ሕዝብ ሆይ! – በላይነህ አባተ

/
#image_title

ሕዝብ ሆይ!

ጅቡ ሲመጣ አፍጦ በአውሬ ባህሪው ሊገምጥህ፣
እንደ አምናው ተዛሬ ነገ ሰውን ይሆናል ብለህ ተጠበክ፣
እንደ ታች አምናው ዘንድሮም ዳግም ቂል ተሆንክ፣
የራስህ አጥፊው ጅብ ሳይሆን አንተው ራስህ ሕዝብ ነህ!

ሕዝብ ሆይ!

ከተቀደሰው ቤተክርስትያን ከምትሰግድበት መስጊድህ፣
እርኩስ ጅብ ገብቶ እየጎመደ ሲበላህ ሲያረክስህ፣
ያላዬ መስለህ ተተኛህ እጅህን አጣጥፈህ ቁጭ ታልክ፣
እንኳንስ ይህ ከንቱ ምድር እግዜር ያለበት ሰማይም አይረዳህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

እርዳኝ እረድሃለሁ ያለውን ትእዛዙን ሕጎቹን ቦጫጭቀህ፣
ጅብ ተቤተ መቅደስ ደም ሲያፈስና ሲጠጣ ዝም ታልክ፣
በአምሳሌ ሰርቸዋለሁ ያለውን ፍጥረቱን መቼ ሆንክ?

ሕዝብ ሆይ!

አሞት አልቦ ጅብ ግራ እግር ጎርሶ ሲውጥህ እያየህ፣
“ቀኜን እንዳይደግም ዝም በል” የሚል ጡርቂ አመል ታሳየህ፣
ልብ አድርግ ለቀብር የሚሆን እራፊ ገላም አይተርፍህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

ጅብና ውሻ ፈሪ እንደማይለቅ እያወክ፣
ወግድ ክላልኝ የሚልን እንደማይነካ ዘንግተህ፣
ፊትለፊት እንደመጋጠም ለመሸሽ ከተፈተለክ፣
እንኳንስ የአንተ የልጅ ልጅህም ታፋው አይተርፍህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

ጅብ ተጠራርቶ ሊጎርስህ በሁሉ አቅጣጫ ሲከብህ፣
አካሎችህን አንድ አርገህ በጥኑ ወኔ መፋለም ሲገባህ፣
የግራ የቀኝ እጅህን አጋጭተህ ክንድ ማስለሉን ተቀጠልክ፣
እንኳን ቀን የሰጠው ጅብ ጆፌ አሞራውም አይምርህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

እንደ ቅደም አያቶችህ አንድ ላይ ሆነህ መፋለም ሲገባህ፣
በጎጥ በመንደር እየጮህክ እርስ በራስህ መናከስ ተጀመርክ፣
ማለቅህን እወቅ በጅቦች የከረፋ አፍ ተራ በተራ ተውጠህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

የቀን ጅብ ተዱሩ ወጥቶ ሊውጥህ አምቧትሮ ሳለ፣
ቀኝ እግርህ ግራውን በተንኮል ጠልፎ ተጣለ፣
ለራስህ የከፋ ጠላት ያለ አንተው ሌላ ማን አለ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለማመን የሚከብዱ - ዓባይነህ ካሤ

ሕዝብ ሆይ!

ቀኑ የጅቦች መሆኑን በእዝነ ልቡናህ አጥንተህ፣
ቀኝ ክንድን በጡንቻህ ተግራው ጋራ አጣምረህ፣
ግራ እግርን ተቀኙ እንደ ብረት ከንች አምቧትረህ፣
ህልውናህን አረጋግጥ እንደ ታሪክህ በትግልህ፡፡

ሕዝብ ሆይ!

ዘመኑ የጅቦች መሆኑን በአይምሮ ልብህ አጢነህ፣
የአያትን ክብሮች አስጠብቅ ክንድ መንፈስክን አንድ አርገህ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ግንቦት ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.

 

 

1 Comment

  1. ዛሬ አደገኛው ሰው በላው ጭራቅ ኦናግ ና ብልጽግና በወያኔ የተጀመረውን ኢትዮጵያን እንደ ሶማሊያ መበተን እንደ ሩዋንዳ እርስ በርስ ጦርነት እንዲሁም እስልምና ክርስቲያን ሀይማኖት አጥፍተው በጴንጤ ለመተካት ሥልጣኑን ለማጠናከር አማራን ከትግራይ አጋጭቶ ዛሬ አማራን በማጥፋት የቤት ሥራ ጀምረዋል እንዲሁም ስሞኑን ህዝቡን በአስከፊ ና ተስፋ አስቆራጭ ኑሮ ውድነት ከጠመዱ በኋላ መዝጊዶችን ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን ማፍረስን ምዕመናን በጅምላ መጨፍጨፍ የኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ መዝረፍ ማፈናቀል ምዕራባውያን መንግሥታት ና የምዕራባውን የብዙሃን መገናኛ ዝምታን ለሴራው ና ኢትዮጵያን ለመበተን ለአብይ ድጋፍ እንዳላቸው ትልቅ ማስረጃ ነው የኢትዮጵያ እነዚህ ስው በላ ጭራቆች እምነታቸው በጦር መሳራያ ሃይል ና የምዕራባውን ድጋፍ ሥለሆነ ሕዝብ ነቅቶ እነዚህን ጠባብ ዘረኞችን በአንድነት ማጥፋት አለበት ።
    በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዲያስፖራ ባንኮች በኩል የምላክ ሀዋላ ገንዘብ አቁሞ በግልሠቦች በኩል መላክ ።
    የጭራቆችን መከላከያን ለማዳከም ሽምቅና ደፈጣ ውጊያን የነሱን ባንዳዎችን በሁሉም ቦታ መግደል ።
    ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር በሃይማኖት ሳይከፉፈል በአንድነት በጣልያን ፋሺሽት ጣሊያኒን ላይ ያስመዘገበው ታሪክ ዛሬም በዘረኞች ጭራቆች መድገም አለበት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share