August 31, 2023
1 min read

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዩንቨርስቲው ቻንስለር ሆነው ተሹመዋል

abiy ahme Akatariwech 1 1
ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ቴሌኮም ወና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።
abiy ahme Akatariwech 1 1የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።
ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ሹመት ማግኘታቸውም ተገልጿል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ዓም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም ፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ  ተናግረዋል።
Geletaw
_._,_._,_

5 Comments

  1. ለዘሀበሳ አዘጋጆች፦
    ለአቶ አልዩ፦
    በዚህ በተከበረ ድረ ገጽ ላይ በዚህ ወቅት ይህ ወሬ በዘሀበሻ ድረ ገጽ ላይ የሚወጣ ዜና ነውን?
    ለምን አብይ አህመድ ልሳን የሆነው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አትሆኑም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ውርደታችሁን አየን፡፡
    ገለታው የተባለ ገለታቢስ የላከላችሁን የገዥው የኦሮሙማ ዜና ያውም የሁለት እጅግ አሳፋሪ ሰወች ( ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩና የዶ/ር ብርሀኑ ነጋ) ሹመትለዘሀበሻ ዜና አድርጎ ማቅረቡ ድፍረት ንቀት ነው፡፡
    ታ ሳ ፍ ራ ላ ች ሁ !!!!!

  2. እንደሚመስለኝ ብርሃኑ ነጋ ተደጋግሞ እንደታየው ኢንተግሪቲ የሚባል ነገር ስለሌለው ወደ ዩኒቨርስቲ የተወስደው የአቶ አብይን የተጭበረበረ ዲፕሎማ በዚህም በዚያም ብሎ ዶፍቶር ለማሰኘት ነው እመኑኝ። ሰውየው ህልውናው አብይ ጋር የተያያዘ በመሆኑ አብይ ላይ የሚወረወረው ፍላጻ አስቀድሞ እሱ ላይ ማረፉ የማይቀር ነው ሆዱን ወዷልና ይቀበለው።

  3. ካሳሁን የብርሃኑን ሹመት እንኳን ደስ አለን ሊሉ ፈልገው ሳይሆን ላደረገው አጎብዳጅነት አብይ የሸለመውን እንድናውቀው ፈልገው መሰለን አልዩ ደህና አገር ወዳድ እንደሆነ የምናውቅ እናውቃለን ይህ ይሉኝታ የሌለው ግለሰብ ከህዝብ አእምሮ እንዳይጠፋ እየደጋገመ ሲወጣ ተንኮሉንም አብረን እናስታውሳለን። እንዲህ ቶሎ ቶሎ ውርደቱን ካላየን በምን እንወቀው? እንደው ስህተትም ቢኖር በውስጥ መስመር መወቃቀስ ለትግሉ ይበጃል እላለሁ ጭንቀትህ ይገባኛል በርታ።

  4. አይ ሃበሻ ሁልጊዜ አይንህን ላፈር እንጂ ለምን እንዴት ብሎ መጠየቅ የለም። ዘሃበሻ የመሰለውን ዜናና እይታ ለመለጠፍ መብቱ ነው። ድህረ ገጽን መስደብ፤ ሰውን በስም ጠርቶ ማጣጣል የማይለቅ የሃበሻ የድንጋይ ውርወራ ፓለቲካ ነው። በሃገሪቱ የሚወርደው የመከራ ዶፍ ወዴት እንደሚወስደን ባለመገመት ያዘው፤ ጥለፈው፤ በለው እያልን ከሩቅ ሆነን ህዝባችን በዚህም በዚያም እንዲገዳደል በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የምትረድ ሁሉ ቆም ብላችሁ ልታስቡ ይገባል። ለወያኔ የስመ ነጻነት ውጊያና ለ 3 ጊዜ ወረራው የአንገታቸውን ሃብልና የእጅ ቀለበት ለድርጅቱ የሰጡ ዛሬ ላይ በህይወት ያሉ ምንኛ ይቆጫቸው ይሆን? የሃበሻ ፓለቲካ ውሃ ወቀጣ ነው። እንቦጭ። የማይደቅ ነገር ላይ ጉልበት ማፍሰስ። የብርሃኑ ነጋም ሆነ የወ/ሪት ፍሬህይወት ሹመት ያዙኝ ልቀቁኝ የሚያሰኝ አይደለም። ዶ/ር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስቴር ከሆነ ወዲህ የትምህርቱን ጥራት ለማሻሻል የደረገውና የሚያደርገው ተግባር ሁሉ መልካም ነው። ወ/ሪት ፍሬህይወትም በመስኳ ምስጉን ናት። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ስልጣን ቢሰጣቸው ምን ችግር አለበት። ግን እሳቤአችን ሁሉ ለዛሬ፤ ኑሮአችን ለአሁን፤ እይታችን በዘርና በሃረግ እንዲሁም ወንዝ በማይሻግር የቋንቋ ቋቋታ ተገን ያደረገ በመሆኑ እውነቱን ለማየት ይሳነናል። ይህ ሲባል ሰው ሆኖ እንኳን በስልጣን ላይ ያለ ይቅርና ተራው ኗሪም ስህተት ይሰራል፤ ይታረማል፤ ይማራል። ስለሆነም የሃገሪቱን የፓለቲካ እይታ ለመቀየርና ህዝባችን ህሳቤው ሰዋዊ እንዲሆን ከተፈለገ ዘመቻው ከራስ ነው ነው መጀመር ያለበት። በተገኘው የውሸት ወሬ እየሰከሩ በዚህም በዚያም ሰውን በጭፍን መጥላት፤ ህዝብን በወል መስደብ፤ የሌለ ስም እየሰጡ ሰው ያለስሙ ስም እየሰጡ ጭቃ መቀባት ከጥቅሙ አፍራሽነቱ የጎላ ነው። ስለሆነም የሁለቱን ሹመት ካለፈ የሥራ ስኬታቸው በመነሣት ይህ አዲሱ ሃላፊነታቸውም የምድሪቱን ህዝብ ለማገልገል በሙሉ ጉልበታቸውና እውቀታቸው ለመወጣት ጊዜው የሰላምና የጤና እንዲሆንላቸው እመኛለሁ። ሌላው ሁሉ ጫጫታ “ወ ቀጣፊ ይደልዎ ጥፊ” እንዲሉ ነው። በቃኝ!

  5. Well, it is fair to say that as long as this generation keeps terribly failing over and over and over again to make a difference that should lead to the emergence a real democratic political , social, economic, etc system, not only this but also the generation to come will suffer a lot !

    Imagine guys how a totally self- dehumanized persons such as this so called professorBerhanu Nega could be an asset for making the higher education institutions independent and self sufficient ???

    Imagine guys how persons l like this guy who have remained the very loyal ruling elites of Abyi Ahmed when millions of innocent people have been killed and victims of untold sufferings???

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Amhara
Previous Story

በሰሞኑ የፋኖዎችን አስደማሚ ድሎች – ዐማራ ሕዝብ ድርጅት

Abiy is a killer e
Next Story

የጭራቅ አሕመድ ግርምቢጥ፤ ለመደራደር አልደራደርም ማለት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop