አክትሟል
””””””””””””””
ዙሪያው ገደል ሆኖ
መራቅና መሸሽ
ገለል ዞር ማለት
በጭራሽ አይቻል::
ከእንግዲህ፣በዚህ ሀገር
እንደ ሰው ተከብሮ
እንደ ዜጋ መኖር
አብቅቷል፣አክትሟል:
የሚለውን ብሂል
ላያስችል አይሰጥም!
ይሄ ሕዝብ ሽሮታል
ከሚችለው በላይ
ውርደት፣ውድቀት፣ስቃይ
የቁም ሞት፣መቃብር
ግፍን ተሸክሟል::
~***•°•***~
በቁም መቃብር
ውስጥ ለመኖራችን
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ጥቅምት ፳፬/፳፻፲፮ ዓ.ም
November 4/2023
ቅዳሜ)1:24(ሚኪ.ላ/አ.አ
©ያመጌዕ
አመሰግናለው
ያሬድ መኩሪያ
ከ አ.አ/ኢትዮጵያ