ቅጥረኛ የአብይ አህመድ ጄነራሎች ለሚያፈሱት የአማራና የሌሎች ኢትዮጵያውያን ደም የክፍያቸው መጠን ጨምሯል – አንዳርጋቸው ጽጌ

ይህ መረጃ ከፌስ ቡኬ ላይ መውረዱን ለጠቆማችሁኝ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለምን እንደሆነ እያጣራሁ ነው።

በአማራ ክልል በብጄነራል ዘውዱ ስጥአርጌ የ801 ኮር ዋና አዝዥ ትእዛዝ በአንከር ሚድያ በድረሰው በምታዩት ድብድቤ መሰረት የአማራ ባንክ ምንም አይነት የገንዘብ እንቅስቃሴ በደላንታና ሳይንት አጅባራ ወርዳዎች ቅርንጫፍ ባንኮች እንዲሁም በሌሎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ በሚታይባቸው በደብዳቤው ባልተጠቀሱ የአማራ ባንኮች ጭምር እንዳይደረግ ሃሳቡን ያቀረበው፣ በረጅም የጸረ አማራና የባንዳነት ታሪኩ የሚታወቀው የአሁኑ የአማራ ባንክ የጸጥታ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ተኮላ አይፎኩር መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል።

ይህ ግለሰብ የፌደራል ፖሊሱ ዋና አዝዥ የኮሚሽነር ደመላሽ ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን አዲስ አበባ ላይ ተቀምጦ የአማራ የደላንታና የሳይንት አጅባር ባንኮች ለፋኖ የሚሆን ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው ባንኮች ናቸው የሚለውን መረጃ፣ ቅንጡ መኪና በመስጠት የግል ተላላኪው ላደረገው ኮሚሽነር ደመላሽ በመስጠት ባንኮቹ አጋልግሎት እንዳይሰጡ ማስደረግ ችሏል።

ተኮላ አይፎክሩ ከዚህ ቀደም በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርምመራ ሃላፊ በነበረበት ወቅት በርካታ ትልልቅ ወንጀሎች መርማሪ ሆኖ አናዳቸውም ውጤት እንዳይገኝባቸው ከመንግስት ጋር አሻጥር በመስራት ይታወቃል። የኤንጂነር ስመኝ እና የአስማነው ጽጌ ግድያዎችን ምርመራ የመርራውና ውጤት አላባ ሆነው እንዲቀሩ ያደርገ የስርአቱ ሎሌ ነው።

ይህ መረጃ ከፌስ ቡኬ መውረዱን ለጠቆማችሁኝ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እንዴት እንደወረደ ለማጣራት እየሞከርኩ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቡ የፌደራል ፖሊስ የሰው ሃይል መምሪያ ሃላፊ በነበረበት ወቅት ክ41 እጩ ረዳት ኮሚሽነሮች ሹመት ውስጥ 34ቱ የኦሮሞ ተወላጆች እንዲሆኑ ያደረገ የአማራና የደቡብ የፖለኢስ ከፍተኛ መኮንኖችን ያለእድሜያቸው ጡረታ እንዲወጡ በማድረግ የኦሮሞ ተረኞችን በወዶ ገባነት ራሱን በፍርፋሪ እየሸጠ ሲያገለግል የቆየ መህኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የባሕታዊው ማስታወሻ (ክፍል አንድ)- በገ/ ክርስቶስ ዓባይ

እንዲህ አይነቱን ወገኑን የሚከዳ ባንዳ የሚኖርበት ማህበረሰብ እንዲያውቀውን አንቅሮ እንዲተፋው መደረጉ ለሌሎች ባንዳዎች ትምህርት ሰጪ ስለሚሆን በስፋት ምስሉ እና ድርጊቱ እንዲሰራጫ መረጃውን የላኩል ምንጮቻችን በአማራ ፋኖ ትግል ስም ጠይቀውናል።

ድል ለአማራ ህዝባዊ ፋኖ

ከጥቂት ሰአታት በፊት ባሰራጨሁት ጽሁፍ በጄነራል ሃሰን ምትክ የኮሚሽነር ተኮላን ምስል በስህተት ተጠቅሚያለሁ። ምስሉን ያነሳሁት ለዚህ ነው ። ይቅርታ እጠይቃለሁ
የጄነራሎቹን የስም ዝርዝር እና የተሰጣቸውን የመሬት ስፋት ሙሉ ሰነዱን በሚቀጥለው የቴሌምግራም ገጼ የፒዲኤፍ ቅጂ ማግኘት ትችላላችሁ። የተሳሳተውን የቴሊግራም ሊንክንም አስተካክያለሁ። ለጥቆማቸሁ አመሰግናለሁ። ከተመቻችሁ ሙሉ ዝርዝሩን ከዚህ በታች ማንበብ ትችላላችሁ። https://t.me/+UNLX8ZQKVJw0Y2Fk
 
 

3 Comments

 1. አቶ አንዳርጋቸው፦
  ዱሮምኮ ነፍስህን ለአገርህና ለህዝብህ የሰጠh የተግባር ጀግና ነበርክ፡፡ በመሀል “”የእነብርሀኑ ነጋ ንክኪ”” እና “”የአብይ አህመድ የርክሰት ጠበል”‘ ይመስላል ከአማራና ከኦሮሞ የዘር ምርጫ ቅርጫት ውስጥ ሳያስፈልግህ ገብተህ አማራን አስቀይመሀል፡፡
  ይህ ያጋጥማል፡፡ በትግል አለም ውስጥ ያለም ነው፡፤ ማንነትህን ህዝቡ ወደፊት እያየና አየተገነዘበ ለህዝባዊ ትግሉ ፍሬማነት አንዱ አስተማማኝ አለኝታው መሆንህን ያረጋግጣልና በርታ!!!
  እናደንቅሀለን፡፡እንደችሎታህ ከንተ ብዙም እንጠብቃለን፡፡

 2. አቶ አንዳርጋቸው በወጣትነት እድሜያቸው አባል የነበሩበት ህቡዕ የፖለቲካ ድርጅት ወታደራዊውን መንግሰት የጎዳ መሰሎት በወቅቱ “መለዮ ለባሸ” ይባል የነበረውን የሃገሪቱን ጦር ማጥላላት የጀመረው እንዲህ ነበር፡፡ ምናልባትም የኢትዮጵያ ጦር በግልጽ መሰደብ የጀመረው በዚህ ጊዚይ ይመስለኛል፡፡
  ጥላዬ ጨዋቃ (በኋላ ላይ በሰም ማጥፋት ጥላዬ “ጨምላቃ” ተብሏል) የሚባል የምድር ጦር ኦርኬስትራ ዘፋኝ ጦሩን ለማሞገሰ (በወቅቱ ሃገሪቱ በአራቱም አቅጣጫ እና በመሃል ተወጥራ ነበር) ዘፈን ያወጣል፡፡ የዘፈኑ ግጥም አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ በጊዜው ወታደር እንደ ባርኔጣ የሚያደርገው “ብረት ቆብ” ይባላል፡፡ ግጥሙም ይህ ነው፡፡
  የብረት ቆቡን ደፍቶ ባናቱ፡
  ወቴ ደስ ሲል ክነእንግቱ፡፡ ይላል ግጥሙ፡፡ ለስም ማጥፋት ሲቀየር እንዲህ ሆነ (ለቃላቶቹ ይቅርታ!)
  የሽንት ፖፖ ደፍቶ ባናቱ፡
  ወቴ ሲገማ ክነክርፋቱ፡፡
  “ፖፖ” ማለት ለለሊት ሽንት መጠቀሚያ እቤት ዉስጥ የሚቀመጥ ጎድጓዳ ፕላስቲክ ነው፡፡
  የጀመሩት እነሱው ክዚያም ክ17 አመት በኋላ ወያኔ አዲስ አበባ ገብታ ጦሩን ስትበትን “እሪ” ያሉት እነሱው፡፡ ሰም ይወጣል ክቤት ነው ነገሩ!
  እነዚህ ወታደሮች ይህ ቦታ የተሰጣቸው አቶ አንዳርጋቸው ራሳቸው በግል ዘምተው እያበረታቱዋቸው በተዋጉት የወያኔ ጦርነት ነው፡፡ ሌላው ይቅር በብ/ጄኔራል ምድብ በተራ ቁጥር 48 የተጠቀሱት፡ በቅጽል ስማቸው “ባለክዘራው” የተባሉት ናቸው፡፡ እሳቸውም 800 ካሬ በዛባቸው? አጼ ቴዎድሮስ “ትውልድ ይፍረደኝ!” ያሉት አሁን ገባኝ::
  ስላማችን ይብዛ

 3. ዳሹሬ:-
  አለቦታው ገብተህ ዳሸርክ::
  ምንም ይሁን ምንም አንዳርጋቸው ፅጌ ወያኔን በግንባር ሊፋለም ተዋጊ ሆኖ ከጏዶች ጋር ጫካ የገባና ሞት የተፈረደበት ጀግና ነው ::
  አብይ አህመድ የነካው ምን ያህል እንሚበላሽ ባታውቅም ገምትና አንዳርጋቸው በአብይ ተታሎ እንደነበር እወቅ:: ያ አቋሙ ስህተት ነበር:: እርሱም ብሎታል::
  ያ ሁሉ አልፎ ግንአንዳርጋቸው አሁን ከህዝቡ ትግል ጎን ተሰልፏል::
  በወያኔ የእብሪት ጦርነት ጊዜ የባለከዘራውን ውሎ ሁላችንም እናውቃለን:: ታድያ በዚያ ውለታ እንዴ ክሬድት ተውስዶለት ባለከዘራው የአማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ላይ የእብይን ትእዛዝ አንግቦ ሚሊዮኖችን እያረደና እያስገደለ እየገደለ ይቀጥል ነውን የምትለን??ወይንስ አንተም የአማራን ህዝብ የህልውናን ትግል ትቃወማለህ???
  የሆንከውን ሁን:: ባለከዘራውም የሆነውን ይሁን:: ይህ አሰላለፍ ነው:: እንዳችሁም ግን የአማራን የህልውና ተጋድሎ ልታስቆሙት ቀርቶ ልታዘገዪት አትችሉም::
  ልክ እንደ ወንጀለኞቹ እንደ ባለከዘራውና ሌሎችም የአብይ እህመድ ፀረ ህዝብ መደዴ ጀንራሎች ጥያቄህ መሬት ይሰጠኝ
  ከሆነ ጥያቄህን በደረጃህ አንተም ሰልፍ ግባና ጠይቃችው::
  አንዳርጌ:- በጀመርከው የኦሮሙማን እገዛዝ የማጋለጥና የመዋጋትም ትግልህ ግፋበት ::
  ድል በአማራነቱ እየታደነና እየተገደለ ላለው ለእማራ ህዝብና የህዝቡ አለኝታ ለሆነው ፋኖ

  የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ:-
  ለማይቀረው በግፈኛው ኦሮሙማ ተጠንስሶ እየተብላላ ላለው የእርስ በእርሱ ጦርነት ተዘጋጅ
  እኔም ፋኖ ነኝ :-

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share