በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
እንደ አያቶቻችን ታሪክ ቢሆንማ አማራና ባንዳ አብረው ተጦማር መጻፍ የማይችሉ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ስምንተኛው ሺ ደረሰና የአማራ እናት የወለደችህ አንተ ባንዳው የዘር ሰንሰለት ለውጥ (ጂን ሙቴሽን) አድርገህ “የአማራ ባንዳ” የሚል ሐረግ እንዲፈጠር አደረክ፡፡ እንደ ይሁዳ ያለን ከሀዲ እማይወደው እግዜር ይይልህ!!!
እናም ይድረስ ለአንተ ለአማራው ባንዳ! አንተን ነው! ለምን ያልሰማ ያላዬ መስለህ ታልፋለህ!
አዎ አንተን ነው! አማራንና ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ለማጥፋት እቅድ ሲያወጡ ከርስ በሚባል እሳት ልብህንና አሞትህን እንደ ብረት አቅልጠው መጀመርያ ኢህዴን፣ ቀጥሎ ብአዴን፣ ተዚያም አዴፓና ቅብጥሶ የሚባል የአማራ እግር ብረት የሰሩህ!
አዎ አንተን ነው! በሆድህ እየገዙ የእነሱ ሰላይ፣ ካድሬ፣ ለፍላፊ ዜና አንባቢና ጋዜጠኛ፣ ዘበኛ፣ ዘፋኛ፣ እንደራሴ፣ ሚኒስቴር ወዘተርፈ ያደረጉህ!
አዎ አንተን ነው! ለአርባ አምስት ዓመታት አማራ ዘሩ እየተመረጠ ሲጨረገድ በመላው ዓለም ሆድህን እንደ ቅንቡርስ እየሞላህ በዝምታ ዘር አጥፊዎቹን የደገፍክ!
አዎ አንተን ነው! የአማራን ከምድር መጥፋት ለመከላከል ህይወቱን እየገብረ ያለውን ፋኖ ያጥላላህና እንደ ይሁዳ አሳልፈህ የሰጠህ!
አዎ አንተን ነው! ተአማራ ሺል ወጥተህ አማራን ለማጥፋት ቆርጠነው ለተነሱት በወታደርነትና በፖሊስነት በማገልገል ላይ ላለህ!
እባክህ! እባክህ! በኣያት በቅደመ አያቶቻችን ነፍስ ይዘንሃል ባንዳነት ይብቃህ!
እባክህ! እባክህ! የአርበኛ አያቶቻችን ድምፅ ተመቃብር ውስጥ ይሰማህ፡፡
እባክህ! እባክህ! በአድዋና በአምስቱ ዘመን ለነጻነት የወደቁት ፋኖች አጥንት ሲወጋህ ይሰማህ! እባክህ! እባክህ የባንዳ የልጅ ልጆች አሽከር መሆኑ ያሸማቅህ!
ባንዳ ሆይ! ነገ ሞተህ ምስጥ አፈር ሊያደርግህ እባክህ የምሳር ዛቢያ ሆነህ ሕዝብህን እያስጨፈጨፍክ መኖር ይብቃህ!
ባንዳ ሆይ አገርህን፣ ነፃነትህንና ክብርህን ለማሰጠበቅ ለሶስት ሺህ ዘመናት ደማቸውን እንደ ዓባይ ፏፏቴ ያፈሰሱት ተወዳዳሪ የሌላቸው ጀግኖች ቅድመ አያቶችህ ነፍስ ከሰማይ ቤት ሲገስጽህ ይሰማህ!
ባንዳ ሆይ! ይብቃህ! ይብቃህ!
ባንዳ ሆይ ተቀላቀል ተወገንህ ለሰራሃው ሀጥያትህ ንስሃ ገብተህ!
የበቃህን እግዜር ይርዳህ! አሜን፡፡
ሐምሌ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.