የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ ወጥመድ ተይዟል!!! ‹‹የጫካው ኢኮኖሚ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣ በፍፁም ሣር አይበላም!!!›› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

/

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY) ጥናታዊ ፁሁፍ

ኢኮኖሚውን ያላወቁ፣ በትረ-ሥልጣኑን አይነቀንቁ!!!

የኢትዮጵያ ህዝብ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት ለጦርነት ኢኮኖሚ የሚያውለውን ብድር በተመለከተ የአፍሪካ ወንድሞቹን ምሳሌያዊ አነጋገር ‹‹የጫካው ኢኮኖሚ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣ በፍፁም ሣር አይበላም!!!›› ይላቸዋል፡፡ ብልጽግና መንግስት ከዓለም ባንክና አይኤምኤፍ ብድር ወስዶ ውጦ ውጦ፣ የማይዋጥ የማይተፋ የጉሮሮ ውስጥ አጥንት ሆኖበታል! ቀይ ባህር ኬኛ!  ከአስር የፖለቲካ ዲስኩር አንድ የኢኮኖሚ ዲስኩር ይጠቅማል!!! ወያኔና ኦህዴድ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዘርፈዋል ወርቁን ዶላሩን ባህር ማዶ አሽሽተዋል፡፡ ኢኮኖሚውን ያላወቁ፣ በትረ-ሥልጣኑን አይነቀንቁ!!! የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠንቅቀው ያወቁ ፖለቲካኞች በትረሥልጣኑን ይቆጣጠራሉ!!! ኢትዮጵያዊያን የአበዳሪ አገሮች ተጨማሪ ብድር ለብልጽግና መንግስት እንዳይሰጡና የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ታላቁ የኢትጵያ የህዳሴ ግድብ፣ ኢትዮቴሌ፣ ሒልተን ሆቴል፣ ጊዮን ሆቴል የህዝብ ኃብቶች እንዳይሸጡ፣ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢትዮጵያዊያን አጥብቀው መታገል አለባቸው እንላለን!!! የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ኃብቱን፣ መሬቱንም፣ ባንኩንም፣ ታንኩንም በትግሉ ያስመልሳል፡፡ የኮነሬል አብይ አህመድና የሼክ መሃመድ ቢን ዛአይድ አል ናህያን ሚስጢራዊ ግንኙነት አገራችንን ያረክሳታል፡፡ ኮነሬል አብይ ለስልጣን ሲል አገሩ የሚሸጥ ሰላቢ ነውና!!!

 

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍጢሙ ተደፍቶል፣ በአንድ በኩል የሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበትና በሌላ በኩል ደግሞ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ዶላር እጥረት፣ የእዳና የብድር ወለድ አገልግሎት የመክፈል አቅም መሞሸሽ፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት፣ የጦርነት ኢኮኖሚ አዙሪት በትግራይ ሁለት አመት ጦርነት ወደ አማራ ሰባት ወራት ጦርነት ቀለበት ውስጥ ሆኖ ሚሊዮን ወጣቶች ሕይወታቸውን አሳጣ እንዲሁም ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ-ልማት ውድመት አስከተለ፡፡  የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት፣ በ2021እኤአ የጂ20 አገሮችን የእዳ ኮመን ፍሬም ወርክ  የእዳና የወለድ ሽግሽግ እንዲደረግለት ቢጠይቅም በጦርነት ምክንያት ዘግይቶበት ነበር፡፡ መንግሥት በአይኤም ኤፍ ፕሮግራም መሠረት የብር ኖቱን በጥቁር ገበያ ዋጋ የማርከስ ጥያቄ ቀርቦለታል፣ የውጪ ባንኮች አገር ቤት እንዲገቡ እንዲፈቅድ ታዞል፣ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችን ፕራይቬታይዝ እንዲያደርግ መመሪያ ወርዶለታል፡፡ እነዚህን ትዕዛዛት የመሳሰሉትን ተፈጻሚ ካደረጉ ከዓለም ባንክና አይኤም ኤፍ ብድር ሊያገኙ እንደሚችሉ ቀጭን ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡

{1} የፓሪስ ክለብ የአበዳሪዎች ክበብ( Paris Club)፡-ኢትዮጵያ ከፓሪስ ክለብ አበዳሪ አገራቶች ጋር የሁለትዮሽ የብድር ስምምነት አድርጋለች፣ የእዳ ክፍያ እፎይታ ጊዜ ከ2025 እስከ 2026 እኤአ ድረስ እንዲራዘምላት ሆኖል፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር የብድር ስምምነት እስከ ማርች 31 ቀን 2024እኤአ ድረስ ብድር ካላገኘችና ካልፈፀመች ግን የፓሪስ ክለብ ስምምነት ውድቅ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ እዳና የብድር ወለድ ክፍያ ከ2023 እስከ 2024 እኤአ የእፎይታ ጊዜ በማግኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ እስከ ኖቨንበር አስር ቀን 2023እኤአ 1.5 (አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር የብድር እፎይታ ጊዜ አግኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከፓሪስ ክለብ አበዳሪ አገራቶች፣ ከ2025 እስከ 2026እኤአ የብድርና  የወለድ የእፎይታ ጊዜ አግኝታለች፡፡ ኢትዮጵያ ከፓሪስ ክለብ አበዳሪ አገራቶች የብድርና  የወለድ ክፍያ የምትጀምረው ከ2027 እስከ 2029እኤአ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ Ethiopia’s agreement with its bilateral creditors, other than China, to suspend debt payments until 2025 could be voided if the country does not secure an International Monetary Fund (IMF) loan by March 31, 2024, the Paris Club of developed creditor nations said. The debt service standstill for 2023 and 2024, which the central bank governor says will save the country $1.5 billion, applies to loans agreed before Nov. 10. It will see suspended payments repaid from 2027 to 2029 after a grace period from 2025 to 2026, the Paris Club said in a statement, noting that the deal was reached on Nov. 23…………………………………………….………(1)

ተጨማሪ ያንብቡ:  እጁ በንጹሀን ደም የተጨማለቀው አብይ አህመድና የአማራው የህልውና ተጋድሎ

 

 • የፓሪስክለብ የአበዳሪዎች ክበብ በ1956 እኤአ ተመሠረተ ተበዳሪ አገራቶች ብድራቸውን ለመክፈል ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የተቌቌመ ቡድን ነው፡  የፓሪስ ክለብ ቆሚ አባላቶች አውስትራሊያ፣ አውስትሪያ፣ ቤልጀም፣ ብራዚል፣ ካናዳ ፣ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፍራንስ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ እስራኤል፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ ኮሪያ፣ ኒዘርላንድ ኖርዌ፣ ራሽያ ፌዴሬሽን ፣ስፔን፣ ስዊድን፣ ሲዊዘርላንድ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ ናቸው፡፡ ከ2022 እኤአ ጀምሮ ሳውዝ አፍሪካ የወደፊት እጩ አባልነት ታጭታለች፡፡

 

 • የፓሪስክለብ የአበዳሪዎች ክበብ አባላት ተሳታፊዎች የይፋ ህጋዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ ወኪሎች የሆኑ አገሮች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ህጋዊ መብትና ጥየቄ ያላቸው አገራቶች አውስትራሊያ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ እስራኤል፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ ኮሪያ፣ሲውድን፣ ሳውዝ አፍሪካና ሲውዘርላንድ ናቸው፡፡ የፓሪስ ክለብ አባሎች ያልሆኑ የይፋ ህጋዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ ወኪሎች የሆኑ አገሮች ውስጥ ቻይና፣ ህንድ፣ ኩዌት፣ ፖላንድ፣ ሳውዲ አረቢያና ቱርክ ይገኙበታል፡፡

 

 • እዳውባለበት እንዲረጋ ፣የኢትዮጵያ ብድርና የወለድ  የእፎይታ ጊዜ ከ2023 እስከ 2024እኤአ ድረስ5 (አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ከኖቨንበር 10 ቀን 2023 እኤአ በፊት ለተደረጉ ብድሮችን ሁሉ የእፎይታ ጊዜው ያካትታል፡፡ የፓሪስ ክለብ ለኢትዮጵያ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ለሁለት አመታት እንዳትከፍል የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶታል፡፡ የፓሪስ ክለብ አበዳሪ አገሮች በእፎይታ ጊዜ በኃላ የቀረው የብድርና ወለድ ክፍያዎች ከ2027 እስከ 2029 እኤአ ባለው ጊዜ ውስጥ ክፍያቸው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ይህ የፓሪስ ክለብ ስምምነት የሚጸናው ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክና ከአይኤፍኤም ጋር የብድር ስምምነት አድርጋ ተጨማሪ ብድር እስክታገኝ ድረስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብድር ካላገኘች ግን የፓሪስ ክለብ ብድርና የወለድ እንዲሁም የእፎይታ ጊዜ ስምምነት ይሰረዛል፡፡

 

{2} ዩሮ ቦንድ ብድር፡-የብልጽግና መንግሥት በህዳር ወር 2007እኤአ ከግል አበዳሪዎች የተበደረውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ብድር በ6.625 በመቶ ወለድ መበደሩ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የዩሮ ቦንድ የወለድ ክፍያ 33 ሚሊዮን ዶላር እስከ 11 ዲሴንበር 2023 (ታህሥስ አንድ ቀን 2016ዓ/ም) ድረስ መክፈል  ቢጠበቅበትም ከወዲሁ እንደማይችል ገልፆል፡፡ አያይዞም የአንድ ቢሊዮን ዬሮ ቦንድ ብድር የመክፈያ ጊዜ ዲሴንበር 2024እኤአ እንዲራዘምና የወለዱ ምጣኔ 5.5 በመቶ ዝቅ እንዲል የብልፅግና መንግሥት ጠይቆል፡፡ በዚህም የተነሳ ከዓለም ባንክና ከአይኤፍ ኤም ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም፡፡ ስለዚህም የፓሪስ ክለብ የአበዳሪዎች ክበብ ጋር የተፈጸመው የብድርና ወለድ የእፎይታ ጊዜ ስምምነት ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ The debt standstill provided by all OCC members (bar one who will apply its own terms) will suspend debt service repayments due over 2023 and 2024. Suspended payments will be repaid after a two-year grace period, and over a three-year period from 2027 to 2029.

ተጨማሪ ያንብቡ:   ኢትዮጵያና የፖለቲካ ፓርቲዎቿ - ኤፍሬም ማዴቦ

The government announced the agreement last month, alongside stating its intention to restructure its single $1 billion international bond, maturing in December 2024. In August, it said China was suspending payments for debt maturing in the fiscal year to July 7. Investors in the 2024 bond, a group of whom had offered a maturity extension earlier this year, are watching to see if a Dec. 11 coupon payment, that research firm Tellimer puts at $33 million, will be made……………………………………….(2)

 

{3} የቻይና ብድር፡-የኢትዮጵያ የውጪ ብድር ከ28 እስከ 33 ቢሊዮን ዶላር ሲገመት ከዚህ ውስጥ የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ ያበደረው 14 (አስራ አራት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከ2006 አስከ 2022 እኤአ ድረስ የተከማቸና የተቆለለ ብድር ነው፡፡ የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ የብድርና ወለድ ክፍያ የማሸጋሸግ በመድረግ የብድር ክፍያ እስከ ጁላይ 7 ቀን 2024 እንዲራዘም አድርጎል፡፡

Ethiopia’s external debt totaled $28.2 billion at the end of March, according to government data. It includes a $1 billion international bond maturing in December 2024 . Between 2006 and 2022, Chinese lenders committed to more than $14 billion of loans to the landlocked country, according to Boston University.Oct 14, 2023

Ethiopian authorities said in August that China was allowing Ethiopia to suspend debt payments for the fiscal year running until July 7, 2024. ” …

 

{4} ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ (United Arab Emirates) ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ 3 (ሦስት) ቢሊዮን ዶላር በእርዳታና በኢንቨስትመንት መልክ ለመስጠት ቃል በመግባት ተግብራዋለች፡፡ ኢምሬትስ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስአንድ ቢሊዮን ዶላርለውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ እጥረትን ለማሞላት በኢትዮጵያ ባንክ ተቀማጪ አድርጋለች፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የነጻ ንግድ ለማሻሻልና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችን ሊብራላይ ለማድረግና የውትድርና ወጪን ለመቀነስ እንደተመረጠ ሰሞን ቃል ገብቶ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ድርድር ከወያኔ ጋር? የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና መጪው ጊዜ! (ለውይይት መነሻ) - ባይሳ ዋቅ-ወያ

United Arab Emirates pledges $3 billion in aid and investments in Ethiopia.

The UAE will deposit $1 billion in Ethiopia’s central bank to ease its foreign currency shortage.

Prime Minister Abiy Ahmed is speeding up market reforms such as liberalising state companies and reducing the role of the military in the economy.

 

 

ምንጭ

(1)Ethiopia debt service pause contingent on IMF deal by end-March -Paris Club/By Rachel Savage/December 1, 2023/ JOHANNESBURG, Dec 1 (Reuters) –

 

(2) THE PARIS CLUB WELCOMES THE AGREEMENT TO PROVIDE ETHIOPIA WITH A DEBT STANDSTILL (November 30, 2023)

 

3 Comments

 1. አቶ ሚሊዮን ዘአማኑኤል፦ በሙያዎ ህዝብን በማንቃት ደረጃ የሚሰቱትን አገግሎት አደንቃለሁ፡፡ አብይ አህመድ የበጋ ንፋስ ያመጣው አቧራ ነው፡፤ ወስላታ ነው፡፤ ጥጃ ነው፡፤ “ስልጣንና ንግስና” ነው የሚፈልገው፡፤ ይህንን ከሚያጣ ሀያና ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ በመንጋው የኦሮሙማ ሰራዊት፣ በድሮን በታንክና በመድፍ ቢያልቅ ይመርጣል፡፡ ስለዚህ ምርጫችን መሆን ያለበት ከፋኖ ጎን ቆመን ኦሮሙማን ጠራርጎ ለደፍርድ ማቅረብ ነው፡፡ ከዚያም ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን ያቀፈና ያካተተ “በህዝብ ለሀዝብ ከህዝብ” በሚል መንፈስና አካሄድ ብቻ በሀቅና በእውነት ልይ የተመሰረተ በህዝብ የተመረጠ መንግስትና ህገ መንግስት ነው፡፡
  ከዚያ በፊት ግን በኦሮሙማው መንግስት የሚሸጥ ማንኛውም የአገር ሀብት የህዝቡንና የህዝቡን ትክክለኛ ወኪሎች ይሁንታ ያላገኘ የዝርፊያ ሽያጭ ስለሆነ ገዥ አገሮች በተለይም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስና ቱርክ እንዲያውቁት ማድረግ ይህንንኑም ለአለም ማሳወቅ የሚያስፈልገን ይመስለኛል፡፡
  እየር መንገዱን፣ ግድቡን፣ ቴሌኮሙኒኬሽንን የመሳሰሉትንስኳር ፋብሪካወችን ባንኮችን ..። ወዘተ የኢትዮጵያዊያን ሀብቶች በሙሉ ያለህዝቡ ይሁንታ መሸጥ ማለት “”ሌባ ሰርቆ መርካቶ ወ ስዶ እንደሚሰጠው እቃ”” ነው ማለት ነው፡፡

 2. ወዳጄ ተይዟል ሳይሆን ታንቋል ነው የሚባለው አማካሪዎቹ ዳንኤል ክብሪት ባለስልጣኖቹ ሽመልስ እብዱሳ፤አዳነች አቤቤ፤አረጋ ከበደ፤አገኘሁ ተሻገር፤ አዲሱ ቂጤሳ ጋዜጠኞቹና ተንታኞቹ ስዩም ተሾመ፤ጫላ ምናምን፤አቤ ቶኪቻው፤የጦር ሰዎች ብሎ የሸማቸው ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ፤አበባው ታደሰ፤መንፈሳዊ አማካሪዎቹ ቀጣፊው ዮናታን አክሊሉ፤እስራኤል ዳንሳ፤እዩ ጩፋ ታዲያ አብይ ከመሃይምነቱ ጋር ተዳብሎ እውር ድምብሩ ቢጠፋው ይፈረድበታል? ፍርድ እንደራስ ነው፡፡ ፋኖ አገር ሳይበተን ፈጥነህ ታሪካዊ ሃላፊነትህን ተወጣ፡፡

 3. “የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ …”

  Well it’s Ethiopia, our beloved country which is tied up with this debt. So the title of this article is not 100% correct.
  At the end of the day, ethiopians will have to pay this debt, not PP.
  Of course bad governance of the PP government has a big contribution. The internal conflicts and the security issues which paralized the economy are due to PP’s bad governance and hidden agenda.
  That a huge amount of money is printed by the Government for the “Chaka project “.
  Looting, corruption and fraud practices by authorities etc.
  For the above mentioned is the PP government responsible.

  But the war in the north which was ignited by TPLF has destroyed the economy too.
  Additional global effects and COVID have contribution too.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share