በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል የውይይት መድረክ እዬተዘጋጀ የሚቀርብ አስተያዬት

ፋኖስ Fanos

ፋኖስ ቁጥር 3 ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓም(06-11-2023)

ፋኖስ ብርሃን ለግሶ ጨለማን ገፎ የሚያሳይ፣ድቅድቅ ባለጨለማና በተሰወረ ቦታ ላይ ያላዬነውን ፍንትው አድርጎ በማሳዬት ከአደጋ የሚያወጣ ጠቃሚ መሳሪያ ነው።እኛም የሃሳብ ጥራትና ግንዛቤ እንዲኖረን ፋኖስን ምሳሌ አድርገን ለውይይት መድረካችን ልሳን ስያሜ አድርገነዋል።የውይይት መድረካችን ዓላማና መነሻ ያልታዩና የተዘነጉ ጉዳዮችን ፈልቅቀን በማውጣት የጋራ ግንዛቤና እውቀት እንዲኖረን ይረዳል ከሚል ቀና አስተሳሰብ በመነሳት ነው።

ባለፉት ሁለት ዝግጅቶቻችን የተለያዩ እርእሶችን አንስተን ያገኘናቸውንና የደረስንባቸውን የጋራ ግንዛቤዎች ለቀረው ወገናችን ያካፈልን ሲሆን በዛሬውም ቅንብራችን ጠቃሚና መነሳት አለባቸው ባልናቸው እርእሶች ላይ የደረስንበትን ግንዛቤ ለማካፈል እንወዳለን።

በኖቬምበር 5,ቀን2023 ባደረግነው የዙም ስብሰባችን በሚከተሉት እርእሶች ላይ ተወያይተን የጋራ ግንዛቤ አግኝተናል።

1 የአንድ አገር ልዑላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም ስንል ምን ማለታችን ነው?በነማንና እንዴት ይደፈራል?እንዴትስ ይከበራል?

2 የወደፊቱ የአገራችን የፖለቲካ ህይወትና ሥርዓት ምን መሆን አለበት? በማንና እንዴትስ ሊረጋገጥ ይችላል?

3 አንድ አገር ብቻውን ሊቆም ይችላል ወይ?የከሌላው አገር ጋር ግንኙነት ያስፈልገዋል አያስፈልገውም?ግንኙነቱስ ምን መምሰል አለበት?

4 አሁን የሚካሄደው ትግል ዓላማው ምንድን ነው?የሚታገላቸው ሃይሎች እንማን ናቸው?ወያኔና ኦነግ መራሹን ስርዓት ማሸነፉ ብቻውን የሕዝቡን ጥያቄ ይመልሳል ወይ?ብሔራዊ ነጻነትንስ ያጎናጽፋል ወይ?

ከዚህ በላይ ለቀረቡት የመነሻ ጥያቄዎች በውይይታችን የሚከተሉት ማብራሪያዎችና የጋራ ግንዛቤዎች ተደርሶባቸዋል።

ልዑላዊነት ማለት በአጭሩ የአገር ዳርድንበር በውጭ ወራሪ ሳይደፈርና በውስጥ አስተዳደር ማለትም በፖለቲካና በኤኮኖሚ እንዲሁም በባሕልና በማህበራዊ ኑሮ ላይ ሌሎች ጣልቃ ሳይገቡበት እራስን ችሎ የመንቀሳቀስ ነጻነት ባለቤት መሆን ማለት ነው።ይህንን ነጻነት የሚገፉ ከውጭና ከውስጥ በሚነሱ ሃይሎች፣በነጠላ ወይም በጥምረት ሊከሰት የሚችል አደጋ ሊኖር ይችላል።ይህንንም በእኛና በሌሎች አገሮች ሲከሰት አይተናል እያዬንም ነው።የአገራችንን ዳር ድንበር ጥሶ የመጣ የውጭ ጠላት በታሪካችን በተደጋጋሚ ታይቷል።የጣሊያኖች፣የሶማሌ አሁንም ድረስ ያለው የደቡብና ሰሜን የሱዳኖች ድንበር ጥሶ የመውረር ድፍረት የውጭና የውስጥ ሃይሎች ጥምረት ውጤት መሆኑ አይካድም። የውጭ ጠላት ውስጣዊ ችግር በሚከሰትበትና በሚዳከምበት ወቅት ጊዜ ጠብቆ፣ወይም በውስጥ ያለን ጥቃቅን ችግር መጠቀሚያ አድርጎ ከውስጡ ተባባሪ ሃይል ጋር በጥምረት የሚፈጽመው ሴራ ለመሆኑ በወያኔና በኦነግ መራሹ ስርዓት ያዬነውና አሁንም ድረስ የገባንበት ችግር በቂ ማስረጃ ነው።ሌላው የልዑላዊነት መገለጫው ደግሞ አንድ አገር በራሱ ሕዝብ ፈቃድና ፍላጎት የፖለቲካ መንገዱን በነጻነት ቀይሶ ፣የመተግበር፣ብሔራዊ ኤኮኖሚውን ካለማንም ተጽእኖና ትዕዛዝ እንዲገነባ የሚያበቃውን ነጻነቱን ማረጋገጥ ሲችል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በአስቸኳይ ይቁሙ! - ኢሰመጉ

ላለፉት ዘመናት አገራችን በራሷ ሕዝብ ፍላጎትና ምርጫ እንዲሁም ውሳኔ የራሷን የፖለቲካ ጉዞና የኤኮኖሚ ግንባታ እንዳታካሂድ የውጭ ሃይሎች ከውስጥ ሃይሎች ጋር በመተባበር ደንቃራ ሆነው ሕዝቡ ለተሻለ ኑሮ ሳይበቃ ፣የአገር ሃብትና የተፈጥሮ ንብረት እዬተመዘበረ ለውጭ ሃይሎች መጠቀሚያ ሆኖ በድህነት አሮንቃ ለመኖር ያበቃው የራስን ዕጣ ፈንታ የመወሰን መብት ባለመከበሩ የተነሳ መሆኑንን በውይይታችን ወቅት የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰንበታል።የውጭ ሃይሎች በሚቆጣጠሩት የገንዘብ ተቋማት መዳፍ ስር መሆኑ አገራችንን በራሷ እግር ለመቆም እንዳትችል አድርጓታል።እነሱ የሚያወጡትን አስገዳጅ መመሪያ የሚተገብር እንጂ በራሱ የሚተማመን መንግሥትና ስርዓት እንዳይኖር በማድረግም ፖለቲካውም ኤኮኖሚውም ጥገኛ እንዲሆን ሆኗል።ያንንም የሚያስፈጽሙት የራሳችን ያገሪቱ ዜጎች ናቸው።ለብሔራዊ የፖለቲካና የኤኮኖሚ እንዲሁም የባሕልና የማህበራዊ ጉዳዮች ውሳኔ ነጻነት የሚከበረው አገር ወዳድና አርቆ አሳቢ የሆኑ ብቃትና እውቀት ያላቸው ዜጎች የአመራሩን ቦታ ሲረከቡ ብቻ ነው።የወያኔና የኦነግ መራሹ ስርዓቶች አሁን ላለንበት ውድቀት የዳረጉን መሆናቸውና ከሥልጣን ተወግደው ሕዝባዊ ስርዓት ካልሰፈነ በቀር ሁኔታው ከድጡ ወደማጡ እንደሚሆን የጋራ መግባባት ላይ ደርሰናል።

ግንኙነትን በተመለከተ አንድ አገር ብቻውን ለመቆም እንደማይችልና የግዴታ ከሌላው አገር ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚገባ ውይይታችን አምኖበታል።የሚኖረው ግንኙነት ግን በጌታና በባሪያ መልክ የሆነ ግንኙነት ሳይሆን በጋራ ጥቅምና በመከባበር ላይ የተመሠረተ መሆን እንደሚገባው ፣የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሰብአዊና ዓለምአቀፋዊ ግዴታ እንደሆነና አገራት ያላቸውን በመስጠት የሌላቸውን በመቀበል ተደጋግፈው ሊኖሩ የሚችሉበትን ደንብና ስርዓት መከተል እንዳለባቸውና የእኛም አገር ከዚሁ የጋራ ሰንሰለት ውስጥ መግባትዋ የሚጠቅማት እንጂ የሚጎዳት እንዳልሆነ ታምኖበታል።የውጭ ግንኙነት ከማንም ተጽእኖና ቁጥጥር ነጻ መሆን እንደሚገባው ውይይታችን አጽንኦት ሰጥቶበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማኅበረ ቅዱሳን የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

አሁን የሚካሄደውን ሕዝባዊ ትግል በተለይም የአማራ ፋኖን ትግል በተመለከተ ትግሉ በጸረ ኢትዮጵያ በሆኑት የውያኔና የኦነግ መራሹ ሃይሎች በአማራው ላይ ላለፉት 33 ዓመታት ሲደርሱበት የኖረውንና በተለይም ላለፉት 5 ዓመታት በኦነግ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ እዬተፈጸመበት ያለው ግፍና በደል አንገፍግፎት እራሱን ከመጥፋት ለማዳንና ብሎም የአገሩን አንድነት ለማስከበር የሚያደርገው ብሔራዊና ሕዝባዊ ብሎም ለዴሞክራሲመስፈን ይዘት ያለው ትግል እንደሆነና ይህንን ትግል መደገፍም የሁሉም አገር ወዳድ ግዴታ እንደሆነ ታምኖበታል።ሆኖም ግን ትግሉ ወያኔንና ኦነግን በማሸነፍ ብቻ የሕዝቡንና ያገራችንን ችግር ሙሉ ለሙሉ ያሶግዳል ብለን አናምንም።ለዘላቂ ሰላምና የአገራችን አንድነት ብሎም ለሕዝቡ ኑሮ መሻሻል የግድ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብር አገር ወዳድ ስርዓት መስፈን ይኖርበታል።ያንን ሥርዓት ለመመስረት ደግሞ በእውቀት የታነጸ፣ብሔራዊ ክብርን የሚያስጠብቅ የፖለቲካ ፍልስፍናን ተመርኩዞ ፍኖተ ካርታ የነደፈ የአገር ወዳዶች መሰባሰብና መደራጀት ወሳኝ ነው።ስለሆነም ከፋኖ ትግል የድል ማግስት አገራችንን ለዘላቂው አስተማማኝ የፖለቲካ፣የኤኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል በሕዝቡ ውሳኔና ምርጫ ስልጣኑን የሚረከብ አካል መፍጠሩ ከአሁኑ ጎን ለጎን ሊታሰብበት ይገባል ብለን እናምናለን።ይህ ቅድመ ዝግጅት በትግሉ ጀርባ በውጭ ሃይሎች በሚታዘዙና በሚመሩ ግለሰቦችና ቡድኖች እንዳይቀለበስ ለመከላከል ይረዳል።ይህ ካልሆነ ግን ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በተደጋጋሚ የተከሰተው ክፍተት ለታጠቀና ለአምባገነኖች መነሳት ዕድል እንደሰጠው ሁሉ አሁንም ተመሳሳይ ውድቀት ውስጥ ላለመግባት መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆኑን ሌላው ወገናችን እንዲረዳው ያስፈልጋል እንላለን።ለዳግመኛ ተቃውሞና ትግል ላለመነሳት ፣ጊዜና ጉልበታችንን፣እውቀትና ገንዘባችንን በልማትና አገር ግንባታ ላይ ለማዋል የግድ የምንፈልገው ሥርዓት እንዲመሠረት ሕዝቡ የመወሰን መብት ሊኖረው ይገባል ከሚለው መደምደሚያ ላይ ደርሰናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን በባሕር ዳር የጣና አፍሪካ ከፍተኛ የደኅንነት ፎረም ተሳታዎች ‹‹የእንኳን ደህና መጣችሁ›› መልዕክት አስተላልፈዋል

 

1 Comment

  1. ጎበዝ መልእክቱ መልካም ሁኖ በዚህ አጋጣሚ ብሄራው ምልክቶቻችን ብዬ የማምንባቸውን ከዚህ ቀጥሎ እጽፋለሁ እናንተም የጎደለውን ሙሉበት አቶ ታድዮስ ታንቱ፤መስከረም አበራ፤ጎበዜ ሲሳይ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረ ገጽ አዘጋጅ)፤ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ፤አቶ ገ/መድህን አርአያ፤ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ(ወልቃይትና ጠገዴ አስተዳዳሪ)፤ እስክንድር ነጋ የፊት መስመር ታጋዮች ናቸው ብዬ እገምታለሁ በኔ ግምት ሆኖም እኔ ውስንነት ስላለብኝ ያልደረስኩበትን ዜጋ በማሟላት ይሁንታውን ወይ ነቀፌታውን ቢያስቀምጥልኝ ወይም በጎደለው ቢሞላበት ።
    በባንዳዎች ተርታ ግምባር ቀደም ብርሃኑ ነጋ፤አገኘሁ ተሻገር፤ስዩም ተሾመ፤ደመቀ መኮንን፤አረጋ ከበደ፤ይልቃል ከፍያለው፤በለጠ ሞላ፤ጣሂር ኢብራሂም፤…ልደቱ አያሌው….. እዚህ ላይ ትግሬዎችን ከግምት አላስገባሁም እነሱም ኢትዮጵያዊ ነን አላሉም እኛም ማስገደድ አንችልም።የሚደነቀው/የሚመሰገነው የህዝብ ይሉኝታን ካላገኘ ባንዳ እየነገሰ ለሃገር የደከመ ሞራሉ እየወደቀ ይወርዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share