የውሸት ሽምግልና አቀንቃኞች ሆይ! ሳይንስ እንደሚያስረዳው ውሾች እንኳ የከዷቸውንና ያጭበረበሯቸውን ሰዎች ዳግም አያምኑም!

ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታቸው ተማታውቃቸው አይናቸውን በሚጥሚጣ ከታጠቡ ከሀዲ፣ ውሽታም፣ አጪበርባሪና ቁማርተኛ ጭራቅ ገዥዎች ጋር ዛሬም እንደ ትናንቱ   “ሽምግልና” የሚሉ ከንቱ ሆድ አደሮች ማየት ያለመታከት “እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ!” የሚያሰኝ ነው፡፡

የውሸት ሽምግልና አቀንቃኝ ሆይ! ከሀዲዎችን አንጠርጥረው ተሚለዩትና ዳግም ማመን ቀርቶ ይቅርም ተማይሉት አንዳንድ የውሻ ዝርያዎች እያነስክ ነው፡፡ አንድ 260 ውሾችን ያካተተ ምርምር እንደሚያስረዳው አንዳንድ የውሻ ዝርያዎች ያታለሏቸውን ሰዎች በደንብ እንደሚያውቁ፣ ዳግም ለማመን ብቻ ሳይሆን ይቅር ለማለትም እንደሚቸገሩ አረጋግጧል፡፡ ከጽሑፉ ግርጌ ያሉት ዋቢዎችን ይመልከቱ፡፡ [1-3]

የትግሬ ነፃ አውጪ፣ ይህ አድግ፣ ብአዴን፣ ኦፒድኦ፣ አዴፓ፣ ኦዴፓ፣ ወነግ፣ ብልጥግና  ወዘተረፍ እያሉ በሶስትም በአስርም ስም የሚመጡ በእርኩስ መንፈስ የተለከፉ ከሀዲዎችና ከሰይጣን የከፉ ሞላጫዎች የኤፍሬም ይስሃቅ አይነቱን ይሁዳዊ ሽምግልናን የወንበር ማስጠበቂያና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርገው ሲጠቀሙበት እንደኖሩና አሁንም በዚሁ የማጭበርበር ቁማር እንደቀጠሉ አገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬም ስለሽምግልና በማውራት ላይ ያለነው የከዳውንና ያጭበረበረውን ሞላጫ ማመን ቀርቶ ይቀር ተማይለው ውሻ አንሰን ነው?

በታሪካዊትና መንፈሳዊት ኢትዮጵያ ሽምግልና ከእውነተኛ ችሎት እጅግ የበለጠ ርትኡ ፍርድ የመስጥትና ዘላዊ ሰላምን የማስፈን መለኮታዊ ሀይል ነበረው፡፡ የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች እየጠራረገ የሰይጣንን የቅጥፈት፣ የሌብነት፣ የአውሬነትና የጭራቅነት መንፈስ ሲሰራና ሲተክል የኖረው ይሁዳው ይህ አድግ ከመጣ ጀምሮ ሽምግልና ተበዳይን ከበዳይ እግር የሚያስደፋና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ እንደሆነ እንኳን ነፍስ ያወቀ ህጻንም የሚረዳው ነው፡፡ የወሮብሎች ሽምግልና ከርሳም ካህናትንና ሼህችንም በሆዳቸው እየገዛ የመልኮትን ማምለኪያ ስፍራዎች እንደተዳፈረ የታወቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በጥላሁን ገሠሠ ሥም እየነገደ ያለው ሰው ምነው ተው ባይ አጣ?

ይህ አድግ የተባለው የትግሬ ነፃ አውጪ እርጉም የእጅ ሥራ እነ ኤፍሬም ይስሀቅን የይሁዳዊ ሽምግልና መሪ ተዋናይ አድርጎ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ እደተጠቀመበት ሁሉ  በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈው ከአስራ አምስት ሚሊዮን ሕህዝብ በላይ ስደተኛ ያደረገው ከሁሉም የከፋው የጭራቅ ቡድን  ስለሽምግልና ምንም የማያውቁትን ሆደ አደር ምሁር ተብዮዎች፣ ከርሳም የቤተክርትያንና የመስጊድ ሰዎችን የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአለፈው መማር ያቃተው ልብ የለሽም በማያባራ ይሁዳዊ ሽምግልና እየተጠለፈ ታግሎ ማስወገድ ያለበትን መከራ እያራዘመው ነው፡፡

እምነት ቀርቶ የአውሬ ያህል እንኳ የደመነፍስ ባህሪ ካልፈጠረባቸው እነዚህ አረመኔዎች በሽምግልና በኩል፣ እርቅን፣ ፍትህንና ሰላምን መጠበቅ ከሳጥናኤል በረከትን ተጭራቅ ርህራሄን እየጠበቁ ሲንዘላዘሉ እንደመኖር ነው፡፡

ሕዝብ ሆይ! ጭራቆች ለወንበር መጠበቂያና ለሕዝብ መጨፍጨፊያ ተሚጠቀሙበት ይሁዳዊ የ ሽምግልና ፍትህና ሰላምን ጠብቀህ መከራህን አታራዝመው፡፡ መፍትሔው መጀመርያውንም ጭራቅን ደጋግፎ ተወንበር አለማውጣት፤ ከወጣም ዥልጦ ማውረድ ነው፡፡ ዛሬም እንደትናንቱ ከጭራቅ ጋር ሽምግልና መቀመጥ ከሀዲና ሞላጫን አንጠርጥረው አውቀው ዳግም ማመን ቀርቶ ይቅር ለማለትም ተሚቸግሩት ውሾች ማነስ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ዋቢ፡- (All last accessed in December, 2023)

 1. Big Think, Dogs Know When People Are Lying  Dogs know when people are lying – Big Think
 2. Life Science, Dogs Know When Humans Are Lying to Them Dogs know when humans are lying to them | Live Science
 3. Psychology Today,Can Dogs Know When We Are Lying to Them? Can Dogs Tell When We’re Lying to Them? | Psychology Today
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ቡልቻ ከአንድነት ፓርቲና አባላት አናት ላይ መቼ ይወርዱ ይሆን ?

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

 

2 Comments

 1. የትክክለኛ እርቅና ሰላምን ትርጉም የበለጠ ሊረዱ የሚችሉ በሰላም መጥፋት በህይወታቸው በዘመዶቻቸው የቀመሱት ይሆናሉ:: ከአጼው እስከ ወያኔና የወያኔው የጡት ልጅ አብይ አህመድ ድረስ ህዝባችን ከመከራ ወደመከራ ሲሸጋገር መኖሩን በሚገባ የማውቅና ያለፍኩበት ነኝ:: ንጉሱ እድሜያቸው ገፍቶ በራሳቸው ወታደሮች ተዋርደው ሳይሰናበቱ በፊት በሽምግልና መልክ ከራሳቸው ወንድም ልኡል ራስ እምሩ ጀምሮ በቅርቡም የራስ አስራት ካሳ ልጅ አባታቸው በጎ ምክር ሲያቀርቡ ንጉሱ ያለመቀበላቸው መስከረዋል:: ደርጉ የፕሮፌሰር መስፍንን የባላደራ መንግስት ጥያቀ የሃገር ጉዳይ የባልና ሚስት ጉዳይ አይደለም ብሎ በማናናቅ በትእቢቱ ቀጥሎ ምስኪኑን ሰራዊት ሜዳ ላይ ለማኝ በማድረግ ራሱ ግን ወደከበርቴዎቹ መነደር ዚምባቡዌ ፈረጠጠጠ ዛሬ ድረስ ይኖራል:: ወያኔ የግዮኑን እርቅና ሰላም ጉባኤ ተሳታፊዎች ፊታውራሪ መኮንን ዶሪና መሰሎቹን ከምክር ቤት በማባረር በሃሰት በቀይ ሽብር አስሮ ከአምስት አምታት በሁዋላ ነሳ ብሎ ፈታ:: ብልጽግና ንጉስ ነኝ ባይ አብይ እርቅ እየሰበከ የከፋ ጥላቻውን መደበቂያ የደረገው የኦሮሙማ አጀንዳ ይፋ እየታየ ነው:: በዚህ ሁሉ ውስጥ በሃቅ የሃገራችን ጉዳይ ግድ ብሎዋቸው እርቅና ሰላም የሞከሩ ሲኖሩ ገዥዎቹ የህዝብ ቁጣ ለማብረድ የተጠቀሙባቸውም ይገኛሉ:: እዚህ የተጠቀሱት ፕሮፍሴር ኤፍሬም ይስሃቅ ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ በእእርቅ ያስፈቱዋቸው የቅንጅቱ መሪዎች ይገኛሉ እነዚህን ሰዎች መሪውን ፕሮፌሰር ኤፍሬምን መንቀፍ ትክክል አይደለም:: በዚህ ወቅት እርቅ ምክክር የሚያስፈልገው በጋራና በቀኝ በሚልዮኖች በዘር ፖለቲካው ጡዘት ለማያልቅ ጦርነት ስለተዘጋጁና ስለሚታይም ነው:: የሃገራዊ እርቅና ሰላሙ ጉዳይ ከአጼ ሃይለስላሴ ከመመንግስቱ ሃይለማርያም ከመለስ ዜናአኢ ከኣአብይ ኤህመደ የስልጣን ጥማትና ፍላጎት በላይ የህዝባችን ሲወርድ ሲዋረድ የቆየ የጥላቻ የመናናቅ እእርም የሚወገድበት ሃገራዊ ምክክር መሆን ይገባውላና በዚህ በቅን መንገድ የሚተጉትን ጦርነቱ ይቀጥል ዘንድ ሚልዮኖች ይፈናቀሉ መቶሺሺዎች በለጋነታቸ ያልቁ ዘንድ ከሚፈልግ ክፉ መንፈስ በተቀር ማንም በጎ ህሊና ያለው አይፈልገውም::ለመለስ ዜናዉ ገጣሚው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በግልጽ ደብዳቤ እንዳሉት ዛሬም ለእርቅና ሰላም ድርድር ጊዜው አልረፈደውም:: በፖለቲከኞች ስህተት ትናት በደርጉ በወያኔው በቅርቡም በእህት ፖለቲካ ድርጅቶች ወያኔና ኦህዲድ የረገፉት የአካል ጉዳተኛ ወገኖቻችን ክቡር ህይወት ግድ ብሎን ለትክክለኛ እርቅና ሰላም ሃገራዊ ምክክር እንትጋ ::
  ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

  • ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው፣
   ድርድር ጥሩ ነው። ከሰው ልጅ ጋር ከሆነ። ይህ የጅብ መንጋ ከስርዓቱ ከተወገደ።
   በመጀመሪያ ከዚህ አረመኔ መንግሥት (ታዬ ደንደአም እንዳለው) መደረራደር “ጥሩ መንግሥት ነህ፣ ጥያቄያችንን ከመለስክ፣ ዙፋንህን አንነካም፣ እንደቀድሞው መሰሪ ሥራህን መቀጠል ትችላለህ” ማለት ነው።

   ፓስተር፣ አህያ ከጅብ ጋር ይደራደር እያሉ ነው እኮ። ድርድር የሞራል ብቃት ካለው ሰው ነው። የመፅሀፍ ቅዱሱን ትምህርት ባልተገባበት አይሰንጉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share