አይቀሬው የእርስ በእርሱ ጦርነት ማንን ይበልጥ ይጎዳል? (እውነቱ ቢሆን)

አብይ አህመድና ለማንም (ለኦሮሞ ህዝብም) የማይበጀው ግትልትሉ የኦሮሙማ መንጋ ከሁሉም በላይ እኛእና ”ሁሉም የእኛ  አስተሳሰቡ ጋር እስከወዲያኛው ተጠራርጎ  ካልተወገደ በስተቀር  አገሪቱ በእርግጠኝነት ወደማይቀረው የእርስ በእርስ ጦርነት ታመራለች፡፡ ይህ አይቀሬ ነው፡: ታዲያ ከዚህ  አይቀሬው የእርስ በእርስ  ጦርነት ማንም የሚጠቀም/ የሚያተርፍ ባይኖርም ማን “ይበልጥ”ይጎዳ ይሆን??

መገመት እንደሚቻለው በዚህ አይቀሬ በሚመስለው የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት  ይበልጥ የሚጎዱት  ከሚከተሉት ተፋላሚወች ከሁለቱ አንዱ ነው፡  አንደኛው ተፋላሚ አካል ሁሉንም እየሰለቀጠ ያለው ኦሮሙማ ሲሆን ሌላኛው አካል ደግሞ  በኦሮሙማ ተሰልቅጠው የጠፉት ማህበረሰቦችና አሁን በመሰልቀጥ ላይ ያሉት ሌሎች ህዝቦች ናቸው፡፡

አገሪቱ በተጨባጭ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር የእርስ በእርስ ጦርነቱን ለማስቀረት ብቸኛው መፍትሄ የስርአት ለውጥ ማድረግ ብቻ ነው፡  ይህንን የስርአት ለውጥ ጥያቄ አብይ አህመድና መንጋው ኦሮሙማ ተገድዶ ካልሆነ በስተቀር ፈቅዶ አይቀበልም፡፡ ኦሮሙማወች ለጊዜውም ቢሆን በጥጋብ ተነፋፍተው፣ በተለይም በሆዳም አማራ አሽከሮቻቸው የልብ ልብ ተስምቷቸው፣ በቅጥፈታቸው ቅቡልነት ያገኙ መስሏቸው፣ በህዝቡ መተፋታቸውን ሳያውቁ አሁንም በተሳሳተውና ሊመለስ ባማይችለው የጥፋት ጎዳናቸው ቀጥለውበታል፡፡ ጥጋብ የነፋው ይባል የለ???

ተረኞች ነን ብለው በይፋ የሚደነፉት  ኦሮሙማወች በ5 አመት ውስጥ የስሩት ግፍና እልቂት እያንቀዠቀዣችው አሁንም  ግፍ ከመስራት አልተቆጠቡም፡፤ አሁንም በታንክ፣ በመድፍ፣ በድሮንና በተዋጊ አውሮፕላኖች ንጹሀንን ይገድላሉ፡፤  ከተሞችን፣ የታሪክ አሻራወችን የሀይማኖት ተቋማትን፣ ፋብሪካወችን ትምህርት ቤቶችን፣ በከባባድ መሳሪያወች ያፈራርሳሉ፡፡ኦሮሙማወች ባለፉት 5 አመታት የሰሩት ግፍና እልቂት ወያኔ በ27 አመት ከሰራው ግፍ  በሚሊዮን ጊዜ እንደሚልቅ አይረዱም፡፤ ለመረዳትም አይፈልጉም ብቻም ሳይሆን የማገናዘብ ችሎታም የላቸውም፡፡

እድሜ ለተመስገን ጥሩነህ፣ ደመቀ መኮንን፣ አገኘሁ ተሻገርና የመሳሰሉት ታማኝና ሆዳም የአማራ አሽከሮቻቸው፡፡ አሁን ደግሞ  እድሜ አብይ አህመድ ጉያ ውስጥ ገብቶና በሚሊዮን  በሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች ደምና በሟቾቹ እናቶች እንባ ላይ ተረማምዶና በኦሮሙማ አንቀልባ ታዝሎ  “ወልቃይትንና ራያን “አሰጡኝ እያለ ለሚያላዝነው ወያኔ፡፡ እነዚህን ሁለት የተሰባበሩ ምርኩዞችን ይዞ  አብይ አህመድ አሁንም ልቡ እንዳበጠ ነው፡፡ ሰውየው አሁንም በቅዠት አለም ውስጥ ስላለ  እየመጣ ስላለው አደጋ ሁኔታወችን አመዛዝኖ  ሊረዳ የሚችል ጭንቅላትም የለውም፡፡ ስለዚህ ጦርነቱ ይቀጥላል ማለት ነው፡፡

አንድ ማሳያን ብቻ ላንሳላችሁ፡፡

አማራው አሁን እያደረገ ያለው የህልውና ተጋድሎ ከማሸነፍ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ይህንን የአማራ  የህልውና ተጋድሎ እንኳን ግትልትሉ የኦሮሙማ ጦር ሌላ ሀይል ወይንም ብዙ  ሀይሎችም ተጣምረውና ተጋግዘው ቢመጡ ተጋድሎውን ሊያንበረክኩት ቀርቶ ድሉን ሊያዘገዩት ፈጽሞ አይችሉም፡፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ሳልሰማ ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ” - ተስፋዬ ገ/አብና የሶሻል ሚዲያዎቻችን ነገር 

የፋኖ ተጋድሎ ከጀርባው 56 ሚሊዮን ለአማራነቱ ለመሞት የቆረጠ ህዝብ አለው፡፡ ይህ ማጋነን አይደለም፡፤ ፕሮፓጋንዳም አይደለም፡፤ ግልጽ ለማድረግም  ያህል የአማራው  ተጋድሎ  የህልዉና ማለትም የመኖር ያለመኖር ተጋድሎ ነው፡፡  አማራውን ወያኔ 27 አመትና ኦሮሙማም ደግሞ 5 አመት ሙሉ ህገ መንግስት፣ ብአዴን፣ብልጽግና… ምናምን  እያሉ በራሱ ሆዳም ልጆች አሽከርነት ለዚህ ሁሉ መታረድ፣ መጨፍጨፍ፣ መዋረድና አገርየለሽ መሆን ስለዳረጉት ማንነቱን  በአማራነቱ  አማራነቱንም  በነፍጡ  አስመልሶ   ካላረጋገጠ በስተቀር የጀመረው ተጋድሎ አይቆምም፡፡  በአገር ደረጃም ታላቅ ራእይን ሰንቆ ኢትዮጵያን ደረስኩልሽ እያላት ነው፡፡

ለዚህ ነው መሬት ላይ ያለው የአማራ ህዝባዊ  ግንባርና አመራሩ መነሻዬ አማራ  መድረሻየ ኢትዮጵያ ነው ያለው፡፡ ይህ ቁርጠኝነት  መሬት ላይ እየተተገበረ ባለበት ሁኔታ  የእርስ በርስ ጦርነቱ  መከሰትና  እንዲሁም የአብይ አህመድ መቀለጃ የሆነው የእርቅ ወይንም የሽምግልና/ድርድር ምናምን  ኮሚሽኑ የሚሉት ነገር ለአማራው ምኑም አይደለም፡፡

በተመሳሳይ መልኩም አስቂኝ የሆነውም በዲያስፖራ በኩል የሞተው ብአዴን እያደረገ ያለው መፍጨርጨር ነው፡፡ በአብይ በኩል ታቅዶ በአማራ አስሽከሮቹ  (ዲያስፖራ ባለው  የብአደን ስብስብእንዲተገበር የተሰላው ፋኖን የመጥለፍ፣ የማኮላሸት ሙከራ ከወዲሁ ተነቅቶበት ከሽፏል፡፡ ፋኖንና የህዝባዊ ሀይሉን   ብአዴን  አደራጅቶት  በነበረው አድማ በታኝና የአማራ ሚሊሽያ ወዘተ.. በሚል  ስም ለማጥቃት የተሰለፈው  ግብስብስ  የአማራ  ከሀዲወች   ስብስብ በተገቢው  መንገድ ዋጋው እየተሰጠው ስለሆነ  የፋኖን ትግል አያደናቅፈውም፡፡

አብይ አህመድ ከዚህ የሚያተርፈው አማራን በአማራ አባላሁት የሚለውን እኩይነት ብቻ ነው፡ በአሁኑ 21ኛው ክፍለ ዘመን ራሱ ግራኝ አህመድ  ቢኖር ኖሮ የአብይ አህመድን ያክል ጨካኝና እቡይ ይሆን ነበርን?? በእኔ ግምት አብይ አህመድን የሚወዳደር እኩይና እቡይ ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተፈጥሮ አያውቅም፡፡

ወደ ርእሴ ልመለስ፡_

የእርሰ በእርስ ጦርነት  ማጠንጠኛው “”ይህ መሬት የኔ ነው“” የሚለው ጥያቄና ይህም ጥያቄ በይዘቱም ሆነ በጥልቀቱ  ዋናው የጦርነቱ ሞተር መሆኑ ነው፡፡ እናስ እርሰዎ ከዚሁ አላስፈላጊ የነበረ  “ወቀጣ” ማን ይበልጥ ይጎዳል ብለው ያስባሉ???

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ! - ማላጅ

እንደ እኔ ግምት እንደላስቲክ በሁሉም አቅጣጫ ተንሰራፍቶና ተነፋፍቶ የተለጠጠው ኦሮሙማ አንሶ አንሶ ኩምሽሽ ብሎ ወደትንሽነት የሚቀየር ይመስለኛል፡፡ያኔ ሁሉም የየራሱን ትክክለኛ ቦታና መሬቱን ከኦሮሙማ ጉረሮ መንጭቆ ወደነበረበት ወደራሱ ለማድረግ ሁሉም በየማእዘኑ  ከኦሮሙማ ጋር ይፋለጣል፡፤ ይዋደቃል፡፡  ሰላምና እረፍት ያኔ ኦሮሙማ መንደር ህልም ይሆናል፡፡ ከአራቱም አቅጣጫ የኦሮሙማ ወሰኖች የተዋጡና የተሰለቀጡ ህዝቦችና በኦሮምያ መስፋፋት ተውጠው   መሀል የተደረጉ  ሌሎች  ብሄር  ብሄረሰቦችም  ለነጻነታቸው ተገቢውን ዋጋ እየከፈሉ ራሳቸውን ከኦሮሙማ ነጻ ያወጣሉ፡  ኦሮሙማ ከሁሉምጋር ተዋግቶና ሁሉንም ጨፍልቆ ማሸነፍ የማይችለውና እንደዚህም የማድረግ ቅንጣት የታሪክ አሻራ የሌለው ስለሆነ በቀላሉ ይረታል፡፤ እዚህ ላይ ለማስታወስ ያህል አዋሽ ድረስ መጥቶ የነበረውን የዚያድ ባሬን የሶማሊያ ወራሪ ጦር በታጠቅ ጦር ሜዳ የ3 ወር ስልጠናን ወስዶ ወራሪውን የሶማሊያ ጦር አይቀጡ  ቅጣት ቀጥቶ ኦሮሙሞን ነጻ ያወጣው በአብዛኛው የአማራው የገበሬ ጦር ነው፡፡ ይህ ታሪክ ስለሆነ ሊካድም አይችልም፡፡

ስለ መጪውና አይቀሬው የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመማር የሩዋንዳን  ታሪክ ማየት ብቻ በቂ  ነው፡፡ በእኔ ግምትና እምነት በዚህ ጦርነት የኦሮሞ ያልሆኑና የኦሮሞ ያልነበሩ በኦሮሚያ  የተሰለቀጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብዙ መሬቶች፣ ከተሞች፣ ወደነባር ባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡ ዝርዝሮቻቸው ብዙ ሲሆን ሁሉም ግን ባለቤቶች አሏቸውና ለነባር ባለመብቶቹ ተመላሽ ይሆናሉ፡  በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ይህ እስካልተደረገ ድረስ አለባብሶ ማረሰ ይሆናል፡፡ ችግሩን ቢሸነግሉት ጊዜና ወቅት ጠብቆ ማገርሸቱ አይቀርምና ቁስሉ እስከመጨረሻው ይደርቅ ዘንድ ችግሩን ከስሩ መፍታቱና ወደነበረበት ወደባለቤቶቹ መመለሱ  ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡  በአማራው በኩል ይህ ቁርጠኛ አቋም ተደርጎ ተወስዷል፡፡

 

ለምሳሌነት ያህል በኦሮሙማ የተሰለቀጡ  ጥቂት መሬቶችን/ከተሞችን/ቦታወችንብቻ  ልጥቀስ፦ የሲድማው የነበረቸው ሻሼመኔ፣ በኦሮሙማ የተሰለቀጠው የሀረሪ ህዝብ፣ የዝዋይ ሀይቅና አካባቢው ታሪኩ ተደምስሶ ባቱ መባሉ፣ በዚህ ሳምንት ውስጥ የተደረገው ሰሜን ሸዋ በሸንኮራ ወረዳ በጣም ስትራቴጅክ የሆነችው የአውራ ጎዳና ከተማን ሙልጭ አድርገው ከዘረፏትና ኗሪዉን ቤት ለቤት እየገቡ ከጨፈጨፉት በኋላ ስሟን ቆርኬ በማለት ከተማዋን የመሰልቀጡ ዘግናኝ ድርጊታቸው፣ ወዘተ…..ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፤ በሚገባም ሁሉም ስለሚታወቅ ሁሉንም እዚህ ላይ መርዘሩ አያስፈልግም፡   እንደተባለው እስክሁን በዚህን ያህል ራዥም ጊዜ ውስጥ ብዙ የኦሮሙማ ስልቀጣወች ተካሂደዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የታቀደው የመንግሥትና የሕወሃት ንግግር፣ መሰናክሎቹና የሚጭረው ተስፋ - ባይሳ ዋቅ-ወያ

አማራን በሚመለከትም በኦሮሙማ የተሰለቀጡት የአማራ መሬቶች  ይህንን ያህል ጊዜ ሳይመለሱ የቆዩት በብአደን ሆዳሞች ሸክምነት መሆኑ ተደጋንሞ ተገልጿል፡፡ አዲስ አበባን  ፊንፊኔ/ መናገሻ እያሉና አብይን አህመድን ከላይ ቁጭ አድርገው ለሁለት ግራና ቀኝ ቆመውከተማዋን የተካፈሉትኮ [መካለል የሚለው አግባብ አይደለም] ቀበሮዋ አዳነች አበቤና ጀዝባው ሽመልስ አብዲሳ ናቸው፡፡

ስንት የአዲስ አበባ ከተማ ታሪካዊ ቦታወች እየተናዱ ለኦሮሙማወች ተከፋፈሉ?? አንዷን ብቻ ላስታውሳችሁ፡፤ታሪካዊ  አንበሳ ፋርማሲ፡፡ የሌሎቹንም ዝርዝሮች ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል ብቻም ሳይሆን መዝግቦ ይዟቸዋል፡  ምስሌ፦ ከከንቲባዋ ቢሮ በቀጥታ ለምርኮኛው አምሳ አለቃ (ለፊልድ ማርሻሉ በህርሀኑ ጁላ) በስሙ ካርታ ተሰርቶ በቦሌ የተሰጠው ሰፊ ቦታ ሁሉ በሚገባ ተመዝግቧል፡፡ የሁሉም ዝርፊያወች መዝገብ ከነጻነት በኋላ ይከፈታል፡፡፤ ያኔ ሁሏም ዘራፊና ዝርፊያ በነቂስ ዋጋዋን ታገኝና አዲስ አበባ ወደነበረችበት ትመለሳለች፡፤የፌደራል መንግስት መቀመጫ የሆነችው የዱሮዋ ክልል 14 አሁን ተኮርኩማና ጠብባ ጠብባ ትንሽ ከተማ እንዲትሆን  የተደረገችው  አዲስ አበባ  የማንም የግል ሀብትና የማንም ተቀጥላ አካል ሳትሆን ወደ በፊቱ ስፋትዋ ታላቅነቷና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዋና ከተማነቱ ትመለሳለች፡፡ በኗሪወቹ በአዲስ አበቤወች ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ብቻ በሚመራ መስተዳድርና ከንቲባም ትመራለች፡፡ የአዲስ አበቤወች ከተማ ሆና ስሟንና ክብሯን ህንጻወቿንና ታሪካዊ ቦታወቿን ስፋትዋንና ድንበሮቹዋን  ወደነበሩበት አስመልሳ በህዝብ ለህዝብ የምትተዳደር ራሷን የቻለች ከተማ ሆና ትቀጥላለች፡፡ ከሁሉም ህዝብ ለብቻው ተለይቶ በከተማዋ ውስጥ  የኦሮሚያ መስተዳድር ፣የኦሮምያ ቢሮ፣ የኦሮምያ ሸገር ከተማ ፣ የኦሮምያ ምናምን የሚባለው ድሪቶ ሁሉ ተቀዳድዶ ይጣላል፡፡ አዲስ አበባ በህግ ወደነበረበችት እስከምትመለስ ድረስ ህዝቡ ተጋድሎውን አጧጡፎ ይቀጥላል፡፡

በኦሮምያ አራቱም ማእዝናት ብቻም ሳይሆን የመሬት ስልቀጣውን ከኦሮሙማ ጉረሮ የማስተፋቱ አመጽና ትንቅንቅ በዚህችም  የአገሪቱ የፖለቲካ መፍለቂያ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማም  ይተገበራል፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በሁሉም ማእዘናት መሬቱን፣ ርስቱን፣ ሀብቱንና ማንነቱን አስወስዶ ዝም ብሎ የሚቀማ ህዝብ እንደማይኖር ሁሉ 7 ሚሊዮኑ አዲስ አበቤም ከተማውን አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ይህ የአማራ ህዝብ አቋም ነው፡፤ ይህ አብይ ያስገደለው የአቶ ምግባሩ ከበደ የአደራ ቃል ነው፡፡

አንዲት የአማራ ግጥምን ላንሳላችሁና አጭሯን ጽህፌን ልቋጭ፡፡

በለው በምንሽር አስኪደው በዋንዛ

በአባት አገርና በሚስት የለም ዋዛ!!

ከስርአት ለውጥ መለስ በማይቀረው የእርስ በእርስ ጦርት ማን ይበልጥ ይጎዳል?? መልሱን ለእርሰዎ!!!

ድል የውድ አገአርችን ኢትዮጵያ አንዱ መሰሶ ለሆነው ለአማራ ህዝብ!! እኔም ፋኖ ነኝ፡፡

 

6 Comments

 1. አማራ ከማሸነፍ በስተቀር በህይወት ለመኖርና ዘሩን ለማትረፍ ምንም ምርጫ ስለሌለው ለህልውናው መዋጋት ግደታው ነው፡፤ ይህም ስለሆነ ተፈለገም አልተፈለገም አግጥጦ እየመጣ ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ማንም ሊያስቆመው አይችልም፡፡
  ከመዝረፍና ህዝብን በዘር እየለዩ ከመጨፍጨፍ በተጨማሪ የኦሮሙማ የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት እቅዱና እንቅስቃሴው የመንጋውን እንሰሳነት ቁልጭ አድርጎ ያስያል፡፡
  በኢትዮጵያ መቃብር ልይ ለሚመሰርታት ታላቋ ኦሮሚያ በዙሪያው ያሉ ክልሎችን ፣ዞኖችን፣ ወረዳወችን ለመሰልቀጥ ብዙ ጥረቶችን እያደረገ ነው፡፤ ጥቂት የማይባሉትንም ስልቅጧቸዋል፡፡ ብዙወቹን አናሳወችንም አጥፍቷቸዋል፡፡
  በዚህ ሳምንት ብቻ ታፍኖ ነው እንጅ በአማራ ክልል ውስጥ በሽዕንኮራ ወረዳ ከሚገኘው የአውራ ጎዳና ከተማ ስልቀጣ ሌላ ብዙ የሶማሊያ ወረዳውችን ጠቅልሎ ወደራሱ ለማድረግ ከሶማሊያ ህዝብ ጋር ዉጊያ ላይ ነው፡፤ ምን አለፋችሁ ኦሮሙማ ሊውጠው ያልሞከረው አጎራባች ክልልና ዞን የለም፡፤ ከአፋሩ፣ ክጉራጌው፣ ከጋምቤላው፣ ከስዳማው፣ ከቤንሻጉልና ጉሙዝ ፣ ከወላይታው ከአማራው ክደቡብ ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር የ””ልሰልቅጣችሁ”” ሌሎቹ እምቢ “”አንሰለቀጥም”” ግብ ግብ ውስጥ ነው ያለው፡፡
  እኔ ከተቀባው ዛፍ ራቅ ብዬም ቢሆን “”በዋቄ ፈታ”” እምላለሁ የኦሮሙማ አገዛዝ ይህንን የእርስ በእርስ ጦርነት አያልፍም፡፡ ላይመለስ ወደነበርነት ይቀየራል፡፡

 2. መልካም ጽሁፍ ነው ብአዴን በሚሉት በድን ላይ ትንሽ ብትቆይበት መልካም ነበር። በረከት ስምኦን ከየት ፈልፍሎ አገኛቸው በድን በድኖችን።

 3. የእርስ በእርስ ጦርነት ብዙ ይጎዳል:: አያድርስ ነው:: ተረኞቹስ መሳሪያም ብርም አላቸው :: ሌላው ምን አለው???
  ዝም ብሎ መረገጥ ድግሞ ያማል ::
  ፈጣሪ እምላክ ድረስልን እባክህ::

 4. የኦሮሞ ልዩ ሀይል ስሙን ሸኔ ይበሉት ወይንም አይበሉት የአብይ አህመድንና የሽመልስ አብዲሳን ትእዛዞች ይዞ መላውን የኦሮሞ ህዝብ ወደ ገደል ይዞት እየነጎደ ያለው ይህ የመንጋ ስብስብ ነው፡፤
  ይህች የዛሬዋ የጥጋብ ቀን ዛሬዉን ታልፋለች፡፤ ነገስ???
  ስለሆነም የሚፈራው የእርስ በእርስ ጦርነት አይቀሬ ነው፡፡ ስሟን ከአውራ ጎዳና ወደ ቆሬ የቀየሯት የሰሜን ሸዋ የሸንኮራ ከተማ ትኩስ ሬሳና ትኩስ ዘረፋ እየተካሄደባት ነው፡፡ ይህንን “ቻሉት፣ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት አታስገቡን” የሚል ሰው ካለ ራሱን ይፈትሽ፡፤
  ብዙ እልቂቶችን ቢያመጣም የእርሰ በእርስ ጦርነቱ ብቻ ነው የጓሸውን አጥርቶ ለአገሪቱ ዘላቂና ፍቱን መድሀኒት ሊያመጣ የሚችለው፡፡

 5. ጦርነቱ የሚካሄድ ከሆነ ሁሉንም የሚጎዳ ቢሆንም ይበልጥ የሚጎዳው ግን ለጦርነቱ አይቀሬነት መንስኤ የሆኑትን ነው፡፡ እነርሱም አብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳና እነርሱ ያስከተሉትን መንጋወችና የኦሮሙማ ክፍልፋዮችን ያጠቃልላል፡፡
  መቼም ቢሆን አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ጦርነቱን ስለማይዋጉት ሁለቱ የወጡበት ብሄረሰብማለትም የፈረደበት የኦሮሞ ህዝብ ይበልጥ ተጎጅ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ በስሙ የሚነግደውን ይህንን የኦሮሙማ ፈላጭ ቆራጭ አናሳ ስብስብስ ማስቆም ካልቻለ ከኦሮሙማ ተጠቃሚ የሆኑት ክሁለትና ሶስት ሽህ የማይበልጡቱ እንጅ ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ስላልሆነ ህዝቡ አስቀድሞ ሊያስቆማቸው ይገባል፡፡

 6. ጽሁፉለሆዳሞቹና ለተረኞቹ የማይመስል ነገር ግን ለትጉሀን ሊሆን የሚችል ወቅታዊ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ ነው፡፤
  ይህንን ጠቃሚ ማስጠንቀቂያ ጽሁፍ በሰራተኞቻቸው በኩል ቢሰሙትም ወይንም ራሳቸው በዘሀበሻ ድረ ገጽ ላይ ምን ተጻፈ የሚለውን በየእለቱ ማወቁ ስላማያስችላቸው ያነቡታል፡፡
  በሆነው መንገድ ይህንን ማስጠንቀቂያ ቢሰሙም ግን አሹፈውበት ነው የሚያልፉት እንጅ ይሆናል አይሉም፡፡ ልባቸው ተድፍኗላ!! ልባቸው ህሊናቸው በምን ተደፈነ ለሚለው ጥያቄ ራሳችሁ ድረሱበት ነው መልሱ፡፡
  የሚመለከትህ ህዝቤ ሆይ፦ ራስህን ለማይቀረው አዘጋጅ!!! ተናብብ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share