September 7, 2023
6 mins read

የዳንኤል ክብረት ጎቤልሳዊ ፍፃሜ

Daniel Kibretሐሳዊ ተዋኙ (con artist) ጭራቅ አሕመድ ወደር የለሽ የሐሰት ትወና ክሂሎቱን በመጠቀም አያሌ ጉምቱ ጦቢያውያንን አይዋረዱ ውርደት አዋርዷል።  ከሁሉም በላይ ያዋረደው ግን ያለ ምንም ጥርጥር ዳንኤል ክብረትን ነው።  ከሞላ ጎደል ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚያደንቁትን ሰው አር እንደነካው እንጨት እንዲፀየፉት አድርጓል። ዳንኤል ክብረትን የኦሮሞ ፅንፈኞች ድሮውንም ቢሆን ስለማይወዱት፣ ተልዕኮውን የጨረሰ ሲመስላቸው በርግጠኝነት አጋድመው ያርዱታል። ትግሬወች እጃቸው ላይ ከገባ ያለ ምንም ጥርጥር በዘይት ይቀቅሉታል።  አማሮች፣ ጉራጌወች፣ ጋሞወችና የቀሩት ደቡቦች ደግሞ በጫጭቀው ቢጥሉት ደስታውን አይችሉትም።

የዳንኤል ክብረት አንዱና ብቸኛው መፅናኛው በዚህ ደርጃ ያዋረደኝ ተራ ሰው ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው የሚለው ነው። ስለዚህም የጭራቅ አሕመድ የስልጣን ዘመን መርዘም ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ለዳንኤል ክብረት የሞት ሽረት ጉዳይ ነው።  ጭራቅ አሕመድ ከስልጣን ከተወገደ ወይም ከሞተ ዳንኤል ክብረት የውርደቱን ብቸኛ መፅናኛ ስለሚያጣና ሕይወቱ ምንም ትርጉም ስለማይኖረው ራሱን ብቻ ሳይሆን ልጆቹንና ባልተቤቱን ይገድላል

በዚህ ረገድ ዳንኤል ክብረት ከናዚው የቱልቀዳ (propaganda) ሚኒስቴር ከዮሴፍ ጎቤልስ (Joseph Goebbels) ጋር በብዙ ረገድ ይመሳሰላል።  ጭራቅ አሕመድ በዳንኤል ላይ ያለው ፍፁማዊ ተፅእኖ (influence)፣ አዶልፍ ሂትለር (Adolf Hitler) በዮሴፍ ጎቤልስ ላይ ከነበረው ፍፁማዊ ተፅእኖ ጋር አንድ ዓይነት ነው።  ዳንኤል ክብረት አልፋና ኦሜጋውን ጭራቅ አሕመድን ያደረገው፣ ዮሴፍ ጎቤልስ አልፋና ኦሜጋውን አዶልፍ ሂትለርን እንዳደረገው ነው።  ዳንኤል ክብረት ጭራቅ አሕመድን እንደ እየሱስ የሚመለከተው፣ ዮሴፍ ጎቤልስ አዶልፍ ሂትለርን እንደ መሲሕ ይመለከት እንደነበረው ነው።  ዳንኤል ክብረት በጭራቅ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ላይ ሙሉ በሙሉ የተንጠለጠለው፣ ዮሴፍ ጎቤልስ ባዶልፍ ሂትለር ቻንስለርነት ላይ ሙሉ በሙሉ ተንጠልጥሎ በነበረበት ሁኔታ ነው።

ስለዚህም ያዶልፍ ሂትለር ቻንስለርነት ገመድ ሲበጠስ፣ ዮሴፍ ጎቤልስ የሒወቱ ክር መበጠሱን አውቆ፣ ስደስት ልጆቹን በሳይናይድ (cyanide) መርዞ ከገደለ በኋላ ራሱንና ሚስቱን እንዳጠፋው፣ የጭራቅ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ገመድ ሲበጠስ ደግሞ ዳንኤል ክብረት ተመሳሳይ ድርጊት ያደርጋል።

ስለዚህም የዳንኤል ክብረት ያሁኑ ሙሉ ትኩረት የጭራቅ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ገመድ እንዳይበጠስ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ነው። ጭራቅ አሕመድን አሁን ላይ የሚመክረው፣ የስልጣኑ ዋና ተቀናቃኝ በሆነው ባማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን የጭፍጨፋ ዘመቻ ይበልጥ አጠናክሮ፣ መጨፍጨፍ የሚችለውን ያህል እየጨፈጨፈ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ማርዘም የሚችለውን ያህል እንዲያረዝም ነው።

ፋኖ ወደ ዐራት ኪሎ ሲቃረብ ዳንኤል ክብረት ጭራቅ አሕመድን የሚመክረው ደግሞ የራሺያ ቀይ ጦር (red army) ወደ ራይክስታግ (Reichstag) ሲቃረብ ዮሴፍ ጎቤልስ አዶልፍ ሂትለርን የመከረውን ምክር ዓይነት ነው።  የዳንኤል ክብረት ብቸኛ ክብሩና ጌጡ ጭራቅ አሕመድ በመሆኑ ሳቢያ የጭራቅ አሕመድ በማናቸውም መንገድ መዋረድ የሱ መዋረድ ስለሆነ፣ ጭራቅ አሕመድ ሙቶም ቢሆን ሬሳው እንዲዋረድበት አይፈልግም።  ስለዚህም፣ ለጭራቅ አሕመድ ባፅንኦት የሚመክረው፣ የመጨረሻው ሰዓት ሲደርስ ራሱን በራሱ እንዲገድልና ሬሳውን ደግሞ እሱ (ማለትም ዳንኤል ክብረት) በቤንዚን አቃጥሎ ደብዛውን እንዲያጠፋውና፣ ጭራቅ አሕመድ አልሞተም፣ የዳንኤል ክብረት እየሱስ አርጓል ተብሎ እንዲወራ ነው።

የመጨረሻው ሰዓት እስከሚደረስ ድረስ ግን፣ ጭራቅ አሕመድ በዳንኤል ክብረት ምክር መሠረት ባለ በሌለ ኃይሉ አማራን መጨፍጨፉን ይቀጥላል።  ስለዚህም ፋኖ አማራን መታደግ የሚችለው የመጨረሻውን ሰዓት በተቻለው መጠን በማፋጠን ነው።  አልበለዚያ ይዘገያል፣ ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኸ ይሆናል።

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop