የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ 13 ወር ፀጋ በሚል ርዕስ ካሳተማቸው ፖስተሮች አንዱ የሆነው የዝነኛዋ “ውቢት ኢትዮጵያ” ተፈጥሮአዊ ውበት የሚታይባት ወ/ሮ ውቢት አመንሲሳ…….

(አጭር የሕይወት ታሪክ)

ወ/ሮ ውቢት አመንሲሳ ከእናታቸው ከወ/ሮ ዓለሚቱ ኡርጂ ከአባታቸው ከአቶ አመንሲሳ እዴላ ጥቅምት 5 ቀን 1946 ዓ.ም በነቀምቴ ከተማ ተወለዱ፡፡ የሕፃንነት ዕድገታቸውን በእናትና በአባታቸው ቤት በእንክብካቤ ካሳለፉ በኋላ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን፣ በጎሬ አቡነ ሚካኤል ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ በሚገኘው የእቴጌ መነን ት/ቤት አከናውነዋል፡፡

ከዚያም ቀጥሎ ፣ በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ በሚገኙት ክራውን ኮሌጅ (Crown Secretary Since) በሴክሬተሪያል ሳይንስ (Secretary Since) በከፍተኛ ዲኘሎማ ደረጃ ፤ በሜንዶዛ ኮሌጅ Mendoza Training College) በኤር ቲኬቲንግና ሪዘርቬሽን(Air Ticketing and Reservatory) ሙያ ተመርቀዋል።

በተጨማሪም አዲስ አበባ በሚገኘው በኢትዮጵያ የማኔጅሜንት ኢንስቲትዩት በቢሮ ሥራና ማኔጅመንት (Office Operator Management) ፣ ከሣይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን የብሔራዊ ኮምፒተር ማዕከል ደግሞ የኮምፒዩተር አጠቃቀም ትምህርትን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀቶች አግኝተዋል። ወ/ሮ ውቢት የአማርኛ ፣ የኦሮምኛ ፣ እንግሊዘኛና የፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ ነበራቸው፡፡

⩩ ወ/ሮ ውቢት በሥራ ዘመናቸው

➻በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UN) በፀሐፊነት – ለሁለት ዓመታት

➻ በባህል ሚኒስቴር በኤክዩቲቭ ፀሐፊነት (oche Scea) ለሦስት ዓመታት

➻ በኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ኮሚሽን መሥሪያ ቤት በልዩ ፀሐፊነት የኰሚሽነሩ ረዳት በመሆን — ለአሥራ ሁለት ዓመታት፣

➻ በአልመሽ የግል ኩባንያ በረዳት አስተዳዳሪነት ለሦስት ዓመት ተኩል በመጨረሻም በኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ የግል ኩባንያ ከገዛ ዓ.ም ጀምሮ በሞት እስከተለየበት ቀን ድረስ ለሦስት ዓመት ተኩል በአስተዳደር መምሪያ ክፍል የሠራተኛ አስተዲደር ረዳት ሥራ አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል።

ወ/ሮ ውቢት ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ መሥሪያ ቤታቸውን ወክለው በተለያዩ ሥራዎች ሠርተዋል፣ ተሳትፈዋል ፣ በሠሩባቸው የሥራ ቦታዎች ሁሉ ሥራቸውን የሚያውቁና የሚያከብሩ ከባልደረቦቻቸው ጋር ተግባቢ በጋራ በመሥራትና ኃላፊነታቸውን ጠንቅቀው በማወቅ የተደነቁ አስተዋይ ሠራተኛ ነበሩ። ወ/ሮ ውቢት በተለይም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዕድገት በሚመለከት ከቋሚ ሥራቸው በተጨማሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ለዘመናት የማይረሳ ቅርስ ጥለው አልፈዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከታሪክ ማህደር: የውጫሌ ውል - መስፍን ማሞ ተሰማ

በዚህ ረገድ በነበራቸው የተፈጥሮ ድንቅ ውብት ተመርጠው ውቢት አትዮጵያ በመባል በሚታወቀው ፖስተር (Poster) ላይ ምስላቸው እንዲቀረጽ በማድረግ የኢትዮጵያ ውብት ለዓለም ቱሪስቶች እንዲቀርብ ያደረጉና፣ ከፖስተሩ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ የእርዳታ ማስተባበሪያ እንዲውል ያደረጉ አገር ወዳድ ነበሩ።

ወ/ሮ ውቢት ከሕግ ባለቤታቸው ከካፒቴን ብሩ ይርዳው ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን በአደረባቸው ሕመም በአሜሪካ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ 48 ዓመታቸው መስከረም 20 ቀን 1994 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

#ታሪክን_ወደኋላ

https://www.youtube.com/@TariknWedehuala

3 Comments

  1. ዘሀበሻ፦
    ስለስ ዉቢት ኢትዮጵያ የቀረበው ጽሁፍ በይዘቱ ትክክል ነው፡፡
    አስነዋሪው ነገር ግን እናንተ ይህንን ጉዳይ ባልችሁ ስለ ሴትዮዋ በዚህ ድረ ገጽ ላይ መዘገባችሁ ጥቅሙ፣ አገልግሎቱና መልእክቱ ምንድን ነው??
    አመንሲሳ??
    What relevance does it have to bring her up on this web page under “history” portion? stupidity!!
    ታሪክ ወደኋላ ለሚለው አምድ ከዚህ የተረኝነት ሽታ ከሚሸትበትጊዜ ላይ ተቁሞ ከዚህ ርእስ ይበልጥ እጅግ ብዙ ታሪክ ማህደር ፣ኢቀርቡ የሚጋባቸው ብዙ አሉ፡፤
    አሁን ጭቃ ማቡካት ምን አስፈለጋችሁ????
    ታሳፍራላችሁ፡፡

  2. ክቡር አቶ ታሪኩ ዘመን የማይሽረውን ከኦሮሞ የበቀሉ ድንቅ ኢትዮጲያዊያንን በዚህ ወቅት መጠቀስ ከድሮውም ተገቢውን የኦሮሞ የመብት ትግል ያሳቱና ከድንቅ ሃገራዊ የኢትዮጲያ ጭቁን ህዝቦች ትግል ወደኦሮሞ ትግል የቀየረው ታላቁ ባሮ ቱምሳ የሳተበትን ወንድሙ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ከጫካ ወደቤ/ክ ያስገቡትን ትግል ለማጋለጥ ይህን ጠማማ ትግል ሳይቀላቀሉ የቆዩ ድንቅ ኢትዮጲያንን ማውሳት በክፉ ትርክት የሄዱትን ይመልሳል የለየላቸውን በዚያ ያስቀራልና ሃስብ አይግባህ:: ራሴ ደግሞ ደግሞ የማውቃቸው ዶክተር ጳውሎስ ቀንአ የአያቴ ልዩ ሃኪም በውጭ ሃገር በዙ ዶላር ክፍያ እምቢ ብለው ሃገራችውን በታማኝነት ያገለገሉ የምእራብ ሶማሌ ጀነራል ሆኖ ያደማን ከሃዲ ዋቁ ጉቱ የተጀመረውን የገበሬዎች ትግል ተጠቅሞ ሲፋለም የማረኩት ድንቅ የሚሊታሪ ሊቅ ጄነራል ጃገማ ኬሎ የራሴ የአንደኛ ደረጃ አስተማሪ ብርቱ የኢትዮጲያ አንድነት ደጋፊ መሬት ላራሹ ትግል ስንረብሽ ባግባቡ ብሎ የመከረን የኢትዮጲያ እግር ኩዋስ የአፍሪካ ዋንጫ 3ኛ አሸናፊ ካደረጉን አንዱ እንዳለ ፈይሳን በርቅቡ ደግሞ የደረግ ሰራዊት የሚባለው የኢትዮጲያ ሰራዊትም የምለው ለመብቱ ሲታገልልት ገድሎ አስከሬኑን በአስመራ ጎድና የጎተተው ጄንራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ የህግ ጠበብቱ ለኢትዮጲያ ፍትህ በአለም መድረክ ባባቱ መገደል ቂም ሳይዝ የሚተጋውን ዶክተ ደረጀ ደምሴን ጠቅሳለሁ::የውቢቷ አልማዝ አመሲሳ ቤተሰቦች በኢትዮፒያዊንት ዛሬም የማያፍሩ ከዘመኑ ዘረኝነት የጽዱ ለመሆናቸው በቅርቡ በኢቢሲ የቀረበውን ፈልገህ ተመልከት:: ብዙ ሚልዮን አልማዝ አመንሲሳዎች ጃገማ ኬሎዎች ደሜስ ቡልትዉች አሉን ይኖራሉ;: ገና ድንቅ ኢትዮጲያዊ ኦሮሞዎችን ጨምራለሁ የራሴን ስንገናኝ አወራልሃለሁ::
    ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

  3. ፕስተር ዲጎኔ ሞረቴው፦
    ሀሳብህ (ሀሳብዎ) ገብቶኛል፡፡ እስማማበታለሁ፡፡
    ጀኔራል ጃገማ ኬሎ፣ ጀኔራል ደምሴ ቡልቶ፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነዴ፣ጀኔራል ተፈሪ በንቲ …..ወዘተ በዚህ በዘሀበሻ ድረ ገጽ ላይ በዚህ አምድ ስር ቢዘከሩ ትክክል ነው፡፡ ለዉቢት አመንሲሳ ይህ ቀን ወይንም ይህ ወር የተወለደችበት ወይንም የሞተችበት ነው በሚል”በውቢትነቷ” ለመዘከር ነው እንዳንል ነገሩ እንደዚያ አይደለም፡፡
    በአጠቃላይ በታሪክ አምድ ስር መዘከር ያለበት ቢያንስ ለእኔ ከእውነታወችና ከሂደቶች ጋር ሲቀራረብና ሲያያዝ ስለሆነብኝ ነው፡፤ ታዲያ ሁሉም ነገር ኦሮሙማና መልሶም ኦሮሙማ በሚሸትበት ስታው በጠነባበት በዚህ የትንቅንቅ ወቅት ምን ታስቦ ነው በምወደው በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይህ የተደረገው ነው የእኔ ጥያቄ፡፤
    አሁንም በጥያቄዬ እቆማለሁ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share