July 12, 2023
5 mins read

ጭራቅ አሕመድ ሆይ እርምህን አውጣ፣ የመዋጋት አለመዋጋት ምርጫ ያንተ ሳይሆን ያማራ ሕዝብ ሁኗል

አለባብሰው ቢያርሱ፣ ባረም ይመለሱ።

Abiy Ahmed
#image_title

ጦርነት የሚጀመረው በምርጫ ቢሆንም፣ የሚፈጸመው ግን በግዴታ ነው።  በሌላ አባባል፣ ጦርነትን ለመጀመር ውሳኔው የጀማሪው ብቻ ቢሆንም፣ ለማቆም ግን ውሳኔው የተፋላሚውም ጭምር ነው።  ጭራቅ አሕመድ ግን ኮለኔል ነኝ ቢልም፣ ይህን መሠረታዊ ሐቅ አያውቅም።  አለማወቁ ደግሞ አያስገርምም፣ በወያኔ ዘመን ለኮለኔልነት የበቃው በወታደራዊ ክሂሎቱ ሳይሆን ባማራ ጥላቻው ነበርና።

ጭራቅ አሕመድ ባማራ ሕዝብ ላይ ያልታወጀ ጦርነት (undeclared war) ከፍቶ በሸዋ፣ በወለጋና በመተከል በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አማሮችን አርዶና አሳርዶ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን አፈናቀሏል።  ይህ ሁሉ ስላላረካው ደግሞ ይፋ ጦርነት አውጆ ባማራ ክልል ላይ ዘምቷል።  ባማራ ክልል ላይ የከፈተው ይፋ ጦርነት ግን እንዳሰበው ስላልሄደለት፣ በጃንደረባው በብርሃኑ ጁላ አማካኝነት ከፋኖ ጋር መዋጋት አንፈልግም ብሎ አስነግሯል።

በሌላ አባባል፣ ጭራቅ አሕመድ ባማራ ሕዝብ ላይ ሲያሰኘው የከፈተውን ጦርነት ሲያሰኘው ለማቆም ወይም ለመተገግ (ተግ ለማድረግ፣ pause) ፈለጓል።  ጦርነቱ ሊቆም ወይም ሊተግግ የሚችለው ግን በጭራቅ አሕመድ ፈቃድ ሳይሆን ባማራ ሕዝብ ፈቃድ ነው።   ያማራ ሕዝብ ደግሞ የሕልውና ጠላቶቹን ወያኔንና ኦነግን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሳያስወግድ በፊት ጦርነቱን ማቆም ቀርቶ መተገግ የለበትም።  አለበለዚያ ትርፉ የሕልውና ጠላቶቹ ይበልጥ እንዲጠናክሩ ዕድል ሰጥቶ መከራውን ይበልጥ ማክፋት ነው።  አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዲሉ፣ የውሃ ቀዳ፣ ውሃ መልስ ጦርነት ያማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ መጥፋት ይበልጥ ያፋጥነዋል።

ጭራቅ አሕመድ የከፈተው ጦርነት መደምደም ያለበት ያማራ ሕዝብ ወያኔና ኦነግን ሲያጠፋ፣ ወይም ደግሞ ወያኔና ኦነግ ያማራን ሕዝብ ሲያጠፉ ብቻ ነው።  የጦርነቱ ሁኔታወች በግልጽ እያሳዩ ያሉት ደግሞ በለኮሱት እሳት የሚለበለቡት ወያኔና ኦነግ እንደሆኑ ነው፣ ሎጋው ሽቦዬ፣ ሎጋው ሽቦዬ፣ የጫረው እሳት ሲፈጀው ታዬ፣ እንዳለ ከያኒ (artist) ካሳ ተሰማ።  ማናቸውም የጦርነት ጀማሪ ጦርነቱን የጀመረበትን ዓላማ ሳያሳካ ጦርነቱን ለማቆም ዳር፣ ዳር የሚለው እየተሸነፈ መሆኑን ሲገነዘብ ብቻ ነው።

ስለዚህም፣ ያማራ ሕዝብ ወያኔንና ኦነግን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት የሚያደርገውን ያልሞት ባይ ተጋዳይ ጦርነት ከግቡ ሳያደርስ በፊት የሚያስቆሙ ወይም ለማስቆም የሚሞከሩ ሁሉ ያማራ የሕልውና ጠላቶች ናቸው።  በተለይም ደግሞ ካሁን በኋላ ከጭራቅ አሕመድ ጋር በድርድርም ሆን በሽምግልና እታረቃለሁ የሚል ፋኖም ሆነ የፋኖ አመራር፣ ባንዳ ተብሎ፣ ከወያኔና ከኦነግ ጋር ተጨምሮ አብሮ መወቀጥ አለበት።

ትግሉ መነሻው አማራ መዳረሻው ጦቢያ ነው።  ያማራና የጦቢያ ሕልውና ለዘላለም የሚረጋገጠው ደግሞ የሁለቱም የሕልውና ጠላቶች ወያኔና ኦነግ ሙተው ተቀብረው ለዘላለም ሲወገዱ ብቻ ነው

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

Go toTop