May 31, 2023
2 mins read

ተዋናይት ሜላት ዳዊት ከእስር እንድትፍታ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ይግባኝ ጠየቀ ! ( ይድነቃቸው ከበደ )

347419155 647743003457819 8163470114537388733 n 1 2

የፊልም ዳይሬክተር እና ተዋናይት ሜላት ዳዊት ፤ በዛሬው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. አስሯት የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንድትቀርብ አድርጓል ።

ፖሊስ ለባለፉት 7 ቀናት ፍርድ ቤት በሰጠው የምርመራ ቀናት ፣ ከዚህ ቀደም ይቀሩኛል የሚለውን የምርመራ ሂደት አጠናቆ እንዲቀርብ ጊዜ የተሰጠው ቢሆንም ፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 14 የምርምር ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል ።

melat 1 Copy 1

ሆኖም ግን ፤ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ቀናት በቂ በመሆኑ ፣ እንዲሁም ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ የተለየ የምርመራ ሥራ አልተሰራም በማለት ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፣የፊልም ዳይሬክተር እና ተዋናይት ሜላት ዳዊት በ5 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ጉዳዩን ከእስር ተፈታ እንድትከታተል ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
ጠዋት በዋለው ችሎት ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፤ ተዋናይት ሜላት ዳዊት በ5 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ፤ ፖሊስ ለከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰዓት በዋለው ችሎት ይግባኝ ጠይቋል ።

Melat

ይግባኙን የተመለከው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ፤ በታችኛው ፍ/ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ መርምሬ ” ውሳኔ የምሰጠው ፤ ነገ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 8 ፡00 ሰዓት ነው ” ብሏል ።

All reactions:

259

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop