December 12, 2023
4 mins read

የደብረ ብርሃኑ ስብሰባ ብልጽግና በሰሜን ሸዋ ዞን ጨርሶ እንዳበቃለትና እንደተንኮታኮተ የሚያስተምር ነበር

Beka 2ኅዳር 29/2016 ዓ.ም በአቶ አረጋ ከበደ የሚመራ ቡድን ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ ለብልጽግና የታመኑ ናቸው ተብለው የተመለመሉ ሰዎችና የድርጅቱ አባላት በተገኙበት ስብሰባ አድርጎ ነበር። አቶ አረጋም ሆነ ሌሎች ወታደራዊ ባለስልጣናት በመድረኩ ላይ መንግስት የህዝብ ጥያቄ እንደሚሰማ፣ ለድርድር ፍላጎት እንዳለው ነገር ግን የትጥቅ ትግል የጀመረው ሃይል ለድርድር ፍላጎት እንደሌለው አስረድተው ከቤቱ አስተያየት ጠይቀው ነበር። የተሰበሰቡት የብልጽግና የውስጥ ሰዎች እንደወትሮው “አቶ አረጋ ሆይ ትክክል ብለዋል፣ ከመንግስታችን ጋር አብረን ቆመን ልማታችንን እናስቀጥላለን፣ አይዞን…..” የሚል ዲስኩር አልነበረም። ይልቁን እነ አቶ አርጋን ያስደነገጠ ጥያቄና አስተያየት መዥጎድጎድ ነበር የጀመረው። ደፋር ሴቶች እየተነሱ መንግስት ማዳመጥ አይችልም፣ መምራት አልቻለም፣ አብይ አህመድ አልቻለበትም፣ ሀገራችንን አስፈሪ ሁኔታ ላይ ወድቃለች፣ ብልጽግና ቅቡልነት የሌለው ፓርቲ ነው……… ወዘተ . የሚሉ ጥያቄዎች ሲጎርፉ የነ አረጋ ከበደ ፊት ተለዋውጦ ፍርሃት ነግሶ ነው የዋለው። አቶ አረጋን ያስደነገጠው ይህ አመለካከት በአካባቢው ባሉ እጅግ ታማኝ በተባሉ የብልጽግና ሰዎች ህሊና ውስጥ ነግሶ መገኘቱ ነበር። በስብሰባው ላይ የወታደሩ አዛዦች የነበሩ ሲሆን በስብሰባው ድባብ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀው ታይተዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጃችኋል ነገር ግን አታሸነፉትም ብለው በድፍረት ተናግረዋል። አንዲት ብርቱ ሴት ደግሞ ለመሆኑ የአማራ ህዝብ ጥቁር ክላሽ ታጥቋል እያላችሁ የምታወሩት ለመሆኑ ይሄ ለአማራ ያንሰዋል ወይ? አማራ ይህንን መታጠቅ አያንሰውም…… ስትል የአማራን ትግል በነ አረጋ ፊት ፍርጥ አድርጋ ተናግራለች ። ተሳታፊዎች ሁሉ መንግስት በተለይም አብይ አህመድ ከፍተኛ የእውቀት ችግር እንዳለበትና መምራት እንዳልቻለ ያረጋገጡ ሲሆን ባለስልጣናቱን በአንድም በሌላም መንገድ አስፈራርተው አሰናብተዋቸዋል። አረጋ ከበደ እና አብረውት የነበሩት ባለ ስልጣናት ሁሉ እንዴት የራሳችን የምንለው የብልጽግና አባል እንዲህ ይከዳናል በማለት ከፍተኛ ብስጭት ገብቷቸው ነው የዋሉት። የስብሰባውን ውሎ የተከታተሉ ወገኖች ይህ ስብሰባ የሚያሳየው የብልጽግና መዋቅር በሰሜን ሸዋ ዞን ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ነው ብለው ደምድመዋል።

 

ክብር ለኢትዮጵያ!

 

በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት አንዱ ያቀበሉን መረጃ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop