ፋኖ ተሰማራ!

በገጥ ለገጥ ፍልሚያ አይቀጡ ሲቀጣ፣

እንደ አይጥ ሾልኮ ሄዶ ድሮን ሲያፈነዳ፣

ህፃናትን ሲገድል ልጆች ሲያደርግ ሽባ፣

የአማራን ዘር ጠርጎ ተምድር ሊያጠፋ፣

ፋኖ ተጠራራ ቆላ ወይና ደጋ ፣

በቁጭት በንዴት ገንፍለህ ተነሳ!

 

የእርጉዝ ሆድ ቀዳጁ ሰይጣን ቀንድ ሲያውጣ፣

ብልትን ቆራጩ ሰዶም ደም ሲጠጣ፣

አይን የሚፈነቅል ዲያብሎስ ቅጥ ሲያጣ፣

እሬሳ እሚጎትት አውሬ ጅብ ሲመጣ፣

ኧረ ጎራው ብለህ ፋኖ ተሰማራ!

 

ፋኖ ተመሐሉ ዳር አገር አማራ፣

እንደ አምስቱ ዘመን ሞረሽ ተጠራራ፣

አገርህ ተወሯል ዘርን በሚያጠፋ!

 

ፎክር እንደ አያትህ ሸልልና አቅራራ፣

በከዘራህ መድፍን በበልጅግ ታንክ ቀማ!

 

ፋኖ ተሰማራ በዓባይ ሸለቆ ስርጥ በጫካ በፊላ፣.

ፋኖ ተሰማራ በተከዜ መልካ በዳሽን ተራራ፣

ፋኖ ተሰማራ በጀማ ወንዝ ጋራ በአንኮበር ጉብታ፣
ፋኖ ተሰማራ በበሽሎ ዳገት ላይ ሽቅብ ላሊበላ፣

ፋኖ ተሰማራ በእንጦጦ አቀበት ላይ በአዋሽ ወንዝ ሜዳ፣

ወራሪ ወሮሀል ዘርን የሚያጠፋ!

 

ፋኖ ተሰማራ በአውሮጳ አሜሪካ፣

ፋኖ ተሰማራ በመላው አፍሪካ፣

ፋኖ ተሰማራ ሲድኒ ኤሽያ፣

ፋኖ ተሰማራ በምድሪቱ ሁላ፣

ጭራቅ ለፍርድ አቅርብ ዲፕሎማሲ ስራ!

 

ፋኖ ተሰማራ ስትወድቅም ተነሳ፣

እንደ ነብር ተሳብ እንደ አንበሳም አግሳ!

 

ፋኖ ተሰማራ በጫካው በዱሩ በገጠር ከተማ፣

ፋኖ ተሰማራ ተዳር ዳር አማራ፣

በአገር ውስጥ በውጭም ያለህ የትም ቦታ፣

ጭራቅ አገር ወሯል ዘርህን የሚበላ፣

ሞረሽ ተጠራራ ፋኖ ተሰማራ!

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መስከረም ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዘመናዊ  ፉከራ - በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share