ጉዳዩ በሐዋሳ ከተማ ከተከሰተ ሳምንት ያስቆጠረው የአንድ እንስት በከተማዋ ከንቲባ ጠባቂ ( ጋርድ) መጠለፏን እና በዚህም ቤተሰቦች ከፍተኛ ጨንቀት ዉስጥ መግባታቸውን ሰምቻለሁ።
የቅርብ ሰዎች
ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለው ግለሰብ በሁለት በመንግሥት ተሽከርካሪ መኪና ከስራ ገበታዋ ስትወጣ ጠልፈዋት ይዘዋት ከአከባቢው ተሰዉረዋል ፤ በምስዕሉ ላይ የተምትመለከቱት የባለስልጣኑ ጠባቂ ወደ ትዉልድ ቀዬው ሲያቀና “የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል”!
ዛሬ ነገ ድምጿን እንሰማለን በሚል በተሰፋ ሲጠባበቁ የነበሩት ቤተሰብ ከአጋች አንድ የስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል ” ልጃችሁ እኔዉ ጋር ነች በቅርቡ ሽማግሌ እልካለሁ በግዴታ ትቀበላላችሁ ” የሚል እንደነበር በግሌ ባደረጉት ማጣራት ለማወቅ ችያለሁ ።
ጉዳዩ በዚህ አያበቃም ፖሊስም ምላሽ ሰጥቷል።
እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ድርጊቱን የፈፀመውን ግለሰብ በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ እንዲሁም ከሐዋሳ አቅራቢያ ወደ ምትገኘዉ ሐገረ ሰላም ማቅናቱን አረጋግጠዋል ። ነገር ግን ከዉስጥ ለባለስልጣኑ ጠባቂ መረጃ ቀድሞ እየደረሰዉ በመሆኑ ፖሊስ ይገኝበታል ብሎ ያሰበበት ስፍራ ቢሰማራም ቦታ መቀየሩን ተናግሯል ። ይህም ስራዉን አክብዶብኛል ብሏል።
እንዲህ አይነት ድርጊት እንዴት ሊፈፀም ቻለ?
የልጅቱ መጥፋት ተደማምሮ በርካታ የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ ትኩረት ተደርጎበታል ነገር ግን ከየገጠር ወረዳዎች ይህ ነገር አሁንም ድረስ መኖሩ ለስራ አጋጣሚ ወደ ክልሉ ፖሊስ የሴቶችና ህፃናት ክፍል ባመራሁበት ወቅት አረጋግጫለሁ ።
የግል ጠባቂው ከዚህ ቀደም በልጅቷ ላይ የተለያዩ ማስፈራሪያ ዛቻዎችን የሚፈፅም ቢሆኑም እንዲህ ያደርጋል ብሎ የጠበቀ ማንም አልነበረም ይልቁኑ በቅርብ ልትሞሸር ሽር ጉድ እያለች ትገኝ ነበር።
ከመሬት ተሰነስቶ ሊያዉም በከተማው ፈፅሞ ሊደርግ የማይችል ድርጊት ሊፈፀም የቻለዉ እና በግልፅ ማንም ሲናገር ያልሰማሁት መረጃ ላካፍላችሁ ይህንንም ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ ግለሰብ ነዉ ቃል በቃል እንዲህ ብሎኛል …”ሁለቱም ትዉዉቅ አላቸዉ በግልፅ እንዲህ ነዉ የምለዉ ነገር ባይኖረኝም ከስራዋ ጋር የተያያዘ ነዉ፤ እሱ እንደሚወዳት በተደጋጋሚ ነግሯታል በስልክም ያወሩ ነበር ” ሲል ለጉዳዩ ቅርበት ያለዉ ሰዉ መረጃዉን አድርሶኛል።
አሁን ግን ቤተሰቦቿ በእጅጉ ተጨንቀዋል ይህ የከተማዋን ገፅታ ማበላሸት ነዉ የሚባለዉ ትርክት አይገባኝም ይሄ የሰዉነት ጉዳይ ነዉ.. ዛሬ በዚህች ልጅ የተፈጠረው ነገ በእኔ እህት እንደማየሰከሰት ማረጋገጫ የለኝም።
እንደሚሰማዉ ፖሊስ ከአቅሙ በላይ ሆኖበታል … ቀድሞ መረጃ እየደረሰዉ በመሆኑ ጠባቂዉን ለማግኘት አዳጋች አድርጎታል … ይሄ ፊልም የመሰለው ድርጊት ዝምታ ተመርጦ እስካሁን ምላሽ አለመሰጠቱ እርስበርሳቸው መፈራራት እንዳለባቸው ያሳብባል።
Eyasu Zekarias ከስፍራው