June 3, 2023
11 mins read

ዉሻ  በበላበት ይጮኃል

rttttyyyyy 1 1
#image_title

rttttyyyyy 1 1

በዓለማችን መስማት የተሳነዉ ስብስብ ድርጂት እና ለዚህም አጨብጫቢ የማይነሳዉ  ነገር ግን እንደ አለመታደል በአድር ባይነት ሳይሰሙ እና ሳይረዱ በሚስማሙት ከድንቁርና ወደ ድንቁርና እንዲረማመዱ በጥቅም እና በከንቱ ዉዳሴ እንዲሰክር የሆነዉ ብቸኛዉ የፖለቲካ ድርጂት ኢህአዴግ ነዉ ፡፡

ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር በመላ አገሪቷ ለፈፀማቸዉ  ዕኩይ እና እድር ባይ ብሄራዊ ወንጀል እና ክህደት ምንም አይነት  ጥፋት ፣የሰዉ ልጆች ሞት ፣ዕልቂት ፣ስደት ፣ድህነት …መስማት እንዳይችል ያደረገዉ ወንጀል እና ኃጢያት ዋና ባህሪዉ ሆኖ ከመለማመዱ በላይ ትክክል እንደነበር እና እንደሆነ ከማመኑ በላይ የአደንቋሪዎች ጭብጨባ ባዶነቱን እንዳያይ በማድረግ ህጋዊ እንደሆነ በማድረግ ድጋፍ ቸሮታል ፡፡

በፖለቲካ ስያሜ እና የንግግር መደጋገም የከንቱ ዉዳሴ ጋጋታ በአድር ባይ ተቋማት ጫጫታ እና ይሁንታ ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የመስማት ብቻ ሳይሆን ከራሰ ጋር ያለመስማማት የጥላቻ እና የምቀኝነት  መንፈስ እያለባቸዉ መጥቶ በበደል ላይ በደልን በኢትዮጵያ እና ህዝብ ላይ ዙሩን እየጨመሩ ነዉ ፡፡

ከመስማት ችግር  አጥፍቶ ወደ መጥፋት የዉስጥ ተቃርኖ የገባዉ የአገራችን ፖለቲካ በኢህአዴግ ፊዉታራሪነት በአደንቋሪ ተከታይነት ጨለማዉን ብርኃን፤ ድንቁረና እና ድህነት ስልጣኔ ፣ ወደ ኋላ መቅረት ወደ ፊት መራመድ ፣ ህዝብን ማስጨነቅ እና ማሸበር ኅግ ማስከበር…. በሚል በራሳቸዉ መዝገበ ቃላት እየተረጎሙ እነሱ የሚፈልጉትን እንዲሰሙ ሲደክሙ ይስተዋላል ፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ  ከአዉቅላችኋለሁ እኔን ብቻ ከሚል ከነጠላ ዉድድር ወጥቶ ህዝብን እና አገርን ወደ መስማት እና ሰምቶም ወደ አገልጋይነት አስካልመጣ እኔን ስሙኝ ፤ ዕመኑኝ ፤ተከተሉኝ ድንቁረና የማስተላለፍ በማይሰማ ጆሮ በሀሰት በተጀቦነ አንደበት መሰለቻቸት ነዉ ፡፡

ነፃነት በሌለበት መናገር የማደንቆር ተግባር መሆኑን በተደጋጋሚ ንግግር ወይም ስሙኝ ባይነት የተሰላቸ ህዝብ የሚሰማዉን እና የሚገባዉን ሀሳብ መግለፅ ጥፋተኝነት በሚየደርገዉ የሌሎችን መብት እና ነፃነት በማይቀበል ስሙኝ እመኑኝ  ለአገር እና ለህዝብ ከመታመን ይልቅ በባርነት እና በግዞት መገልገል ምኞት የሚያስከትለዉ የፖለቲካ ንግድ በሚገኝ ሥልጣን እና ንዋይ ልክፍት መፍዘዝ ነዉ ፡፡

በግልም ሆነ በፐለቲካ ማህበር እንደ ኢህአዴግ የእድሜ ልክ የፖለቲካ ስልጣን ጉልተኞች ከእኛ በቀር ሌላ አትስሙ እና አትቀበሉ ማለት በዚህ ዘመን እንደ አሸን መፍላቱ ቢያስተዛዝብም ኢትዮጵያዊ እና ሠዉ የሆነ ሁሉ ዛሬም እንደ ትናንቱ የሚበጀዉን እና የሚመርጠዉን የሚያዉቅ አለመሆኑ መታወቅ አለበት ፡፡

በላቀ አስተሳሰብ እና ብሄራዌ ቁመና የሚመጡትን ህዝባዊ አደረጃጀቶች እና መሪዎችን ማጥላላትም ከባዶነት እና ግለኛ ምኞት ከሚመነጭ ስጋት የሚፈጠር ነዉ ፡፡

ኢህአዴግ እና በማደናቆር ፖለቲካ ከዳሚዎች ዛሬም እኛን ስሙን ተከተሉን ሲሉ በነበሩበት የጉለተኛ ፖለቲካ ዘመን ፡

ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ተስምቶም ፤ሆኖም በማያዉቅ ሁኔታ ፡-

ከአምስት ሽ ዓመታት የታላቅነት ማማ ወደ ዉርደት ቁልቁለት ስትምዘገዘግ ዝም በማለት  ወይም ከማጨብጨብ ዉጭ ምን ሰሩ ፤

ኢትዮጵያ የባህር በር ከነበሯቸዉ አገራት አንዷ የነበረች ቢሆንም ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለመጉዳት ሲባል የነበራትን ስታጣ ማን ምን አደረገ ቀርቶ ከማጨብጨብ ምን አለ ፣

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፤ዘመናዊ እና ህዝባዊ ሠራዊት በግፍ እና በጥላቻ ተበትኖ የፖለቲካ ድርጂት እና ግለሰብ ጠባቂ ኃይል ሲቋቋም እንዴት ያለ ማን አለ ፣

የኢትዮጵያ ህዝብ በራሱ እና በአገሩ ላይ እንዳይነጋገር እና እንዳይወስን ጨቋኝ እና ተጨቋኝ በሚል መደብ አባር እና ገባር ሆኖ በአገሩ ሁለንተናዊ ጉዳይ ባይተዋር ሲሆን ማን ምን አለ…….

ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኘት ወይም ኢትዮጵያ ማለት የማርያም ጠላት በተባለባት አገር ምን ሰራችሁ ….እነ ሆዴ ዘመዴ..

የዓማራ ህዝብ በመላ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነቱ ፣ በማንነቱ ፣በዕምነቱ  እና ሠዉ በመሆኑ ለድፍን ሶስት አሰርተ ዓመታት የጂምላ ዘር ፍጂት ፣ ስደት ፣ መፈናቀል ፤ በሁሉም መገለል …የመከራ ቋጥኝ ሲከመርበት ምን ..ማን…

ትናንት የብሄራዊ መብት እና የመኖር ነፃነት የፖለቲካ ጥያቄ በሚያነሱት ዛሬ ግን በዕምነት ተቋማት በግለጭ ለሚደረግ ጥቃት እና ጥፋት ምንም አለማለት….ከጥፋት ትብብር የሚለይ ይሆናል ወይ ….

እና ለምን ይሁን የግዑዝ አስተሳሰብ በተመረዘ አመለካከት ወደ ፊት ከመራመድ ይልቅ መንገድ ላይ በመቆም የአገሪቷን እና ህዝቧን የወደፊት ጉዞ በማስተጓጎል የሄደ በሚመስል ጨለምተኛ ጉዞ እኛን ተከተሉኝ በማለት ማደናቆር ቢቀር እና የትፋት ጉዞዉ ቢቋ

 

ሠላሳ ዓመት ከዉድቀት ወደ ሞት ፣ በጭጋግ ወደ ድቅድቅ ጭለማ ፣ ከአንድነት ወደ መለያየት ፤ ቀምሶ ከማደር ፤ ተርቦ ወደ መኖር፣ ከብሄራዊ አንድነት ወደ መለያየት፤ ከባህር በር ወደ  ደረቅ ምድር እንድንወድቅ ላደረገን በኢህአዴግ ፊት መሪ እና ፊታዉራሪ ከዚህ በላይ የምንሰማዉ ሆነ የምንሸከመዉ መከራ ምን ይሆናል ተብሎ ነዉ ስሙኝ ተከተሉኝ እያሉ በጥፋት ጎዳና መንጎድ ፡፡

አገር ሲናድ ዝም ፤ ዜጎች በግፍ እና በገፍ ሲገደሉ ዝም፣ የዕምነት ተቋማት ሲደፈሩ ዝም ፤ ዜጎች በድህነት እና በስደት ዜጎች ሲዋረዱ ዝምታን የመረጠ ዛሬ በተገፉ የቁርጥ ቀን ጀግኖች ጥላ ስር የተገፋ ህዝብ ወደ አንድነት ሲመጣ የመጪዉን ጊዜ የነፃነት እና የህልዉና መንገድ አቅጣጫ እና መሪ ልመርጡለት የሚዳዳቸዉ በለመዱት ዝም ቢሉ ከተጨማሪ ጥፋት እና ፀፀት መታቀብ ይገባል  ፡፡

ዜጎች ሠዉ በመሆናቸዉ እና በዜግነታቸዉ በአገራቸዉ ባይተዋር ሆነዉ ከሠዉነት በታች ሆነዉ ቢፈረጁባት አገር ከመሞት መሰንበት ብለዉ የሚስማማቸዉን እና የሚሆናቸዉን  ፍኖተ ትግል- ህልዉና  “ፍትህ ” እንዲከተሉ ለራሳቸዉ መተዉ ፍትኃዊነት ሲሆን ከዚህ ዉጭ በዜጎች የዘመናት መከራ እና ሞት በራስ ወዳድነት የራስን የስልጣን እና ቁሳዊ  ጥቅም ለማስቀጠል አገርን እና ህዝብን በባርነት እንደመገልገል ይቆጠራል፡፡

ሆኖም እንደ ዉሻ ለምንበላዉ ስንጮህ ጊዜዉ አልፎ በታሪክ እና በትዉልድ ተወቃሾች እንዳንሆን ስለ ሆዳችን ሳይሆን ጌታችን ለሆኑት “አንዲት አገር እና ህዝብ ” ሊሆን ይገባል፡፡

ለህልዉና እና ለነጻነት የሚተጉ አካላትም የበግ ቆዳ በለበሱ ተኩላዎች የ፭ቱን በሬዎች ዕጣ እንዳይገጥማቸዉ ትብብር እና አንድነታቸዉን ከመቸዉም ጊዜ በላይ አጠንክረዉ ለራሳቸዉ ለአገራቸዉ የሚደረገዉን የትግል አንድነት በማፅናት በህዝብ እና አገር ላይ የወደቀዉን የመከራ ቋጥን ዘመን ለማሳጠር ተባብረዉ ማስተባበር ይኖርባቸዋል፡፡

 

ALLEN!

 

“አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡”

1 Comment

  1. ወዳጄ አትድከም ብአዴን በድን አድርገው ጠፍጥፈው የሰሩት ድርጅት ነው ከምንም በላይ ሹማምንቱ አረቄና ጥሬ ስጋ ከቀረበላቸው ከዛ አልፈው አይሄዱም አጋጣሚ ካገኙ ግን እንዳለፈው ብር በኬሻ አስይዘው ይሸሻሉ አንዱ ገበሬ አናታቸውን ብሎ እስኪቀማቸው። በተረፈ እንሱንና ብርሃኑ ነጋን መምከር ውሃ መውቀጥ ነው ቀጥሉበት ነው ማለት ያለብህ አገኘሁ ተሻገር ከወይጦነት ኦሮሞ ነኝ ብሎ ኦሮምኛ ማጥናት ጀምሯል እንዲህ ነው ብአዴን። አህመዲን ጀበል አቡበከር ምናምን ኡስታዞቹ መስኪድ በሌለበ የአማራ ክልል ተቃጠለብን ሸኑበት ብለው አገር ምድሩን ጤና ነስተው ኦሮሞ ሼህ አስመርጠው እራሳቸው ያለፍቃድ ያሰሩት መስኪድ በራሳቸው በነ አህመዲን ጀበል አቡበክር ምናምን ሲፈርስ አላይንም ብለዋል እንዲ ነው የቀጣፊ እምነትና ፖለቲካ።አንዱ ሸለምጥማጥ ሆኖ ያስቸገረው ሲሳይ መንግስቴ የሚባል ሰው ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy Ahmed
Previous Story

ሕዝብ ሆይ! – በላይነህ አባተ

National Army Amhara Special Force 1 1
Next Story

የሰንሹ የጦርነት ጥበብ ላማራ ሕዝባዊ ግንባር፤ ማጥቃት መከላከል ነው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop