የአብይ አህመድን ጉድና ቅሌት ራሱም አይችለው (እውነቱ ቢሆን)

ውሸታሙ አብይ ገጽታው
ውሸታሙ አብይ ገጽታው

በአሁኑ ወቅት አገራችንና ህዝባችን ከምንጊዜውም ይበልጥ በታሪክ ተወዳዳሪ በሌለውና ታይቶ በማይታወቅ እጅግ አስከፊ በሆነ ችግር ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ከአምስት አመት በፊት በህዝብ መራራ ትግል ወያኔ ከስልጣኑ ከተወገደ በኋላ የህዝቡን ድል በሽወዳ የራሱ ያደረገው ኦህዴድ በአሁን ስሙ የ’ኦሮሞ ብልጽግና’ ኦሮሙማን ማለትም በቀጥታ ትርጉሙ ‘በሁሉም ረገድ የኦሮሞ የበላይነት የሰፈነበትን አይዶሎጅ’ መመሪያው በማድረግ በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ታላቋን ኦሮሚያ ለመመስረት ኢትዮጵያን እያፈራረሳት ይገኛል፡፡ አብይ አህመድ ለይስሙላ በማናጆነት ከየክልሎቹ የሚመስሉትን ሰብስቦ ብልጽግና የሚባል ፓርቲ ፈጥሮና ራሱን የፓርቲው ፈላጭ ቆራጭ በማድረግ አገሪቱን ወደመቀመቅ እየወስዳት ይገኛል፡፡ ይህንኑ አስከፊ ስርአት ዛሬ ታግለን በቶሎ ካላስወገድነው ሟርት ካለትባለ በስተቀር ምናልባት ተመልሰን እንደ አንድ አገር ህዝብ የምንኖርበት ሁኔታ ያከትማል፡፡

በኦሮምያ ከ8 ሚሊዮን በላይ በሚሆነው የአማራ ህዝብ ላይ << አንተ ዜጋ አይደለህም፣ በዘርህ ለይተን ብንገድልህም አስክሬንህ ጅብ ይብላው እንጅ እዚህ እንዲቀበር አንፈቅድም፤ ይህ መሬት አንተም በህይወት አትኖርበትም አስክሬንህም አይቀበርበትም ወዘተ>> የመሳሰሉት ጉዶች ኦሮሚያ በተባለችው የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ እየተደረገና እየሆነ ያለ ሀቅ ነው፡፡ በክልሉ ደረጃ  ይህንኑ የግፍ ግፍ በበላይነት የሚመራው አንድ ወቅት “’ አሜሪካ እሷም አታውቀኝም እኔም አላውቃትም” ሲል ባዶነቱን የገለጸው የክልሉ ፕሬዝዳንት ተብየው ሽመልስ አብዲሳ ነው፡፤ ሽመልስ አብዲሳ ማሰቢያው ጭንቅላቱ ሳይሆን ሆዱ ነው፡፤ ጭንቅላቱን የሞላው ንፍጥ ብቻ ነው፡፤ ለዚህ ማንነቱ ይህ ቦታው ባይሆንም ብዙ ማሳያወች አሉ፡፡

በኦሮምያ  በስፋት ከሚጨፈጨፈው አማራ በተጨማሪ ቁጥሩ ከአማራው ተጨፍጫፊ ጋር  ሲነጻጸር አናሳ ቢሆንም ግዲያው፣ ማፈናቀሉና ማሳደዱ በጉራጌው፣ በጋሞው፣ በወላይታውም፣ ወዘተ… ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰዉ በዘሩ ተመርጦ ለምን ተገደለ የሚለውን ጥያቄ ለጊዜው እንተወዉና አስክሬን  በጅምላ መቅበሩ ወይንም እንዳይቀበር ከልክሎ በጅብ ማስበላቱ ምን የሚሉት የሰው ባህርይ ነው?? በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን ህጋዊ  ኗሪ በዘር እየለዩ ለቤትህ ማፍረሻ ብር አስር ሽህ ክፈል ብሎ ማስገደዱ ካልከፈልክም ትታሰራለህ ብሎ ማስፈራራቱ እንደዚሁም ቤትህን አፍርሰውና እቃህን ውሰደውብህ ሜዳ ላይ ስትወድቅ በብዙወች ላይ እንደተፈጸመው የአንተንም ልጆች ጅብ እንዳይበላቸው በአካባቢው ተከራይተህ ልጆችህን  ለማስጠለል ስትሞክር አከራዮቹ አንተን መሰሉን ቤት የፈረሰበት ሰው ሲያከራዩ 15 ሽህ ብር ቅጣትና 3 ወር እስራት እንደሚፈረድባቸው እየተደረገ መሆኑን ስታይና ስትሰማ  የግፉ ጥግ የትየለሌ መድረሱን ትረዳለህ፡፤ ይህ ስርአት እስካለ ድረስ አሁን ኦሮሙማ ሊውጣት ባዘጋጃት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተጀመረው ቤት የማፍረስና ሰውን ጅብ የማስበላት የተረኞቹ  ዘመቻ ወደ መሀል ከተማና ብሎም በመላዋ አዲስ አበባ ላይ ላለመፈጸሙ ምንም ዋስትና የለም፡፤ ስለዚህ  አዲስ አበቤ ሆይ በየተራ ከምታልቅ አንዴ ተነሳና የሚሆነው ሆኖ ይለይልህ፡፡

የጥንት የማህበረሰብ ምመራማሪወች “ባሪያ ሰንሰለቱን ቢበጥስ ምን ይቀርበታል” ይሉ የለ?? ለነገሩ ልክ ናቸው፡፡ እንደታሰረ ቢቆይ ያው ባሪያ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ አመጽ አስነስቶ ሰንሰለቱን ቢበጥስ ግን ነጻ የመውጣት እድል ይኖረዋል፡፡ ካልሆነለትም ያው ሰንሰለቱን አያጣውምና አባባሉ ትክክል ነው፡፤ ይህ አባባል አሁን የአዲስ አበባ ኗሪ ያለበትን ሁኔታ ገላጭ ነው፡፤ ህዝቡ እየኖረ ሳይሆን ታስሮ እየታረበ ጥቅቂቶች ተረኞችን ግን በቁንጣን ሲቸገሩ እያየ ነውና፡፡

የሌሎች አገሮችን የህዝብ ጥያቄወችን ስንቃኝ እኛ ኢትዮጵያዊያን ምን እንደሆንን ፈጣሪ ይወቀው ያሰኛል፡፡ በአንድ ዳቦ ዋጋ  ላይ የሳንቲም ጭማሬ ሲደረግ ወይንም  በነዳጅ ላይ የሳንቲም ለውጥ ሲደረግ ወይንም ትንሽም ብትሆን የህዝብ መብት ጥስት ሲደረግ በሌላ አገር ህዝቡ ግልብጥ ብሎ ወጥቶና መንግስቱን አስጨንቆ ጥያቄውን ያስፈጽማል ወይንም መንግስትን ያስቀይራል፡፡ እኛ አገር የህዝብ አመጽ ያልተካሄደበት ምክንያት ህዝቡ በዘር ስለተከፋፈለ ነው የሚል አስተያየት ሊነሳ ይችላል፡፤ ግን እስከመቼ?? ህዝቡ በዘር ቢከፋፈልምና በተለይም  አብይ አህመድ “ኦሮሞ ዝሆን ነው ፣ ሌላው ሚዳቆ ነው’’ ስለሆነም የኦሮሞ በህዝብ ቁጥር በአገሪቱ ውስጥ ትልቁ ነው ….ወዘተ  እያለ እንደተለመደው ቢበጠረቅም እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ ሀቁ ሌላ ነው፡፡ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ካለው ጠቅላላ ህዝብ ውስጥ ከተረኞቹ አገዛዝ ተጠቃሚ የሆነው 1% የማይበልጠው ነው፡፡ የተቀረው ህዝብ ደረጃው ቢለያይም ሁሉም እንደ አማራው እንደ ሶማሌው …ወዘተ የችግሩና የኑሮ ውድነቱ ተቋዳሽ ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው! "መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ"

የህዝብ ብዛት ጉዳይ ከተነሳም በአገር ደረጃ አሁን ካለው 120 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ከ46% በላይና በአዲስ አበባ ውስጥም ካለው 7 ሚሊዮን የከተማዋ ኗሪ ውስጥ 60% አማራ ነው፡፡ ወያኔም ኦሮሙማም ይህንን ሀቅ አይቀበሉም ብቻ ሳይሆን ሆን ብለው ሀቁን ይክዱታል፡፤ ለምን ቢባል ሆን ተብሎ ከተዛባው የአማራ ቁጥር ማነስ ራሳቸው ባጸደቁት ህገ መንግስት ተብየው ድርሰታቸው አማካይነት ከፍተኛ የበጀት ድልድል፣ የድምጽ ቆጠራና የስልጣን ክፍፍል ጥቅም ስላላቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ቁጥር ብዛት በብሄር ቁጥር ብዛት ለይቶ ለማወቅ ካስፈለገ መፍትሄው ቁጥር ማዛባት ወይንም ቁጥር መጭመቅ ሳይሆን ትክክለኛና ነጻ የውጭ ታዛቢወች ጭምር ያሉበት ብሄራዊ የህዝብ ቆጠራ ማድረግ ብቻና ብቻ ነው፡፡ ይህ ቆጠራ ልክ አብይ አህመድ ‘በነጻ የህዝብ ምርጫ ነው የተመረጥኩት’ እያለ እንደሚያወናብደው የጨረባ ምርጫ እንዳይሆን ነጻ ምርጫ መሆን አለበት፡፤ ነጻ ማለት ነጻ ነው፡፡ ነገር ግን ነጻና ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ አብይ አህመድና ተረኛው የኦሮሙማ አገዛዝ በስልጣን እስከቀጠሉ ድረስ ይደረጋል ማለት ዘበት ነው፡፡ አይቻልም፡፡ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ህዝቡ  ከኦሮሙማ ካድሬወች ተጽእኖ ሳይደረግበትና ራሱ በነጻነት ወስኖ ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ላይ በነጻነት ይሳተፋል ማለት ቀልድ ነው፡፡ በተለይም በኦሮሚያ ክልል በማንነቱ እየታደነ በማለቅ ላይ ባለው 8 ሚሊዮኑ አማራ ዘንድ ይህ ይደረጋል ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ቆጠራ ነጻ ሆኖ ይካሄድ ዘንድ አስቀድሞ የተረኞቹ አገዛዝ መወገድ ግዴታ ነው፡፤

ኢትዮጵያ አሁን ከወደቅችበት አዘቅት ወጥታ ወደቀድሞው ገናና ታሪኳ በመመለስ ድጋሜ ጠንካራና ነጻ አገር እንዳትሆን አጥብቀው የሚጥሩት የውጭ ሀይሎች አብይ አህመድን “በወንጀለኝነትህ በአለም ፍርድ ቤት እንዳትጠየቅ አናደርግልሀለን” ብለው ቃል ስለገቡለት አገሩንና ህዝቡን አሳልፎ የሸጠው ከሀዲውና ለውጭ አገሮች አዛዦቹ አሽከር የሆነው አብይ አህመድ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራም ሆነ ትክክለኛ የምርጫ ስርአት ፈጽሞ አይኖርም፡፡ ሙቱ ፓርላማም ሆነ ለስሙ ባተቃዋሚነት ቆመናል የሚሉት የፖለቲካ ፓርቲወች የአብይ አህመድ አሻንጉሊቶች ከመሆን ሌላ እርባና የላቸውም፡፤ ህዝቡም አገሪቱም እጅግ ከባድ ችግር ውስጥ ወድቀው የመበታተንና አደጋ በተደቀነበት በዚህ ወቅት እንደዚሁም በአገሪቱ  ላይ የእርስ በርስ ጦርነት ባንዣበበትና እንደ አማራ ክልል ባሉ ሰፋፊ ክልሎች ውስጥም ጦርነቱ በተጀመረበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ያመላከቱት ከችግር መውጫ የመፍትሄ መንገድ የለም፡፡

የህዝብ ቆጥራ፣ የህገ መንግስት ማሻሻያ ወዘተ ….የሚሏቸው የሰሞኑ የውሸትና የማደናገሪያ አጀንዳወቻቸውም ስርአቱ እንደዚህ ቦክቶ በገማበት ወቅት ከስርአቱ መወገድ ውጭ መፍትሄ የሚሆን ነገር ስለሌለ አሁን ላይ ገዥወቹ ከጭንቀት የተነሳ የሚሉት ሁሉ ከማታለያነትና የገዥውን ክፍል እድሜ ከማራዘሚያነት አያልፍም፡፤ ህዝቡኮ ስርአቱን በቃኝ ብሏል፡፤ ስለሆነም ሌላ ውትፍትፍ ነገርን አይቀበልም፡፡

አብይ አህመድ አማራውን በታትኖ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ቢሞክርም እስካሁን ግን አልተሳካለትም፡፡ከእነ ዶ/ር አምባቸው መኮንን አና ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ….ወዘተ ግዲያ ጀርባ የአማራ ሆዳሞች እጅ እንዳለበት ህዝቡ አሳምሮ  ያውቃል፡፡ አብይ ይህንን የሚያፈጽመውም ሞቶ በተገነዘው በብአደን በአሁኑ መጠሪያውም  በአማራ ብልጽግና አማካይነት ነው፡፤ ዋናወቹም አስፈጻሚወችም ተመስገን ጥሩነህ፣ አገኘሁ ተሻገር ደመቀ መክንን… ወተ የመሳሰሉት ሆዳሞች ናቸው፡፡ ግርማ የሽጥላ አንዱ ሆዳም የነበረ ሲሆን ለአላማው መጠቀሚያ ለማድረግ ሲል ራሱ አብይ አህመድ ጨክኖ ሸኝቶታል፡፡ የአብይ አህመድ አላማ እስከቻለ ድረስ አማራን በአማራ ማስበላትና ማባላት ነው!! ወያኔ አርበኛ ጎቤ መልኬንኮ ያስገደለው በራሱ የእህት ልጅ በኩል ብር 500 ሽህ ስጠቶ ነበር፡፡ያንኑ ልጅ አፍታም ሳይቆይ ወያኔ አስወግዶታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰው ገንዘብ ቁንቋን ነው! - በላይነህ አባተ

አሁን ግን ነገሮች ተቀያይረዋል፡፤ አማራው ነቅቷል፡፤ ይበልጥም እየተደራጀና የመልስ ምት እየሰጠ ነው፡፤ በይበልጥም አዲስ የተጀመረው የአማራ ህዝባዊ ሀይል እየጠነከረ ሲሆን ክልሉን ከሆዳሞች አጽድቶ አማራውን ከኦሮሙማና ወያኔ ጣምራ ጥቃት ነጻ በማውጣት ለኢትዮጵያ አለኝታነቱን በተግባር ያረጋግጣል፡፡ ለዚሁ ስኬትም የውጭውም የውስጡም አማራ አንድ ላይ ተናብቦ በመቆም  ክልሉን ከኦሮሞ ወራሪ ጦር ነጻ ለማድረግ  እርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡የትግሉ አስኳል የሆነው ፋኖ  የኢትዮጵያን መከላከያና የአማራ ልዩ ሀይል ዩኒፍሮምን ለብሶና እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊና ከባባድ የአገሪቱን መሳሪያወችን ታጥቆ  የመጣውን የኦሮሞን ሀይል መክቶ በመጣል ጀግንነቱን በተግባር እያስመሰከረ ነው፡፡እየተዋደቀ ነው፡፡ አብይ አህመድ ድሮን፣ ታንክ መድፍና ከባባድ መሳሪያወችን በአማራ ህዝብ ላይ መጠቀም መጀመሩም ይፋ ሆኗል፡፤ ለዚሁ እውነታነት በከባድ መሳሪያወች እየተመታ ያለው ህዝቡ ራሱ ምስክር ነው፡፡ ስለሆነም አማራው ይህ መንግስት ገዳዬ እንጅ መንግስቴ አይደለም ብሎ ቆርጦ ተነስቷል፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል ከድል መለስ ወድኋላ ላይል ወስኖ ተነስቷል፡፡

 

ወያኔ ራያንና  ወልቃይትን በአብይ ህመድ አለቆች ትእዛዝ ጭምር ታግዞና በኦሮሙማ አንቀልባ ታዝሎ ለመውሰድ የቋመጠ ቢሆንም እነዚህ መሬቶች ለአማራው የደም መሬቶቹና ታሪካዊ ርስቶቹ ስለሆኑ እስከመጨረሻው ድረስ አማራው ይዋደቃላቸዋል እንጅ መቸም ቢሆን መቼም እነዚህን ርስቶቹን አሳልፎ ለወያኔ አይሰጥም፡፡ አብይ አማራውን ለመከፋፈል አድስ ስትራቴጅ ቀምሮ ጉዞውን ጀምሯል፡፡ ለዚሁም ተግባር ጀኔራል አበባው ታደሰን የቁማሩ ቀዳሚ መሪ አድርጎታል፡፡ ኦሮሙማ ከወያኔ ጋር በመናበብ ከተቻለ ደቡብ ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ እንደዚሁም  ሰሜን ወሎን ደግሞ ደቡብ ትግራይ ለማድረግ አሲሯል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በአማራው ክልል ውስጥ ያሉትን የወሎን ሸዋን፣ ጎጃምንና ጎንደርን ህዝብና መሬቶች ለብዙ ክፍልፋዮች በመሽንሸን አማራውን ለማዳከምና በተጓዳኝም ቅማንትና አገውን ከአማራ ክልል በመገንጠል ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ለማድረግ አሲሮና እቅድ አውጥቶ ስራውን ጀምሯል፡፡የሚገርመው ግን እነዚህ መሰሎቹ የኦሮሙማ ሴራወች በአማራው አስቀድመው የተበሉና የተነቃባቸው መሆኑ ነው፡፡ እንኳን አሁን ከወያኔ በማይሻለው የኦሮሙማ አገዛዝ ቀርቶ አማራው ዱሮም በጣልያን ወረራና በቅርቡም ለወያኔ መርዛማ አገዛዝ ወቅት ለማንም ያልተንበረከከ ህዝብ ነው፡፡ እንደ ህዝብ አማራው መቼም ቢሆን አይከፋፈልም፡፡

በዚህች መጣጥፌ ላይ ላተኩር የመረጥኩት መንግስት መር በሆነው የውች ምንዛሬ ጥቁር ገበያ ላይ ነው፡፡  መንግስት መሩ የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያ ሁለት መሰረታዊ  ጉዶቹ የተገመዱበትን ሁለት ቁማሮችን መነሻ ያደረገ ነው፡፡

ቁማር ቁጥር አንድ ፦ የሚላከው የውጭ ምንዛሬ ዶላር ነው እንበል፡፡ በውጭ አገር ላኪው ለስርአቱ ለሚሰሩ የተመረጡ የገንዘብ አስተላላፊወች ዶላሩን ይከፍላል፡፤ ያም ለምሳሌ በአንድ ዶላር ብር 110 ምንዛሬ ለተቀባዩ እከፍላለሁ ያለው አስተላላፊ ከአብይ አህመድ ቡድን ጋር ባለው ሰንሰለት መሰረት ዶላሩን ተቀብሎ ብሩን በተባለው ተመን ለተቀባዩ በባንክ እንዲከፈል የብር መጠኑን፣ የተቀባዩን ስም፣ የተቀባዩን ባንክና የተቀባዩን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ወደ ኢትዮጵያ ያስተላልፋል፡፤ ክፍያውም በተባለው ተመን ለተቀባዩ በባንክ አካውንት ቁጥሩ ገቢ ይደረግለታል፡፡ ይህንን ቁማር ብሄራዊ ባንክ አያውቀውም አይባልም፡፡ የቁማሩ ተዋናዮች ግን ክፍያውን የሚፈጽሙት ባንኮችና አገዛዙ ለዚሁ ተግባር የመደባቸው ናቸው፡፡ በህጉ መሰረት ምንዛሬው በህጋዊዉ ተመን በዶላር ብር 54 ሂሳብ ስላልሆነ ወደ የኢትዮጵያ አካውንት ውስጥ እንዲገባ አይደረግም፡፡የጥቁር ገበያው ቁልፍ የተቆለፈው በዚህ ቁማር ላይ ነው፡፡ አንድ ዶላር ብር 110 እየተመነዘረ ይህንን ትቶ አንድ ዶላርን ብር 54 መንዝሮ የሚልክ ዲያስፖራ መቼም ቢሆን አይኖርም፡፡ በዚህ መልክ የሚላኩት የውጭ ምንዛሬወች በቢሊዮን ዶላር ተከማችተው በዚህ መልክ ወደ አገሪቱ ማለትም ወደ ኢትዮጵያ አካውንት ሳይገቡ በዚያው ሰርገው ይቀራሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   ዝ ክ ረ   ዓ   ደ   ዋ  ! - መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

ቁማር ቁጥር ሁለት፦ ሁለተኛው ጉድ ደግሞ ይሄው የምንዛሬ ክፍያ የሚፈጸመው በመንግስት ከወጣው የምንዛሬ ተመን በእጥፍ ጨምሮ ሲሆን አሁንም ክፍያውም የሚካሄደው በባንኮች በኩል መሆኑ ነው፡፡ ይባስ ብሎ አንዳንድ ጊዜ ብሩ ለተቀባዩ የሚገባለት ላኪው በሰጠው የተቀባዩ የባንክና አካውንት ቁጥር አይደለም፡፡ አገር ውስጥ ቢሊዮኖች ብሮችን በየቀኑ ከውጭ ገንዘብ ለተላከላቸው ተቀባዮች እንዲከፈል የሚያድርጉት “ሀይሎች”ምክንያቱን ማወቅ ባይቻልም አንዳንዴ ገንዘቡን የሚያስገቡት ላኪው ወዳዘዘበት የገንዘብ ተቀባዩ ባንክ አክውንት አይደለም፡፡ ይልቁንም በአገሪቱ ውስጥ የባንክ ሂሳብ ያላቸውን የሁሉንም የባንክ ደንበኞች ዳታ ቤዝ በሙሉ በጃቸው ስስገቡት ተቀባዩን በሌላ ባንክ ውስጥ የባንክ ሂሳብ እንዳለው በስሙ ፈልገው ካገኙ በኋላ ለእነርሱ አመቺ በሆነው መንገድ ማለትም የሰውየውን ስምና የሂሳብ ቁጥር ባገኙበት በሌላ ባንክ ውስጥ ገንዝቡን በስሙና በሂሳብ ቁጥሩ ያስገቡለታል፡፡ ይህንን ነው ሁለተኛው ጉድ ያልነው፡፡

እዚህ ላይ እውነቱን ማወቅ ግድ ይለናል፡፡ አንድ ዶላር በብር 54 ከምንልክ በብር 106 ብንልክ አገር ቤት ያሉ ዘመዶቻችንን ይበልጥ ይጠቅማቸዋልና ዶላሩ መጨረሻ ላይ  የሚገባው አገሪቱ ሂሳብ ውስጥም ሆነ አብይ አህመድ ወይንም እርሱ የሚመደባቸው ነጋዴወች ሂሳብ ውስጥ ለእኛ ለውጥ አያመጣም የሚሉ ላኪወች ይኖራሉ፡፡ ትክክል ናቸው፡፤ዶላሩን መላኩ ግዴታ ከሆነ ለውጥ አያመጣም፡፡ አሁን ላይ በሁለቱም በኩል ብር እንደፈለገው እያሳተመ ዶላሩን በቢሊዮኖች የሚያግበሰብሰው አገሪቱ ሳትሆን የገዥው መደብ ስለሆነ በዚህም ሆነ በዚያ ቢላክ እውነትም ለውጥ አያመጣም፡፡ እኔ ግን ነገሩን ያነሳሁትና በጽሁፌ ላሳውቅም የፈለግሁት ይህ ጥቁር ገበያ በተለይ በአገር ቤት ደረጃ በህጋዊ መንገድ በባንኮች በኩል የሚሰራው ግፍና ምዝበራ ጥቁሩ ገበያ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው የኑሮ ውድነት በአገዛዙ ዱርየነትና ለአገርና ህዝብ ባለው ደንታ ቢስነት መሆኑን ማሳወቅ ስለፈለግሁ ነው፡፡ ይህም ደንታ ቢስነትና በህዝብ ህይወት ላይ ቁማር መጫወት ራሱ አብይ አህመድ የአገር መሪ ሆኖ የጥቁር ገበያውን ቁማር ራሱ አውቆት፣ ፈቅዶትና ሆን ብሎ የሚያስፈጽመው የራሱ ጉድ መሆኑን ለማስመር ነው፡፡ መንግስት ተሁኖ እንዴት ጥቁር ገበያ ውስጥ ይገባል??? ይህንኑ ድርጊት በህገወጥነት አቅዶና አደራጅቶ የሚመራው አብይ አህመድ ከላይ ሆኖ ከየሚመለከታቸው የሴክተር መስሪያ ቤቶች ሀላፊወች/ሚኒስትሮች ጀምሮ ባደራጀው ቡድን ሲሆን ይህም ቡድን በውጭ አገራት ከገንዘብ አስተላላፊነት ጀምሮ በአገር ውስጥም ወደታች እስከ ባንኮች ክፍያ መስኮት ድረስ በጥቅም ሰንሰለት የተያያዙትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

እስኪ ይታያችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቀን ከ50 ሽህ ብር በላይ ሲሻቸውም ከመቶ ሽህ ብር በላይ ከባንክ ማውጣት አይቻልም በሚባልባት ኢትዮጵያ ውስጥ ፤እንደዚሁም ወደ ሌላ ሰው የባንክ ሂሳብ በቀን ማዞር የሚቻለው በሽወች መጠን ብቻ ነው በሚባልባት ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ይህንኑም እንዳመቻቸው በየቀኑ ከፍና ዝቅ በሚያደርጉባት ኢትዮጵያ ውስጥ ፤አገራችን ኢትዮጵያ በጥቁሩ ገበያ ለተላከው ዶላር በጥቁር ገበያው ምንዛሬ የብር ክፍያወችን ለማድረግ በአንድ ቀን ውስጥ ቢሊዮኖች ብሮችን ማንቀስቀስ የሚችሉ “ልዩ ዜጎች” ያሉባት አገር ስትሆን ምን ይስማናል?? አይገርምም?? አያምም??

ከጭቆናው፣ከግዲያው፣ ከአፈናውና ከአገር ማፍረሱ ቀጥሎ የህዝቡን የየእለት ተስፋ ያጨለመው፣ ህይወቱን ያመሰቃቀለውና የኑሮ ውድነቱን አይቀመሴ አድርጎ ሰማይ ጥግ ያደረሰው በአብይ አህመድ የሚመራው ይህ የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያ ነው፡፡ በእኔ እሳቤም የአጭቤው አብይ አህመድ አንዱ ቅሌትና አንዱ ጉድ እርሱ በዋናንነት የሚመራው ይሄው የጥቁር ገበያ ቁማር ነው፡፡

 

 

 

5 Comments

  1. ወያኔ መርዝ ረጭታ ሄደች:: ኦሮሙማ ደግሞ መርዛማነትን ተግቶና በመርዝ ስካር አብዶ ህዝቡን ፈጀው::
    መለስ ዜናዊ መጥፎ መሪ የነበረ ቢሆንም ከእንሰሳውና እንዴ ከብት ከሚያስበው እውሬው አብይ አህመድ ሽህ ጊዜ ይሻላል::
    ዳሩ ምን ይደረጋል– ቀን አያውቁ ነገር…

  2. ይሄ ጠቅላይ መሪ የሱ ሰው ማን ይሆን? ጁዋርም አንገቱን ልትለው ቀን እየጠበቀች ነው መራራ ጉዲናም ኪንግ ሜከር ለመሆን አድፍጦ ይከታተላል ሽመልስም የሱ ሰው መስሎ ዞር ሲል ምላሱን ያወጣበታል ኦሮም ምን ቢያሽቃብጥ አይንህን አልየው ብሎታል ትግሬም አሳቻ ጊዜ እየፈለገ ነው ያማራው ማብራሪያም አያስፈልገውም እንግዲህ ይሄ ሰውዬ በነብይ እስራኤል ዳንሳ፤በእዩ ጩፋ እና መራሄ ነብያት ዮናታን አክሊሉ ጸሎት ካልሆነ ማን አለው ከጎኑ? ብርሃኑ ነጋ አደጋ ሲመጣ ሶስቴ ሳይሆን 12 ጊዜ ይክደዋል እንደፍጥርጥሩ ምን አገባኝ ለካ እነ ዳውድ ኢብሳና የባህል ናጅ ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳም አለ መጥኔ አገሪቱ ምን በደለች?

  3. የኤርትራው መሪ ስለ ወያኔና የድህነቱ መንግስት ስምምነት ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል “የሰላሙ ስምምነት ወያኔን ለማዳን በአሜሪካ ግፊት የተደረገ ነው”። ልክ ናቸው። አሁን በአማራ ክልል የተጀመረው ወረራም በአሜሪካ መሪነት የሚፈጸም ነው። ወያኔን እፎይታ ለመስጠትና ያሰቡትን ግብ ከግቡ ለማድረስ የአማራ ፋኖንና የአማራ ልዪ ሃይልን መበተን፤ ህዝብን ትጥቅ ማስፈታትና ማበራየት ወያኔ ፤ የዶ/ር አብይ መንግስትና አሜሪካ አብረው የመከሩበት ጉዳይ ነው። ዛሬ እየታሰረ፤ እየተገደለ፤ ከመኖሪያው እየተፈናቀለ ያለው የአማራው ህብረተሰብ ነው። ወያኔም ገና ጫካ እያለ የተጋተው ይህኑ በፈጠራ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ አማራን የመጥላት በሽታ ነው። ታዲያ ነገር እየተረሳ ጊዜው እየመሸ ሲሄድ ወያኔ የሽንፈት ቁስሉን እየላሰ አሁን ለሁለት በሚመስል መልክ ተከፍሎ በመቀሌ አንድ ሰልፍ ሲጠራ ሌላው ለሰልፉ ፈቃድ አልሰጠሁም ይላል። ይህ የመሸዋወድ ፓለቲካ ወያኔ የተካነበት በትግራይ ህዝብ ስም ለ 50 ዓመት ሲያወናብድበትና ሲነግድበት የኖረበት የፓለቲካ ቁማር ነው። ሌላው የፓለቲካ የመጫወቻ ካርታቸው የአማራና የኤርትራ ሃይሎች ከትግራይ አልወጡም በማለት የሚያሰሙት ሰሚ የለሽ ኡኡታ ነው። ያኔ በሳተላይት እየተደገፉ ደብረ ብርሃን ሲደርሱ፤ ያኔ ተመድ ወያኔን ደግፎ 12 ጊዜ ሲሰበሰብ፤ ያኔ የአሜሪካ የውጭ መስሪያቤት የወያኔ ቃል አቀባይ በሚመስል መልኩ ሲደነፋ ምንም ያልተሳካለት ሙት የፓለቲካ ስብስብ አሁን እንደገና ተሰልፎም ሆነ አሰልፎ እኔን ስሙኝ የሚልበት ጉልበቱም፤ ተደማጭነቱም የለውም። የዓለም የፓለቲካ አሰላለፍም ለይቶለት ለሁለት እየተሰነጠቀ ነው።
    እንግዲህ በዚህ ውስጥ ነው የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ጊዜ ሰጥቷቸው ወያኔን ተክተው የእርሱን ፈለግ በመከተል አሁን እንሆ እስር ቤቱ ሁሉ በአማራ ተወላጆች የሞላው። ዶ/ር አብይ ከወያኔ የክፋት ከረጢት አፈትልኮ የወጣ በእነርሱ ተንኮል የተካነ ብሄርተኛ ፓለቲከኛ ነው። ያኔ ሰው ሁሉ ሆይ ሆይ ሲል ተው ይህ ሰው ቆይቶ ጉድ ያመጣል ብዬ ያስጠነቀቋቸው ጓደኞቼ ዛሬ ደውለው ይህንም ያንም ሊሉኝ ይሞክራሉ። የብልጽግናው ፓርቲ (የድህነት) ፓርቲ ፓለቲካ ልክ እንደ ወያኔ አሰራር ነው። እስቲ ማን ይሙት ሰው ወንድ ልጅን ልብሱን አስወልቆ ፎቶና ቪዲዪ ያነሳል? ለነገሩ በእስረኛ ላይ ሽንቷን የምትሸና የወያኔ መርማሪ እንደነበረች ሰምተን የለ? ይህ ግፍ ሰውን ሊያስተኛ አይችልም። እልፍ እያለቀሰና እየተራበ መናጠጥ የሮም አወዳደቅን ያመጣል።
    በቅርቡ የኤርትራን 32ኛ የነጻነት በዓል ለማክበር ከተሰበሰቡት መካከል ደጋፊና ተቃዋሚ ቡጢ ገጥመው ማየት ምንኛ ሃበሻ መሆን ያስጠላል። ሃበሻ አንድ የሚያደርገው ነገር እንጂ የሚከፋፍለው ነገር ሞልቷል። ማንም ኤርትራዊ ከሃገሩ ውጭ ሆኖ አሸሸ ገዳሜ ማለቱ በኤርትራ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አይቀይርም። ተከበረ አልተከበረ ለውጥ የለውም። ግን በዚህም በዚያም እያሳበቡ ዘና ለማለት ይመቻል። በቡጢና በቃል መራኮቱ ግን የከባቢን ሰላም ከመረበሹ በላይ ራስንም ለትዝብት ይጥላል። ባይገባችሁ ነው እንጂ ፓለቲካ እንደ ቀትር ጥላ ነው። የአቶ ኢሳያስ ከስልጣን መውረድ በኤርትራ መሬት የሚያመጣው አንድም ፋይዳ አይኖርም። ይባስ መጨራረስና መቆራረስን እንጂ። ስለሆነም ነገርን አክሮ ከመያዝ በሰከነ መልኩ መርምሮ ሁሌ በጉልበት ግብን ከግቡ ለማድረስ ከመውተርተር እያወቁ ይለፈኝ ማለትም ብልህነት ነው። በእኔ እምነት የኤርትራው መሪ ጊዜና እድሜ ብልሃት እየጨመረላቸው አሁን አፍሪቃ አላቸው ከሚባሉ ሚዛናዊ መሪዎች ቀዳሚው ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከዚሁ አንጻር በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ ኤርትራዊያን ነጻ የሆኑበትን ቀን ሲያከብሩ ማየትም ደስ ያሰኛል።
    ባጭሩ ያኔ ለወያኔ ከደርዘን በላይ የተሰበሰበው ተመድ አሁን በሱዳኖች መካከል ባለው የእርስ በእርስ ውጊያ አልፎ አልፎ ከማላዘኑ ሌላ የሰራው ተግባር የለም። ይህ ሆን ተብሎ በዚሁ ሳቢያ ኤርትራን ለማተራመስ አልፎ ተርፎም ኢትዮጵያን ለማንገዳገድና መልሶ ለወያኔ ለማስረከብ የሚደረግ ስልታዊ ሂሳብ ነው። ግን አይሳካም። አሁን ያለው ችግር የኦሮሞ ብሄርተኞች የተለጠጠና ከልክ ያለፈ እኛ ብቻ የሚል የአፈናና የግድያ ስልት ነው። ይህ ሊቆም ይገባል። የአፍሪቃ ቀንድ ችግር በአንድ ሃገር ተጀምሮ በዚያው የሚያልቅ አይደለም። የሚቀጣጠል እሳት እንጂ። ታላቋ ሱማሊያ አሁን ለሁለት ተቆርሳ እንደገና ደግሞ ሶስተኛ ሃገር ለመፍጠር ግብግብ ላይ ነች። የኢትዪጵያን መቆራረስ ቆማ የባረከችው ሱዳን ደቡብ ሱዳን ስትለያት አሁን ደግሞ በእርስ በእርስ ውጊያ በመተራመስ ላይ ትገኛለች። ቆይቶም ዳርፉርና ሌሎች ለብቻችን ማለታቸው አይቀሬ ነው። እንዲህ ነው የአፍሪቃ ፓለቲካ – የዘርና የጎሳ የቋንቋ ትርክት ላይ የተመሰረተ፤ እንዲህ ነው በሰፈሩት መስፈሪያ ምላሹን ጊዜ ሲሰፍር። ዶ/ር አብይም በመንግስታቸው ያለውን ብልሹ አሰራርና በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን አጥፊ ዘመቻ ማስተካከል እስካልቻለ ድረስ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ከአሁንም ወደ ከፋ ሁኔታ ሊከታት ይችላል። አሜሪካን ያመነ ውሃ የዘገነ። ከፈረሱ ሃገሮች ሰው እንዴት አይማርም? ዝንተ ዓለም ውሃ ወቀጣ። ስናሳዝን። በቃኝ!

  4. አብይ አህመድ የለየለት ሰይጣን ስለሆነ በማንም ተጠላ በማንም መጨረሻው አያምርም፡፡ አጨራረሱ የሚመስለኝ በውጭ አለቆቹ እንደ ላይቤሪያው መሪ ሳሟኤል ዶ አሟሟት አይነት ይመስላል፡፡ ሳሙኤል ዶን የገደሉት ኋላም ገዳዮቹ ያላለፈላቸው በራሱ ቅርብ ሰወች በውጭ አገራት አለቆቻቸው ታዝዘው ነው፡፤ አገዳደሉም በታሪክ እንደተመዘገበው ይህንን ይመስል ነበር፡፤ አሰሩት፣ ቀጥሎም የእጆቹን ጥፍሮች አንድ በአንድ ነቃቀሏቸው፡፡ ከዚያም የእግሮቹን ጥፍሮች እንዲሁ አደረጉ፡፡ ቀጥሎም አንድ ጆሮውን ቆረጡት፡፡ መጨረሻም ላይ ሁለተኛውን ጆሮውን ደገሙትና ገደሉት፡፡ አስክሬኑንም በዚያች አገር እንዳይቀበር ለማድረግ አቃጥለው አመዱን ወንዝ ውስጥ በተኑት፡፤ የእርሱመጨረሻ ይህንን አይነት ዘግናኝ አሟሟት ነበር፡፡ ስለዚህ አብይ አህመድ ጃዋር ስልጣኑን ሊወስድበት ያደባበታል፣ ትግሬ አሳቻ ጊዜ እየጠበቀለት ነው፣እስራኤል ዳንሳ፣ እዩ ጩፋ ዮናታን አክሊሉ ይጸልዩለታል…..ወዘተ የሚለው ፍሪከርሲኪ ቢሆንም ባይሆንም አብይ አንድ ቀን አለቆቹ ካዘዙት ውልፍት ያለ ቀን በእነርሱ በኩል ያልቅለታል፡፡
    ይልቅስ አማራው ማድረግ ያለበት የአብይን ለአብይ ትቶ አስቀድሞ አማራውን ለዚህ ውርደትና እልቂት ያበቁትን የራሱን ሆዳሞች ሳያቅማማና ለነገ ሳያስድር ሁሉንም ለቃቅሞ መሽኘትና በክልሉ ሊወርረው የመጣውን ሀይል ተደረጅት መመከት ብቻ ነው፡፡ ይልቃል ከፋለ መልቀቂያ አስገባ፣ ደመቀ መኮንን ከአብይ ጋር ተጣልቷል እያሉ ሆን ብለው የሚያናፍሱት ማዘናጊያ ወሬ ሁሉንም የብአደን አህዮች ከተጠያቂነትና ከህዝባዊዉ ፍርድና እርምጃ አያስጥላቸውም፡፤ ማን ሆነና ነው ሚሊዮን አማራወችን ያሳረደው???አይቀርላቸውም!!!
    ፈጣሪኮ አስውቆናል፡፡ ሰው የሰራውን ያገኛል ፡፡ የዘራውንም ያጭዳል ብሎ፡፡

  5. የወያኔና የኦሮሙ አማራን ለማጥፋት ጥምረት ፈጥረናል ማለታቸው ለአማራው በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡፡ ምክንያቱም አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ መጃጃሉን ትቶ ኢትይዖፕያን ለማስቀተል ረዥም ዘመናት ይዞት የነበረውን ፍላጎት ቁርጥ ያድርገለታል፡፡ ስለሆነም ይህ ውሳኔያቸው አማራው አንድ ሆኖ ወያኔንም ኦሮሙማንም ለመመከትና ድል ለማድረግ ያስችለዋል፡፡ መጃጃሉም ይቆርጥለታል፡፡
    አማራው ከአሁን ጀምሮ ጊዜ ሳያጠፋ ክልሉን ከራሱ ሆዳሞች በጥንቃቄ ነገር ግን ያለ ርህራሄ ጠራርጎ ማጽዳትና ክልሉን ነጻ ማድረግ አለበት፡፡ ታሪካዊ ርስቶቹንና መሬቶቹን ማለትም ደራን፣ መተክልን፣ ራያንና ወልቃይትን በአስተማማኝ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ጥንታዊ ርስቱንና የአያቶቹ መናገሻ የሆነችውን በረራን በአሁን ስሟ አዲስ አበባን ኦሮሙማ እንደሚለው የኦሮሞ ብቻ ሳትሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትሆን ራሷን በራሷ የምታስተዳድር ዋና ከተማነቷን በትግሉ ያረጋግጣል፡፡ ይህንኑም ያስቀጥላል፡፡
    ከዚህ ውጭ ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንጦርጦስም ድረስ እገባለሁ እንዳለው ይግባና ይሞክረው እንጅ በኦሮሙማ አንቀልባና በአሜሪካኖቹ ቡራኬ ወልቃይትንም ራያንም ከአማራው መዳፍ ፈልቅቆ መውሰድ ፈጽሞ አይችለውም፡፤
    ሽመልስ አብዲሳና ጌታቸው ረዳ አማርኛ ቋንቋን በየክልላቸው እንዳይነገር ለማድረግ እንደተስማሙ አሳውቀውናል፡፡ ሁለቱ ቅዠታሞች ይህንኑ የተስማሙት በወፍ ቋንቋ ወይንም በምልክት ቋንቋ አይደለም፡፡ ያው በሚጠሉት በአማርኛ ቋንቋ እንጅ፡፡ ታዲያ ይህ ፈገግ አያደርግምን???
    በነገራችን ላይ አብይ አህመድ አሊአሁን ላይ ጦጣ ሆኗል፡፡ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ውጭ መውጣታቸውን እንኳን በአግባቡ ሳይረዳ ፍጻሜው ደርሷል፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንዲሉ ሁሉንም በመሞከር በመስለው ለመዳን እየተንፈራገጠ ነው፡፡ነገር ግን ጊዜው አልፎበታአል፡፤ ውሸቱም ቁማሩም አልቆበታል፡፡ ታዲያ ዝም ተብሎ ይሞታልን??? መንፈራገጥጥጥጥጥጥጥጥ……

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share