የእኛ ኢትዮጵያዉያን ችግር ዞትር “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ከሆነ ከራርሟል ፡፡ እንዲያዉ ዕዉነት መናገር ስለዕዉነት ማደር ቀረ እንጂ የግማሽ ክ/ዘመን ዕድሜ ያስቆጠረ የህዝብ እና የአገር መከራ ቀንበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደረጀ መምጣቱ ግልፅ ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ዘመን ተተክቶ በሄደ ቁጥር በማንነታቸዉ ፣ በዕምነታቸዉ እና ኢትዮጵያዊ ሠዉ በመሆናቸዉ ያልደረሰባቸዉ የምድር ላይ መከራ እና ስቃይ አልነበረም የለም ፡፡
ለዚህ የመከራ ዘመን መራዘም እና መለመድ ደግሞ አዋቂ የሚባሉ እና ዕዉነትን እንዲናገሩ የሚጠበቁ ታላቆች አድር ባይነት እና ጥፋትን በጥፋት ስም ያለመጥራት እና ጥፋተኛዉንም የመፍራት አባዜ ዉጤት ነዉ ፡፡
ላለፉት ሶስት ዓመታት በትህነግ የተነሳዉ የጦር ክተት አዋጂ ዓለማዉ የዓማራ እና አፋርን ህዝብ በኃይል ወረራ በማካሄድ ማንበርከክ እና ግዛት ማስፋፋት ሆኖ ሳለ ጥቃት እና ወረራ የተፈፀመበት ህዝብ ነገሩን የህልዉና ነዉ ብሎ ሲነሳ ሌላዉ እና በኢትዮጵያ ህዝብ መስዋዕት ዳር ሆኖ ተመልካች የህግ ማስከበር ሲል ሌላዉም ይህን ያስተጋባል ፡፡
ከዚያ ቀጥሎ የተዳፈነዉ የጥፋት እና ዕብሪት ዕሳት ሳይጠፋ በዓማራ ክልል የህልዉና ተጋድሎ በደም እና ህይወት ቤዛነት የተገኘ (የተማረከ) ጠበንጃ “ጥቁር ጠብመንጃ ” ሰበብ የተጀመረዉ ስጠኝ አልሰጥም በዓማራ ህዝብ ላይ የሚካሄደዉ ጦርነት ግጭት ወይም የዕርስ በርስ ግጭት ዕያሉ ህዝብ እና አገር በዕሳት ወላፈን ሲነድ ዳር ዳር ማለት ማወቅ ሳይሆን መዘባረቅ ዘላቂ ብሄራዊ ስምም ሆነ ጥቅም እንደማያስገኝ እየታወቀ የሰለሳ ዓመታት የአገር እና የህዝብ መስዋዕትን በአንድ ቀን መቀንበብ ለዕዉነት እና ለፍትህ ገድየለሽነት ነዉ ፡፡
ስለዕዉነት ሁላችንም ለአገራችን ያገባናል ካልን ማስቀደም ያለብን ዕዉነተኛ ይቅርታ እና ዕርቅ መሆን ነበር ፡፡ ይህም የህዝብ እና የአገር ጉዳይ ከምንም እና ከማንም በላይ መሆኑን እና ህዝብም የደረሰበት ፣እየደረሰበት እና ዕየጠየቀ ያለዉ የመብት ፣ ነፃነት እና ዕኩልነት ጥያቄ መሆኑን መመስከር እና መናገር ያስፈልጋል ፤ ጊዜዉም አሁን ነዉ፡፡
ያየንዉን እና የሆንዉን እያለባበስን ስለማይታዉ እና ስለማናዉቀዉ በነሲብ መናገር ከንቱ ዉዳሴ ካልሆነ በቀር ከአዋቂነት ወደ ዘባራቂነት ተራ የሚያወርድ ነዉ፡፡
ዜጎች ባላቸዉ ሠዉ ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ልዩነት ፣የግል አመለካከት ፣ዕምነት እና ማንነት ያለጥፋት ጥፋተኛ በሚባሉባት እና የሚገለሉባት አገር ሠባዊ እና የጠፈጥሮ ክብራቸዉ እና ነፃነታቸዉ በቀላሉ በሚገሰሱባት ኢትዮጵያ ሁሉን በስም እና በልክ አለመጥራት ፍትህም ፤ዕርቅም ማሰብ ከንቱ ነዉ፡፡
ህዝብ በየትኛዉም ዓለም ሆነ በኢትዮጵያ የስርዓት ለዉጥ ታሪክ ተሳስቶ እንደማያዉቅ ይልቅ የሚያስቱትን የቀበሮ ባህታዉያን ሲከተሉት የሚመራ ሲያሳስቱት ከገደል አፋፍ በምክር እና በተግባር የሚመልስ ነዉ ፡፡
፡፡ ለዚህም በ1966/7 የብዙ ዓመታት ተንሰራፍቶ የኖረዉን የዘዉድ ስርዓት በመራር ትግል በመነሳሳት እና በማቀጣጠል የህዝብ ሚና የማይናቅ ሚና ነበረዉ ፡፡ ዛሬም ኢህአዴግ ካልታልኩ አላምን እንዳለችዉ ሙሽሪት ህዝብ በከፈለዉ እና በሚከፍለዉ ተደጋጋሚ መስዋዕትነት ከታዘልኩበት የህዝብ ጫንቃ አስካልረድኩ ድረስ ጥፋተኛ ፤ ስህተተኛ ….ህዝብ ነዉ ማለቱ ዕዉነት እና ምስክርነት እንዲሰጡ ከሚጠበቁ ታላቆች ሲስተጋባ ለዘመናት ማየት የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡
የምናከብራቸዉን እናከብራለን መከባበር ግን መሳ ለመሳ መሆን አለበት ካልሆነ የህልም ሩጫ ይሆናል ፡፡ ስለሠላም ፣ስለርቅ፣ ስለንግግር ስለ አገር ስንመሰክር በቦታዉ እና በሁኔታዉ ዉስጥ ሆነን እንጂ የተሰሳቱ ከስተታቸዉ እንዲመለሱ ማለት ለህዝብ እና ለአገር ያለንን ቦታ እና ገፅታ ብዥታ ዉስጥ መኖራችንን ያሳያል፡፡
በመጨረሻም ህዝብ አይሰሳትም ህዝብ ለማሳሳት የሚሰሳት ግን የለም ወይም አልነበረም ማለት አንልም ፡፡ ለዚህ በአስረጂነት ኢህአፓ በከተማ ዉጊያ ህዝብ አሳስቶ ቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር ጠባሳ አሳርፏል፡፡ በመጨረሻም ህዝብን አሳስቶ ማጣፊያዉ ሲያጥረዉ ወደ ጫካ እና በርኃ ከትሞ የስም እና አሰላለፍ ለዉጥ አድርጎ ዛሬም በኢህአዴግነት እኔ ከሞትኩ ….አገር ይጠፋል ፤ ህዝብ ይሞታል እያለ ነዉ ፡፡
የአገር እና የህዝብን ጉዳይ የተኩላ እና በግ የራት ምርጫ ብልጣብልጥነት እና ክፋት ካለበት ሴራ በላይ መሆኑን ተረድተን በጋራ አገራችን በይ እና ተመልካች ሳንሆን በዕኩልነት፣ በነፃነት እና በአንድነት መኖር የምንችልባት ኢትዮጵያን ወደ ነበረ ክብሯ ለመመለስ ከፖለቲካ እና ከምድራዊ ህግጋት ሁሉ የሠዉ ልጆችን የህልዉና እና ነፃነት ተፈጥሯዊ ማንነት ማክበር እና ማስከበር ላይ እንረባረብ ፡፡
Allen!
አንድነት ኃይል ነዉ !