። መምህሩ በዚያን ዘመን የዘርም ሆነ የቋንቋ ልዩነት ቦታ በማይሰጠው ዘመን ለባህርዳር ተማሪወቹ ያሳይ የነበረው መረን የረገጠ የጥላቻ አስተያየት የተማሪወችን ፍቅር አሳጥቶታል። ሰውየው ሰፊ ግዜውን በማስተማር ሳይሆን በጥላቻ ንግግር ያሳልፍ ስለነበር አብሮት የሚራመድ ጓደኛ እንኳን አልነበረውም (በበኩሌ አላየሁም)። በዚያን ዘመን እና በዚያ ከተማ ትግርኛን ከአማርኛ ተናጋሪ ነጣጥሎ ማየት አይቻልም ነበር እናም ወዳጅ አልባው መምህር የጥላቻ ፍልስፍናውን ሁሉም ስለማይወድለት ነበር ብቸኛ ለመሆን የቻለው። ገብረኪዳን በጥላቻ ፖለቲካ የጉልምስናውን ዘመን አሳልፎ ከጥላቻ ፖለቲካ ሳይነጻ እና ለአበረከተው ችግር ለንስሐ ሳይበቃ በጥላቻ ታንቆ የዛሬ ሁለት አመት ማለፉን አይተናል። የዚያን ዘመን ጓደኞቸ ስላሉ የሚለውን እንደሚጋሩኝ እርግጠኛ ነኝ።

 

የሁለት አመቱ ጦርነት

ስብሐት ነጋ በዚያ ጦርነት ቀስቃሽም መሪም ነበር። ታናሽ እህቱ ወጣቶችን ስልጠና ስታስገባ ስትቀሰቅስ የሚያሳይ ቪዲዮም ተለቆ አይቻለሁ። እናም ስብሀት የጦርነቱ መነሾ ማህከል እንደነበር ሁሉ ሰለባም ሆኖ እስርቤት ቆይቷል።

 

ከዚህ ሚሊዮኖችን ህይወት ካጠፋ፤ ብዙ ሚሊዮኖችን ለረሀብ ከዳረገ፤ ሌሎችን ካሰደደ እና ካፈናቀለ ባጠቃላይ ሰፊ ታይቶ አይታወቄ የማህበረሰብ ቀውስ ካስከተለ ጦርነት እና የጦርነቱ መንስኤ ደግሞ ለአለፉት 30 አመታት በሐገራችን የተዘረጋው ስርአት ሆኖ ሳለ። ዛሬም እንደሁልግዜው የስብሐት ነጋን ቃለምልልስ ትርጓሜ ከአዳመጥሁ በኋላ ወይ ጠቅላላ ሕዝብ እብድ ነው አለያም እብድ ነው ብለን የምናስብ ሰወች የአእምሮ ጤንነት የለንም ወደሚል ድምዳሜ ደረስሁ።

 

ስብሐት ነጋ ለሽምግልና ህይወቱ ቢሊዮን ዶላር ባለሀብት መሆኑ ከእስር ከተፈታ በሁአላ ወደአሜሪካ መጥቶ በዚህ እድሜ እና በምእራብ ቪላ እንክብካቤ እያገኘበት ሲሆን እርሱን እና የእርሱን ቤተሰብ የማረኩ ወታደሮችን እንዳይገድሉት መማጸኑ ባሳደገው አብይ እስርቤት ለትቂት ግዜ ቢቆይም በሐገር፤ በሕዝብ ላይ የሰራው በደል እንደደግ ተቆጥሮለት የተለቀቀ ሚሊዮኖች ትግራውያን ጭዳ የሆኑበትን ጦርነት በአንድ ወይንም በሌላ ምክንያት የእርሱ ውሳኔ ዋና ቃል ሆኖ ሳለ እና ያየሰራው በደልን ከምንም ሳይቆጥር ወይንም አሁንም ለንስሐ ሳይበቃ እንደ ከላይ የጠቀስሁት የድሮ መምህሬ ገ/ኪዳን ወደአይቀሬው ሞት እየተጓዘም ሕዝብን የማስታረቅ የማጣላት መጨረሻ ውጤቱ ምን ያህል ለሐገር እና ሕዝብ የሚከፋ እንደሆነ ከራሱ ልምድ ተምሮ እና ተጸጽቶ እንዳይደገም መማጸን ሲገባው ሳይሆን የመርዝ ልሐጩን ያዝረበረበበትን ቃለ መጠይቅ ሳዳምጥ “ያደቆነ ሰይጣን ሳይገድል አይለቅም” እንድሉ ያረገኝን እና ቤታቸው ሳይመለሱ ለቀሩ ሁሉ ወጣቶች ዳግም ልቢ እንዲሰበር ሆኗል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕወሐትና ከመንግሥት ውጭ ያሉ የሰብዓዊ መብት ረጋጮች ዛሬና ትናንት - አንድነት ይበልጣል

 

ይህ የጥላቻ ጎተራ ወደ 89 አመቱ መሻገሩን፤ የኩላሊት ህሙም እንደሚያመው እና ለዚያም ህክምናውን የሚሸፈንለት በወያኔወች መውጫጮ እንደሆነ በመግቢያ ንግግሩ ይገልጻል። እድላሙ አዛውንት እርሱ፤ ጓደኞቹ እና ወልዶ ያሳደጋቸው ኦነጋውያኑ በፈጠሩት ጦርነት ስንት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕጻናት እንዳለቁ፤ የትግራይ፤ የአማራ፤ የአፋር እናቶች ወልደው የወላድ መካን እንደሆኑ የወላድ መካኖች ያለጧሪ እና ቀባሪ የቀሩ እናቶች ዘክሮ ነፍስ ይማር የማለት እንኳን ሞራል ያልፈጠረበት መሆኑን ሙሉውን ላዳመጠ የረዳዋል ሲጀምርም ስለራሱ እና ስለሚደረግለት እንክብካቤ ብቻ በመግለስ ነው ቃለምልልሱ ውስጥ የገባ። ይህ ሰው በነዚያ ሙታን ወጣቶች ተረማምዶ ነው ዛሬ በምእራብ ሆስፒታል ህክምናውን የሚከታተለው እና ለ 90 ፈሪ የሆነ እድሜውን አርዝሞ አንድ መተ አመት ለመድፈን የተዘጋጀው አነጋገሩም እንደዚያ ስለሆነ ማለቴ ነው።

 

ለመጀመሪያው ጥያቄ የሰጠው እይታ በእርግጥም እውነት ነው። በትግራይ ውስጥ ያለ ችግርን ዛሬ በየትኛውም አለም የለም ይላል። አወ የትግራይ ሕዝብ ህወሓት በስልጣን ላይ ሆኖም በስሙ ተነገደበት ከወገኑ ለሽሆች አመታት አብሮ ከኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲለይ ተደረገ፤ በተለይ ከጎረቤቶቹ በክፉም በደግም ግዜ ችግርን ደስታን በጋራ ከተጋሩት ከአማራ፤ አፋር፤ ኤርትራ ሕዝብ ጋር ቂም እና ቁርሾእንዲኖረው ድፍን 27 ተሰራበት መጨረሻም ወደአየነው እና ይህን ሁሉ መከራ ወዳመጣው ጦርነት ተገባ ውጤቱ ሚሊዮኖች ትግራውያን/አማሮች/አፋሮች የአንድ አገር ልጆች ጭዳ የሆኑበትን ለአብይ አህመድ አረመኔ መንግስት አመቻችቶ የሰጠ ጦርነት ያስጀመረ አብይ እና የአረመኔው ቡድን ወደስልጣን እንዲመጣ የፎከረውን ያደረገው የስብሐት ግሩፕ የፖለቲካ ችንፈቱን በበቀል አራትኪሎን ለኦሕዴድ ሰጠን እንወጣለን የሚል ማስፈራራያ የፖለቲካ ብልጠት ሳይሆን የማይበርድ የጥላቻ በቀል የፈጠረው ጦርነት መሆኑን እየታወቀ ስብሐት አብይ አህመድን የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አስርጎ ያስገባብን ፍጡር ነው ይለናል።

 

27 አመት የኢትዮጵያን በትረመንግስት ይዘው ለእርቅ እና ለንስሐ የሚበቃ ግዜ እያለ አንድም ቀን የድርጅታቸውን ስም እና አላማ ወደሐገራዊ ድርጅትነት ሳይቀይሩ የደረሰባቸውን የለውጥ ግፊት እድሉም እያላቸው ይበቃናል ለታሪክም ለእኛም የመጨረሻችን እንዲያምር በሚል እንኳን ለውጥን ተቀብሎ ሕዝብን እንደማዘጋጀት እርቅ እና ሰላማዊ ሽግግር እንደማድረግ የፍለጠው ቁረጠው ፉከራቸውን እሲኪሰምጡ ያስቀጠሉት እነስብሀት ነጋ ዛሬም ከስህተት ተምሮ ንስሀ ገብቶ ለታሪክ መልካም መንገድ ጠርጎ ከማለፍ ይልቅ ስህተቱን ወደ ዋና ደጋፊያቸው ወደአሜሪካኖች እና ወደስለላ ድርጅት አሽቀንጥሮ ወደቀጣዩ መልስ ይሻገራል።

 

ቀጣዩ መልሱ ስብሐት ነጋ እና የዘር ኩባንያው እድሜ ዘመኑን ተናግሮት ያልጠገበው “የትምክህተኛው የአማራው” ጉዳይ ነው። ስብሐት ያልሰማው ምናልባት ሰምቶ አናንቆ ያለፈው የዳንግላ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ የነፍጠኛው ጦር እርሱ እና ቤተሰቡ አሳስረዋቸው የረሷቸውን የትግራይ መኮንኖች ከታሰሩበት አስለቅቀው ወደትግራይ ያሻገሯቸውን መኮንኖች ታሪክ ሳይሆን አሁንም ይህን አይነቱን የሕዝብ ከሕዝብ ትስሥብን ወደጎን ያረግና እንደገብረኪዳን የጥላቻ ቅርሻቱን “የትምክህተኛው ስርአት እንዳይመለስ አረገነዋል” በሚል እስኮር ካርዱን ይስባል። “ትምክህተኛ” ከጅምሩም የህወሓታውያን ኮድ ለአማራ ሕዝብ የተሰጠ ለአለፉት አምስት አመታት በወለጋ እና በመላ ኦሮሚያ ለተካሄደው የዘር ፍጅት አብሪ የሆነ መርህ ቃል ነው እናም ስብሐት የሚለው ለሁሉም ግልጽ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ሀገር አድን የጋራ ንቅናቄ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ እና መጪ የፖለቲካ ጉዳይ አንፃር ሲፈተሽ

ስብሐት በህገመንግስቱ ያምኑ የነበሩት ሁሉ እንደተነሱባቸው ይመልሳል። ተሐድሶ ብቻ አይደለም ጥብቅ ተሐድሶ አርገው እንደነበርም ለጠያቂው ይገልጻል። አዳማጭ ግን ዘር ከዘር የሚያፋጅ ሕገመንግስት ደንግጎ፤ ዘርን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ስርአት በባለ ብዙ ቋንቋወች ሐገር ዘርግቶ ሕገመንግስታችን አመል የማይወጣለት ነው መቀጠል ይኖርበታል የሚል ሰው ስብሐት እና ኩባንያው ካልሆነ ዛሬ የዚህን ህገመንግስት ውጤት ከአዲግራት እስከቦረና ያለው ሕዝባችን አይቶ መከራውን ተቀብሎበታል። ደጋግሞ በህገመንግስቱ አመል የለሽነት እና የእርሱም ኩባንያ ጥብቅ ተሐድሶ አርጎ ወደስራ እንደተመለሰ ነው ይህ ሁሉ ችግር በአሜሪካ የስለላ ድርጅት የተቃጣበት።

እዚህ እዚያም እድሜ መጃጀትን ያስከትላል እና የረገጠውን በመልኩ ለማድረግ ይህን ህገመንግስት በችሮታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተችው ወያኔ በአፍሪካ ወደር የለሽ ድርጅት መሆኗን ደጋግሞ አስረድቷል። ጠያቂው ወያኔ በመሆኑ አከታታይ ጥያቄ ሳይሆን ቀድሞ የተዘጋጄ እና ስብሐት እንዲያጠናው የተደረገ ጥያቄ በመሆኑ እንዴት እና በምን በምን ወያኔ ታይታ የማትታወቅ ሆነች ወይንም አንድ ሚሊዮኖችን ማስጨረስ? አገርን አደጋ ላይ መጣል? ነው ወይንስ ጥላቻ የኔ የናንተ ባይነት መርህ ወይንስ ምን ብሎ አልጠየቀውም።

 

በጦርሜዳ እንደተፈታተኑት ኢትዮጵያን እኛ ካልመራናት ኢሳያስ ሊመራት ነው በሚመስል 27 አመት የፈጠረባቸው ንቃቻ ከዚህ ጦርነትም በኋላ አለመላቀቃቸው “ኢሳያስ የሚቆጣጠራት ጠንካራ ኢትዮጵያ ይፈልጋል ይላል።” ይህ አባባሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ቢሆንም የስብሐት ገብረኪዳን የልብ ህመም ሁሌ ደካማ እርስ በእርሳቸው የማይተማመኑ የአፓርታይድ መሰል የጎጥ መንደሮች ፈጥሮ መግዛት እንጅ አንድ እና ጠንካራ የሆነች ኢትዮጵያ አላማቸውም፤ እምነታቸውም ህልማቸውም አለመሆኑን ማሳያ ንግግር ነበር። ጠንካራ ኢትዮጵያ ካለች መልሳ ዜጎቿን በሚመቻቸው የምታስተሳስር እንጅ ለአንድ ፈላጭ ቆራጭ ንጉስ የምትመች ልትሆን እንዴት ትችላለች ብሎ ግን ጠያቄ አልጠየቀ። የስብሐት ፍርሐት “ኢሳያስ” ሳይሆን የታላቋ ኢትዮጵያ የመልሶ መወለድ አይቀሬነት ነው ይህን ደግሞ ትምክህተኛውን እንዳይመለስ አጥፍተነዋል ያለው የአማራ ሕዝብ ዛሬ ነፍጥ አንስቶ ለህልውናው ገዝወችን እያስጨነቀ መሆኑን ስብሐት ግጥም አርጎ ያውቃል። የስብሐት ነጋ ቅጥቃጤ  እና ፍርሐት ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የጠየቁት ምእራባውያን ከህወሓት እና ሻብያ ጋር ሆነው የፈጠሩልን ዳር ድንበር ሳይሆን የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትሥስር በሁለቱ ሉአላዊ ሕዝባችን ውስጥ እንደገና ሊያድግ ሊመነደግ መሆኑን ይህ አምስት አመት አሳይቶታል።

 

ይህን የሁለቱ ሕዝቦች ትሥር እና በየትኛውም Arrangement አብሮ መኖር ቀደምት የሁለቱን ሕዝቦች ጦርነት የተቃወሙ የኢትዮጵያ ተራማጆች የኤርትራን የግራ ቀኝ ጦርነት ጥንትም ሲቃወሙ የኤርትራ ሕዝብን ሉአላዊ ግዛት ሳይነኩ በሕዝባችን መካከል የኢኮኖሚ ትስስር የመፍጠር መልሶ የወንድማማች እህታማቾችን ሕዝብ አንድነት ትብብር ማጠንከር ታላቅ ቀጠና መፍጠር ይቻላል ጦርነት ግን አውዳሚ ነው አይገባም ይሉ ነበር። ስብሐት እና ኩባንያው ከጥንት ከጥዋት ጀምረው የሚፈሩት አጥብቀው የተከላከሉት ጉዳይ ይህን በዚያ ትውልድ ተራማጆች ይቀነቀን የነበረውን የሕዝብን ፍላጎት እንጅ ማስገደድን አለመቀበልን ነበር። በዚህም ቃለ ምልልስ “ኢሳያስ የሚቆጣጠራት ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትኖር ይፈልጋል” ስብሀት ነጋ ሲል ይህን ማለቱ ነበር። በተረፈ ማንም አንባገነን ጠንካራ ኢትዮጵያን እንደፈለገ ማድረግ አይቻለውም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቴዎድሮስ - ፋሲካ ገ/ጻዲቅ ወ/ሰንበት

 

ስብሐት የፕሪቶርያን ስምምነት ይጠቅሳል። በዋናነት በዚህ ቃለመጠይቅ የተናገረው “ፕሪቶርያ ስምምነት ለህወሓት አንድ ድል ነው ይላል።” ስብሐት እንደ ድል አድረጊ ተግባር የቆጠረው ደግሞ ከስምምነቱ በኋላ የአብይ ብልጽግና፤ ኢሳያስ፤ አማራን አጣልቷል ባይ ነው።” ይህ አባባሉ በጣም ያሳፍራል። እንደ አንድ Statesman ለ 50 አመታት በፖለቲካ ተግባር እንዳሳለፈ ሰው የጎረቤት ቤት መቃጠል ለእራስም ይተርፋል እንዲሉ አስብለታለሁ ለሚለው የትግራይ ሕዝብ እንኳን ምን ያህል የጭካኔ ልብ ቢኖረው ነው በዙሪያ ለሚኖሩ የትግራይ ሕዝብ ወገኖች ሰላም ማጣትን እንደድል ሊቆጥር የሚችለው? አዲሱ የትግራይ ትውልድ ይህን አይነት መርዝ አስተሳሰብ የያዙ ቆመው የሚሄዱ ሰው መሰል ሰይጣኖች ከየት ተነስተው የት እና እንዳደረሱ ጠንቅቆ ተረድቷል። በዙሪያው በጎረቤቱ ሰላም ከሌለ እዚያም ሰላም እንደማይሆንም ያውቃል፤ በተግባርም አይቶታል። በዚህ የስብሐት አባባል መጀመሪያም ብልጽግና የህወሓት የእንግዲህ ልጅ እንጅ የአማራ ወዳጅም ሆኖ አያውቅም ሊሆንም አይቻለውም። ብልጽግና የኢሓዴግ/ህወሓት ቁጥር ሁለት እና የኢሕአዴግ/ህወሓትን አላማ እስከምናምኑ አስቀጣይ እንጅ ኢትዮጵያን ወደነበረችበት ክብሯ የሚመልስ፤ አንድነቷን የሚያጠናክር ሳይሆን አሁንም የዘር ጥላቻን አስቀጣይ አማራን እና ኦርቶዶክስ ክርስትናን በትምክተኝነት በመክሰስ የህወሓትን ዋና ጠላት ጠላቱ አርጎ የወረሰ እና ያነኑ የግድያ እና የማፈናቀል ስራውን እየሰራ ያለ ድርጅት ነው። ማሳያው ደግሞ ስብሐት አሁንም ከመቃብሩ ደጃፍ ሆፕኖ የሚጨነቅለትን ዘረኛ ህገመንግስት ከእርሱ በላይ የሚጠበብበት ድርጅት መሆኑ ነው።

 

ይህን ቃላ መጠይቅ ከሰማሁ ካስተረጎምሁ በኋላ ያ በልጅነት የማውቀው የሰው ዘር ጠል የነበረው ገብረኪዳን ደስታ እና ስብሐት ነጋ በመንፈስም በሁለንተና ነገረስራቸው አንድ እና ምንም ልዩነት የሌላቸው መሆናቸውን የተረዳሁበት ሆነ። ፈሪው ስብሐት ነጋ አድገው ያልጨረሱ የትግራይ ወጣቶችን በጦርነት እሳት ከጣደ በኋላ ሲያዝ ካሳዘነኝ እና ያኔ ከሰማሁት የያዙት ወታደሮች እንዳይገድሉት የተማጸነው ነው። እንዲህ አይነት ለሰው ህይወት፤ ለሰው ልጅ መቸገር፤ ክፉ ነገር ላይ መውደቅ ጉዳያቸው ያልሆኑ ፈሪወች በራሳቸው ሲደርስ ሞትም እየጠራቸው ሞትን ፈርተው ሲለማመጡ ማየት ነው ልዩ የሆነ ለነሱ የተሰጠ ባህርይ። እናም ጨካኝ ናቸው ደፋር ግን አይደሉም። ጥላቻቸውም የሚመዘዘው ከዚህ ቦቅቧቃ ስነልቦናቸው ነው። እንዲህ አይነት ፈሪወች ጥግ ድረስ በጥላቻ ስለተዋጡም እስከመቃብራቸው ንስሐ አይቀበሉም የሀይማኖት እምነትም አልፈጠረባቸውም እናም ለምንም ምድራዊ እና ሰማያዊ ህግ አይገዙም። የሚገዙት ለነሱ ደስ የሚላቸው ሰው የሚያስከፋው ጥላቻ እና መለያየት ነው። ገብረኪዳን ደስታ እስኪሞት ተናግሮት ሳይተግብ ያለፈው ጥላቻን ነው። ብዙ ሽሆች ሚሊዮኖች ባይሆኑ ተዋልደው አብረው በኖሩባት ሐገር ልዩነትን እና ጥላቻን እስከ የህይወቱ ፍጻሜ ሲሰብክ ኖረ። አቦይ ስብሐት ነጋም ያነኑ ደገመው ስንት ዘመን እንደሚኖር ግን የሚያውቅ የለም ከፈጣሪ በቀር ግን ይህን እድል ለፍቅር፤ ለአንድነት፤ እና ለንስሐ ሊጠቀምበት በተገባ። ADIOS!!

 

1 Comment

  1. ስብሃት ነጋ የአጋንንት አለቃ ንገረው ያሳደግኸው ጥጃህ ነው እሱም ላንተ ልዩ ፍቅር አለው። ንገረው እስከ ዶቃ ማሰሪያው ያልገደሉ፤ያልበሉ፤የተጎሳቆሉ ምስኪን አቶ ታድዮስ ታንቱን አስሮ አንተን በክብር ሲያሰናብትህ አላማው ሌላ ነበር አልሆነም። አትሳሳለት በተከታታይ ቃለ ምልልስህ አበራየው። ልጅህ ቴዎድሮስ ጸጋዬና ስታሊን ገ/ስላሴም በር ከፍተው እየጠበቁህ ነው እስከ ምናምንህ ከጉድጓድ ተሸክመው ያወጡህንና አንተም ያሳረድካቸውን የኢትዮጵያን ወታደሮች ዝለፋቸው ዉለታቸው ይህ ነው። ምን ዋጋ አለው መሪው ሌላ ቢሆን የዘረፍከውን አንድ በአንድ አስመልሶ አንተንም እንዳሰቃየኻቸው ዜጎች መደብደቡ ቢቀር እስር ምን እንደሚመስል ልታውቅ በተገባህ ነበር። ለነገሩ ጻድቃንም 900 ሚሊዮን ብር አጥቁሮ እንዲያስወጣ ፈቅዶለት የለ? በል እንግዲህ አእምሮህ ያሰቃየኻቸውንና የገደልካቸውን ክፉ ነገር የሰራህባቸውን እያስታወሰ እረፍት ይንሳህ ሌላ ምን ይባላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share