September 1, 2023
4 mins read

የጭራቅ አሕመድ ግርምቢጥ፤ ለመደራደር አልደራደርም ማለት

Abiy is a killer eጭራቅ አሕመድ አረመኔ ብቻ ሳይሆን በግርምቢጥ (በተቃራኒ) የሚናገር ግርምቢጣም ነው።  ኢትዮጵያ አትፈርስም እያለ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከጫፍ አድርሷታል፣ ሳናጣራ አናስርም እያለ አማሮችን በገፍ አስሮ ይቶርቻል (ቶርቸር ያደርጋል)፣ መግደል መሸነፍ ነው እያል፣ አማራን ገድሎ ሊያሸንፍ ቆርጦ ተነስቷል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ አስር አለቃ ብርሃኑ ጁላና መሰሎቹ ከፋኖ ጋር እንደራደር የሚል ሐሳብ ሲያቀርቡለት፣ አሻፈረኝ ብሏል የሚል ዜና እንዲሰራጭለት አድርጓል።  የዚህ ዜና ዓላማ ግን የዜናውን ግርምቢጥ (ተቃራኒ) ነው።  ጭራቅ አሕመድ አልደራደረም ብሏል ተብሎ እንዲነገርለት የፈለገው ለመደራደር ስለፈለገ ብቻ ነው

በመጀመርያ ደረጃ ጭራቅ አሕመድ በዙርያው ያሰባሰባቸው ሰው ተብየወች ከሱ ተቃራኒ የሆነ ሐሳብ ማቅረብ ይቅርና ፊቱን ማየት የሚፈሩ፣ የስካርና የነውር እስረኞች የሆኑ፣ ጭራቅ አሕመድ ወተቱን ጥቁር ካለ ጥቁር የሚሉ፣ አልፈው ተርፈውም ጭራቅ አሕመድ እየሱስ ነው የሚሉ፣ ሁለመናቸውን በጭራቅ አሕመድ የተሰለቡ ጃንደረባወች ናቸው።  ስለዚህም እሱ አልደራደርም እያለ የጭን ገረዶቹ እነ ብርሃኑ ጁላና ተመስገን ጡሩነህ እንደራደር ሊሉት አይደፍሩም።  ስለዚህም፣ ጭራቅ አሕመድ አልደራደርም የሚለው ፋኖን ለድርድር ለማግባባት ሲል ብቻ ነው።

ጭራቅ አሕመድ መደራደር የሚፈልገው ደግሞ ሊሸነፍ መሆኑን ሲረዳ ብቻ ነው።  የሚደራደረው ደግሞ ሰጥቶ በመቀበል ለመስማማት ብሎ ሳይሆን፣ ሊያሽንፈው የተቃረበውን ኃይል በድርድር ሰበብ እየተለማመጠ ካዘናጋ በኋላ ድባቅ ለመምታት ሲል ብቻ ነው። ስለዚህም ማናቸውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደረደራለሁ ብሎ የተነሳ ቀን፣ ቀብሩን መማስ መጀመሩን ሊያውቅ ይገባል።

በተለይም ደግሞ ፋኖ ሆይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደራደራለሁ ብልህ የተነሳህ ቀን፣ ቀብርህን መማስ መጀመርህን እወቀው።  ያማራ ሕልውና ትግል አመራሮች እውነትም የሚታገሉት ላማራ ሕልውና ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁለት ቅድመሁኔታወች (preconditions) ባላስቀመጠ በማናቸውም ድርድር ውስጥ አንገታቸው ቢቆረጥ መሳተፍ የለባቸውም።  የመጀመርያው የድርድር ቅድመሁኔታ የጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግሥት ሙሉ በሙሉ መገርሰስና ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው የድርድር ቅድመሁኔታ ደግሞ ጭራቅ አሕመድና ግብራበሮቹ (በተለይም ደግሞ ደመቀ መኮንንተመስግን ጡሩነህስማ ጡሩነህአበባው ታደሰይልቃል ከፋለ እና የመሳሰሉት ብአዴናዊ ግብራበሮቹ) ባማራ ሕዝብ ላይ ለፈፀሙት ወንጀል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ዘላለማዊ መቀጣጫ መሆን ነው።

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

Go toTop