ደብረኤልያስ ወረዳ በሚገኘው የሥላሴ አንድነት ገዳም ላይ 3 ሞርተሮችን ጨምሮ በተለያዩ ከባድና የቡድን መሳሪያዎች ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘው የፌደራል መንግስቱ መከላከያ ኃይል፤በገዳሙ ግቢ ውስጥ ከ200 በላይ መናኝ እናቶች የሚገኙበትን ግቢ በሞርተር በመምታት ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ መነኮሳት አልቀዋል፤ሌሎችም ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።በዚህም ገዥው የኦህዴድ ብልፅግና ስርዓት ከባድ የጦር ወንጀል ፈፅሟል።
ይህ የጦር ወንጀል በገዳሙ መናኝ እናቶች ላይ የተፈፀመው በአካባቢው የመደበኛ ስልክ ጥሪም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ነው።
ይህ ድርጊት በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ህጎች ፍፁም የተከለከለ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍ/ቤት(ICC) ጨምሮ የዓለም አቀፍ ማህበር ጉዳዩን በአጣዳፊ እንዲመለከተው እንጠይቃለን።
በጎጃም ደብረ ኤልያስ ጭፍጨፋ ሲፈፅም የቆየው የኦህዴድ ብልጽግና መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ሸበል በረንታ፣ ዲማ ጊዮርጊስ፣ የትኖራ ፣ወጀል ዓባይ ፣በመርጦ ለማሪያም፣ደብረዎርቅ እና እሁዲት-ኢናባራ አየሁ መከላከያ እንዲገባ ወስኖ ተጨማሪ የጦር ወንጀል እንዲፈፀም እያደረገ ነው።
በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ እንሳሮ፣ራሳ፣መርሃ ቤቴ እና ይፋት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት በማሰማራት በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የጦር ወንጀል በኦህዴድ/ብልፅግና የሚመራው ገዢ ስርዓት እየፈፀመ ነው።
መላው የአማራ ህዝብ በሠራዊቱ እየተፈፀመበት ያለውን የጦር ወንጀል በጋራ በመሆን ሊመክት ይገባል።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ሚዲያዎች፣የሲቪክ ማህበራት፣የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ሌሎችን የንፁሃን ጭፍጨፋን በአፅኖት ሊመለከቱት ይገባል።
የአማራ ህዝባዊ ግንባር
ግንቦት 23/2015 ዓ.ም