የኦህዴድ ብልፅጽግና ኮንትሮባንዲስቶች የኢትዮጵያ ወርቅ ማዕድን ወደ አረብ ኢምሬትስ እያጋዙ ነው!!!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

ለብልጽግና ጭፍራ ለኢምሬትስ ቡችላ፣

አይገዛም ህዝቡ ከዛሬ በኃላ!!!

የኦህዴድ ብልፅጽግና  ኮንትሮባንዲስቶች የኢትዮጵያ ወርቅ ማዕድን ወደ አረብ ኢምሬትስ እያጋዙ ነው፣ ወያኔ የኢዛናን የወርቅ ማዕድን ወደ አዲስ አበባ !!!

የኮነሬል አብይ የገንዘብ ምንጭ፡-የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት በኮነሬል አብይ ኮንትሮባንዲስቶች ወደ ጎረቤት አገሮች እየተጋዘ መዳረሻውን ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እየተጫነ እንደሆነ ተረጋግጦል፡፡ አረብ ኢምሬትስ በልዋጩ  ድሮዉንና ቁምቡላ ተተኮሽ ታቀርባለች፡፡ ኮነሬል አብይ ለአገር ውስጥ የፓርኮችና የጫካው ፕሮጀክቶቹ ዋና የገንዘብ ምንጩ ከወርቅ የዶላር ሽያጭና ከአዲስ አበባ የመሬት ችብቸባ በሚገኝ ሚስጢራዊ ገቢ ነው፡፡

የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን፡- በኮነሬል አብይ ኮንትሮባንዲስቶች የሼክ መሃመድ አላሙዲንን የሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃብት ከኦሮሚያ ክልል ጋር እኩል በመካፈል ብሎም የወርቅ ሽያጭ በኮነሬል አብይ ኮንትሮባዲስቶች  ድንበር ተሸግሮ እንዲሸጥ በማድረግ ለተባበሩት አረብ ኢምሬት የወርቅ ቆት  እየተጋዘ እንደሆነ ተረጋግጦል፡፡

ኢዛና የወርቅ ማዕድን፡ በኮነሬል አብይ ኮንትሮባንዲስቶች የትግራይ ክልል ከኢዛና የወርቅ ማዕድን ማውጫና ባህላዊ የወርቅ አንጥረኞች ሃያ ኩንታል ወርቅ ወይም (ሃያ ሽህ ኪሎግራም ወርቅ) በየአመቱ በኮንትሮባንድ ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ ይጫናል፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ህወሓት/ወያኔ ለኦሮሙማው መንግሥት የወርቅ ግብር ለመገበር ሚስጢራዊ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ህወሓት የትግራይን ህዝብ በአሞሌ ጨው ነው የሸጠው የትግራይ ክልል መንግሥት በሃያ ሰባት አመት አገዛዙ ዘመን ብሔራዊ ባንክ ዘርፎ ያስቀመጠው 850 ኪሎ ግራም (850,000 ግራም ወርቅ) ወርቅ ኃብት በኦህዴድ ብልጽግና በጦርነቱ ሰሞን ተዘርፎል፡፡  ከትግራይ ህዝብ የተዘረፈው ወርቅ ለርሃብተኛው ህዝብ በአስቸኳይ እንዲውል እንጠይቃለን፡፡

 

የኢስት አፍሪካ ስታንድ ባይ ፎርስ (East Africa Stand by Force):- ለመመሥረት ኬንያ ናይሮቢ ቢሮ ከፍቶ የነበረው ድረጅት ወደ ቅጥረኛ ካንፓኒነት (Mircenary Company) መቀየሩን ውስጥ አዋቂ ሚዲያ የኩሽ ሚዲያ ኔትወርክ ‹‹ በደመ ነፍስ ያለው የብልጽግና ስርዓት›› በሚል ርዕስ በአዘጋጁ ሀብታሙ ተስፋዬና በዶክተር ፀጋዬ አራርሳ የተደረገ ውይይት የኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥትና የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ መኃል ያለን ሚስጢራዊ ግንኙነት ዶክተሩ አብራርተዋል፡፡ ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ አንደበት ‹‹ቅጥረኛ ኩባንያ፡- በምስራቅ አፍሪካ፣ በመካከለኛውና በአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች የሚቆጣጠር ቅጥረኛ ኩባንያ የኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥትና የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ መመሥረቱን ይገልፃል፡፡ የቅጥረኛ ኩባንያ መሪ ብርጌደር ጀነራል ወንድወሰን ተካ፣ ምክትል መሪ ብርጌደር ጀነራል ጌታቸው ሽፈራሁ፣ አስተባባሪ ብርጌደር ጀነራል ባጫ ደበሌ፣  የቢሮ አስተባባሪ ጂክሳ ባጫ ደበሌ ናቸው፡፡ ቅጥረኛ ኩባንያ ልክ እንደ ራሽያ ወግነር ቅጥረኛ ድርጅት በአፍሪካ አህጉር በተለይ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የአረብ ኢምሬትስ ጥቅም ለማስጠበቅ የተዋቀረ ድርጅት ነው፡፡ ኢምሬትሰና ሳውዲ አረቢያ የአፍሪካ አህጉር ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡ የኢምሬትስን ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውር ማሳለጥና የወርቅ መዓድን ሃብቶችን ግዢ፣ ህገ ወጥ የቁም እንሰሳት ግዥን ያለአንዳች እንከን በግዢ ማሰባሰብ ዋነኛ ተቀዳሚው ሥራ ሲሆን  ከለገደንቢ እስከ ማላዊ፣ ከቀይ ባህር አስከ ሞንባሳ የመቆጣጠር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ከኢትዮጵያ የሚወጣውን ወርቅና ሌሎች የማዕድን ኃብቶችን ሠብስቦ በመግዛት ወደ ኢምሬትስ የሚልክ ድርጅት ነው፡የዩናይትድ  አረብ ኢምሬትስ የኢትዮጵያን የመከላከያ፣ ደህንነትና የዲፕሎማሲዊ ሥራ በኢምሬትስ ቁጥጥር ስር የመከወን፣ የምሥራቅ አፍሪካን ስትራቴጅካል  አመራር በመስጠት፣ የቀይባህርን አጀንዳ በመቅረጽ፣ የሶማሌላንድ የወደብና የባህር በር ስምምነት በማቀነባበር ከፍተኛ የፖለቲካ ሴራ  በሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን አመራር ገንዘብ ሰጭነትና  ኮነሬል አብይ አህመድና አስፈጻሚነት የሚከናወን ሚስጢራዊ ግንኙነት የተቆቆመ ቅጥረኛ ካንፓኒ የአፍሪካን አህጉር በመበጥበጥ ላይ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንዴት ለዚህ በቃን?--ገዥዎቻችንስ እናውቃቸውለን ወይ?

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና የአፍሪካ አህጉር፡ኢምሬትስ ከአፍሪካ አህጉር በህጋዊና ሕገወጥ መንገዶች በድብቅ የወርቅ ኃብት በመዝረፍ ላይ ትገኛለች፡፡ በ2006 እኤአ ኢምሬትስ ከአፍሪካ ያጋዘቸውና የገዛችው ወርቅ 67 ቶን ወርቅ ምርት $1.3 (አንድ ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ በ2016 እኤአ የተባበሩት አረብ ኢምሬት በወርቅ የውጭ ገቢ ንግድ 446 ቶን ወርቅ ምርት በ $15.1 (አስራአምስት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ከአፍሪካ አገራቶች ገዝታለች፡፡ Customs data shows that the UAE imported $15.1 billion worth of gold from Africa in 2016, more than any other country and up from $1.3 billion in 2006. The total weight was 446 tonnes, in varying degrees of purity – up from 67 tonnes in 2006…………………………………..…(1)

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና ኢትዮጵያ፡የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ በተለይ የወርቅ ማዕድን ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በ2020እኤአ $860M (ስምንት መቶ ስልሳ) ሚሊዮን ዶላር ሲሆን በ2021እኤአ $788M (ሰባት መቶሰማንያ ስምንት) ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ ወደ ኢምሬትስ ተልኮ ነበር፡  ኢትዮጵያ የወርቅ ምርቶን ወደ ሃገረ ሲውዘርላንድ ትልክ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ኮነሬል አብይ ቀጭን ትእዛዝ የወርቅ ኤክስፖርት መዳረሻውን ወደ ኢምሬትስ አደረገ፡፡ The main destination of Gold exports from Ethiopia are: United Arab Emirates ($860M). The fastest growing export markets for Gold of Ethiopia between 2020 and 2021 were United Arab Emirates ($788M).

 

ታከለ ኡማና ስደተኛው ወርቃችን (The Gold Exile)

ኢንጅነር ታከለ ኡማ የማዕድን ሚኒስትር ሆነው በተሸሙ ጊዜ ኢትዮጵያ በወርቅ ማዕድን የውጭ ንግድ  672 ሚሊዮን ዶላር  በማግኘት 242 በመቶ እድገት ማስመዝገቦ በ2020/21 እኤአ ይታወሳል፡፡ Takele Uma, who was appointed minister of mines, has been lauded for achieving a historic high in the mining industry, with gold exports exceeding USD 672 million two years ago. Under the minister, gold exports skyrocketed by 242 percent in 2020/21. ኢንጅነር ታከለ ኡማ የለገደንቢና የአዶላ የወርቅ ማዕድን ቦታዎች በኦሮሚያ ክልል ኃብት በማድረግ ከሼክ መሃመድ አላሙዲን ሜድሮከ ጎልድ ጋር በድብቅ በሮያሊቲ ጉዳይ ድርድር በማድረግ  አርባ ስልሳ የሃብት ክፍያ በማድረግ የኦሮሙማ ሥርዓት በኃብት ማማ ከፍ ለማድረግ ዘመቻ ተደረገ፡፡   ታከለ ኡማ የወርቅ አውጭ ካንፓኒዎችን የንግድ ፍቃድ ሲሰርዝና ሲፈቅድ ዘመኑን ጨረሰ፣ የወርቁም ንግድ በኦህዴድ ስምጥ ገባ፡፡ የማዕድን ሚኒስትር የወርቅ የውጪ ንግድ ገቢ 117.4 ሚሊዮን ዶላር ወይም 59 በመቶ  መቀነሱ በመንፈቅ ዓመት በሪፖርት ተገልፆል፡፡ One of Ethiopia’s major exports, gold, generated close to USD 117.4 million in exports during the first six months of the existing fiscal year, according to the Ministry of Mines…“A large volume of gold extracted from Ethiopia is being smuggled,” said Takele,… In the last six months, according to Takele, 1,910.5 kg of gold were mined, or 39 percent of the target. The same month’s earnings are also less than half of what was expected for the reporting period, which stood at USD 306.8 million. Switzerland is the destination of more than 99 percent of the gold exports from Ethiopia……………………………………………….(2) በኮነሬል  አብይ ትእዛዝ ኢንጅነር ታከለ  ኡማ የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ መረብ ዘርግተው ከስልጣን ተነስተው ወደ አሜሪካ ለትምህርት በሚል ስበብ ተሠናበቱ፣ ወርቁም እሳቸውም ስደተኛ ሆኑ፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት መሪ ኮነሬል አብይ አህመድ በኮንትሮባንድ የወርቅ ሽያጭ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ተቆጣጥረዋል፡፡ የቡና ፣ ሠሊጥ፣ የቁም ከብት እጣ ፈንታ!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለዲ/ን ኒቆዲሞስ፦ በውቀቱ ስዩም፣ ጓደኛው ተመስገንን “ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር ...”  እንዳለበት አልመከረም! ውሸት ነው!

የወርቅ ሰደተኛነት (The Gold Exile) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የወርቅ ማዕድን ከጠቅላላ የውጭ ንግድ አንድ አምስተኛ በመሸፈን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክት ነበር፡፡ በወርቅ ማዐድን ኤክስፖርት የተገኘ ገቢ ከ654 ሚሊዮን ዶላር ወደ 32 ሚሊዮን ዶላር ያሽቆለቆለበት አመት ነበር ፡  የወርቅ ማዕድን ምርት በዘላቂነት ማስቀጠል ያልተቻለበት ዋነኛ ምክንያት ህገወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፣ የሜድሮክ የወርቅ ማእድን በዓየር ብክለት ተከሶ ምርት መቆረጥ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ A decade ago, gold constituted close to one-fifth of the total export earnings of Ethiopia. But the country has not been able to sustain this momentum. Last year, export income from gold plummeted to a dismaying USD32 million from 654 million in 2011/12 fiscal year. This is largely due to the growth of contraband trade and the closure of mining companies for allegedly polluting the environment. EBR’s Ashenafi Endale investigates…………………..……(3)

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (Ethiopia National Bank):- ከባህላዊ ወርቅ አንጣሪዎችና ወርቅ ማዕድን አምራቾች የሚቀርብለትን ወርቅ በመግዛት ወደ ባንክ ገቢ ያደርጋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባህላዊ ወርቅ አንጣሪዎች በ2010/11 እኤአ 878 ኪሎግራም ወርቅ ተብስቦ የነበረ ሲሆን በ2018/19እኤአ 230 ኪሎግራም ወርቅ ብቻ የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጾል፡፡ በደቡብ ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ ክልል ባህላዊ ወርቅ አንጣሪዎች 500 ኪሎግራም ወርቅ ለመሰብሰብ ታቅዶ 24 ኪሎግራም ወርቅ ብቻ መሰብሰቡ ታውቆል፡፡ “In fact, less than five percent of the gold targeted to be collected at the center was attained in the past three years. Even worse, in Ethiopia’s southern state where the gold center is located, gold sourced from artisanal miners dwindled from 878 kilograms in 2010/11 to 230 kilograms in 2018/19. It is no different in the first quarter of the current fiscal year. In the Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region (SNNPR), only 24 kilograms of gold were collected from artisanal miners out of the targeted 500 kilograms in the first quarter of 2019/20.

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሤራና ግድያ ሀሤራና ግድያ ሀገርን ያፈርሳል እንጂ አይገነባም! - አሣምነው ጽጌ

 

በሁለተኛው እቅድና ትራንስፎርሜሽን ፕላን (Growth and Transformation Plan (GTP II))፡- የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ንግድ ገቢን ለማሳዳግና የውጪ ምንዛሪ ገቢን በማዕድን ዘርፍ ገቢ ከ344 (ሥስት መቶ አርባአራት) ሚሊዮን ዶላር 2014/15 እኤአ  የነበረውን 2.0 (ሁለት) ቢሊዮን ዶላር እስከ 2019/20እኤአ  ለማሳደግ እቅድ ተነድፎ ነበር፡፡ የወርቅ ማዕድን የውጪ ንግድ ገቢ ድርሻ 90 በመቶ  የውጪ ምንዛሪ ገቢን ይሸፍናል፡፡ In its second Growth and Transformation Plan (GTP II), the Government of Ethiopia planned to expand the export base by strengthening the export performance of selected sectors, including mining. The government set an ambitious target of increasing foreign exchange earnings of the mining sector from 344 million USD to 2.0 billion USD between 2014/15 and 2019/20. Enhancing the performance of the gold export sector is crucial in achieving this target, as gold contributes well above 90 percent of the foreign exchange earnings of the mining sector. ……………………….….(4)

በኢትዮጵያ የወርቅ ማዕድን ኢንዱስትሪ በሁለት ይከፈላል ዘመናዊና በባህላዊ ወርቅ አምራቾች ይገኛሉ፡፡ የባህላዊ ወርቅ አምራቾች ለአንድ ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረና ሃምሳ በመቶ የወርቅ ምርት በማምረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሽያጭ ገቢ ያደርጋሉ፡፡ የወርቅ የውጪ ንግድ ገቢ ከአጠቃላይ ብሔራዊ ምርት ድርሻ አንፃር እየቀነሰ መጥቶል ለምሳሌ በ2012/13እኤአ 18.6 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2016/17 እኤአ 7.2 በመቶ አሽቆልቁሎል፡፡ ከአጠቃላይ የወርቅ ምርት የባህላዊ ወርቅ አምራቾች  ድርሻ በ 2012 እኤአ 68 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2016እኤአ 48 በመቶ  አሽቆልቁሎል፡፡ Gold export earnings as a proportion of total commodity earnings have been on the decline in recent years, shrinking from 18.6% in 2012/13 to 7.2% in 2016/17. During the same period, the share of artisanal gold mining in total gold exports declined from a peak of 68% in 2012 to 48% in 2016.

 

ምንጭ

(1)Gold worth billions smugeled out of Africa.

(2)Gold exports dropped 59% to 3-year low/ByEyob Tikuye/January 14, 2023

(3)The Gold Exile/ Why & How Ethiopia is Losing its Precious Commodity

(4)Performance of artisanal gold exports in Ethiopia/ProjectActive from 15 Nov 2018 to 31 May 2019 Firms and Firm capabilities

 

1 Comment

  1. የአብይ ስኬት አማራንና ኢትዮጵያን ማውደምና ማጥፋት ነው ኢኮኖሚው ባናቱ ቢተከል ጉዳዩ አይደለም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share