በኢትዮጵያ የማንነት ፤ወሰን/ ዳር ድንበር እና ሉዓላዊነት ጉዳይ ለምን ይደበሰበሳል ?

ኢትዮጵያ እንደ አገር ስትመሰረት እና ስትኖር ከ፭ ሽ ፭፻ ዓመታት በላይ ማስቆጠሯን ከእኛ በላይ ዓለም እና ዓለም የደረሰበት ዕዉነት(ስነ ሰብ )  ይህም በእንግሊዥኛዉ  “ science of archeology “ የስነ ሠዉ ፍጥረተ ቅሪት በኢትዮጵያ ምድር መገኘቱ ነዉ ፡፡

ይህም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና የዜጎችን የሽ ዓመታት ሉዓላዊነት የሚመነጨዉ ከዚህች የሠዉ ልጂ ምንጭ ከሆነች አገር የሚቀድም አገርም ሆነ አካል አለመኖሩን ዕዉነት ለሚገባዉ እና ዕዉነትን ለሚሰልግ የበቂ በቂ ማስረጃ ነዉ ፡፡

ሆኖም ከዕዉነት ይልቅ በሀሰት ላይ መደገፍ የሚቀናን ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያን ተቀምጦ እንዳዋለደ ራሱን የሚያይ የፖለቲካ ድርጂት እና ትዉልድ የኋላ የታላቋን ኢትዮጵያ እና ህዝብ ታሪክ እንደማወቅ እና እንደማስለጠቅ ታሪክ እና መሬት መንጠቅ ስራ ሆኗል፡፡

ለዚህም የታሪክ እና መሬት ቅርምት እና ሽሚያ መነሻ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን በጥላቻ እና በምቀኝነት ደዌ በተለከፉ ኢህአዴግ ወለድ እና ዘራሽ ከዳሚዎች ነዉ፡፡

የኢህአዴግ አስኳል የሆነዉ ትህነግ ከጥንስሱ ሶስት የኢትዮጵያዉነት ጥንተዊ ፣ ታሪካዊ እና ገናና መሰረቶች መገለጫዎችን ማክሰሰም እንደነበረ ከትግል መነሻ እና መድረሻ ሆነዉ የሚጠቀሱት ኢትዮጵያ ፣ ዓማራ እና ኢትዮጵያዊ ማንነት (ባህል፣ ዕምነት እና ቁመና) ናቸዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ሲሉ አገር ፣ ኢትዮጵያዊነት ብሎ ዜግነት ፣ ዓማራ ብሎ ህዝብ ፣ የኢትዮጵያ የነፃነት ምልክት ባንዲራ ( አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ) አይኖርም ብሎ ከሚመኝ የምንጊዜም የዉስጥ እና አገር ወለድ  ታሪካዊ ጠላቶች  (ትህነግ -ኢህአዴግ)  የተከሉት የዓመታት የፍትህ  እና የህልዉና ዕጦት መንስዔ የሆነዉን አካል የዚህችን አገር እና ህዝብ የሽ ዓመታት ታላቅነት እና ክብር እንዲቀበል እና አንዲመለስ መጠበቅ  ብርቱ ድንቁርና ነዉ ፡፡

ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት ራሱ ኢህአዴግ በተከለዉ ህገ ኢህአዴግ፣የክልል ግዛት አወቃቀር እና የኢትዮጵያን ነባር የግዛት አስተዳደሮች እንዳልነበሩ ለማድረግ ቋንቋ መር የክልሎች አስተዳደር ተከትሎ ግልፅ የማንነት እና የግዛት አስተዳደር ችግሮች በአድሏዊ እና ጥላቻ በተለወሰ የፖለቲካ አመለካከት ተፈጥሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንባ ገነን የስልጣን ጥም አባዜ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ)

በዚህም በተለይም በትህነግ -ኢህአዴግ ጠላት እና ወዳጂ ብሎ በመፈረጂ ጥላቻ የወለደዉ ዓማራ ጠል ቅስቀሳ እና ወቀሳ የዓማራዉን ማህበረሰብ ማንነት ፣ ብሄራዊ አስተሳሰብ  ፣ታሪክ እና አገር ለማሳጣት የተደረገ አንዱን አባር እና ሌላዉን ገባር ለማድረግ የሆነ የክልል አወቃቀር ነዉ ፡፡

በዚህ ምክነያት ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን ከስሩ ለማንገል መኃል ኢትዮጵያን በተለይም ዓማራ ክልል የሚባለዉን አካባቢ ጎንደር ፣ጎጃም፡ ፣ወሎ እና ሸዋን(ጐወሽ) ከዉስጥ ከሚገኙበት እና ከዉጭ ከሚኖሩበት ማጣበብ እና ማሳደድ እንዲቻል ሆኖ በልዩነት የክልል ወሰን እና ማንነት ክልከላ ወይም ክለላ ሆኗል፡፡

ይህም ጎንደርን ለማፋለስ በኃይል ወልቃይት እና አካባቢዉን ፤ ከጎጃም መተከል አዉራጃን ፣ ከወሎ ሰሜን ወሎ ( ራያ…..) እንዲሁም በክልል ዉስጥ የብሀረሰብ አስተዳደር(ዞን) በማዋቀር እንዲሁም ከነዚህ አካባቢዎች ዉጭ ለሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን ምንም ዓይነት የፖለቲካ ፣የመደራጀት እና ራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብታቸዉ ተገፎ በራሳቸዉ አገር ምድር በስደተኝነት እና በባይታዋርነት ሲሳደዱ ፣ በተለያየ መንገድ ሲወገዱ ( ሲሞቱ) ለድፍን ሠላሳ ዓመት መንስዔዉ ማንትን መሠረት ያደረገ ትህነግ ኢህአዴግ አገር ነቀል ፖለቲካዊ ሴራ ነበር ፡፡

የሚያሳዝነዉ ግን ዛሬም እንደ ትናንቱ ህዝብ እና አካባቢ ኢትዮጵያን ለማክሰም የሚሰራ የጥፋት ቤተ ሙከራ መሆኑን ባለመረዳት ፍትህ እና ርዳታ ከዚሁ በኃይል ከሚያስገብረዉ እና ከሚያሳድደዉ ትህነግ-ኢህአዴግ ፍትህ እና ዕርዳታ እየጠየቀ መሆኑ ነዉ ፡፡

ለመሆኑ ከላይ በተጠቀሱት የኢትዮጵያ ግዛቶች በምቀኝነት እና በዕብሪት የተቀሙት እና ሌላ ታሪካዊ እና መልካ ምድራዊ መልክ እንዲኖራቸዉ የተፈለጉት መተከል ፣ የጎንደር እና የወሎ ግዛቶች በታሪክም ፤በስነ መልካምድር አቀማመጥም የነዚህ አካባቢዎች መሆኑ እየታወቀ እና አነኝህ አካባቢወችም በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት የማይደራደሩ እና የማይጠረጠሩ ሆኖ እያለ ጩኸቴን ቀሙኝ ጫጫታ ለሚያሰሙ ቀማኞች መልስ መስጠት ያለበት የነዚህ አካባቢ ኗሪወች ብቻ ሆነዉ መታየቱ ያስተዛዝባል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ ሁሉን ከዉጭ የምጠብቀዉ አስከ ምን ይሆን ?

ጎንደር ፣ ጎጃም ፣ወሎ ይሁን ሸዋ  ስሙን ካልሆ ማንቱን እና ይዘቱን መቀየር ለማቻላቸዉ ድብቅ እና ዕብቅ ፍላጎት ላላቸዉ በሆን ድፍን ዓለም ባይሆን ድፍን ኢትዮጵያዊ ያ ባይሆን የዓማራ ህዝብ ከላይ ከፍተኛ የማንነት እና ነፃነት ፣የዳር ድንበር ብሄራዊ ሉዓላዊነት ችግር ያለባቸዉ እና ለዘመናት የህዝብ እና አገር ችግር ማዋላጃ እና መናገጃ ለሆኑት በቃ ርስት ለባለቤት ብሎ እንደማለት ስጡን ፤መልሱልን ማለትስ ለምን ይሆን ፡፡

ማን የሰጠዉን ማን ይጠይቃል ፡፡ እንደሚታወቀዉ  በኢትዮጵያ ዳር ድንበር እና አፈር ቀርቶ በዜጎች ህይወት እና ሞት አዛዥ ናዛዥ የነበረዉነው እና የሆነዉን ትህነግ-ኢህአዴግን ዛሬም ፈቃድህ ከሆነ ስጠን ካልሆነ አንድ በለን እያሉ ጊዜ ማጥፋት ቀልድ ነዉ ፡፡

ከዚህም አልፎ በግፍ እና በዕብሪት ለሰላሳ ዓመታት የመከራ ናዳ የደረሰባቸዉን ኢትዮጵያ ፣ዜጎች እና በተለይም የዓማራ ህዝብ ስቃይ ሳይበቃዉ በማን አለብኝነት ለዳግም ወረራ ሮር ሰብቆ ፤ ዘገር ነቅንቆ ሲወር ራሱን እና አገሩን ከጥፋት ለመታደግ የሞት ሽረት ትግል ያደረገዉን የዓማራ ህዝብ ተጋድሎ እና በዚህም ነባሩን የኢትዮጵያ ግዛት ከመነጠል ያደነ ህዝብ ዋጋ እና ዕዉቅና መንፈግ ነዉ ፡፡

ከሰሞኑ የማንነት ፣ ወሰን እና የስራ ማስኪያጃ ገንዘብ ጥያቄ ጉዳይ እያሉ ለአንድ አካባቢ ህዝብ ጉዳይ አድርጎ ማየት የሚያም እና ሰዶ ማሳደድ ቢሆንም ለዚህ ኢትዮጵያዉያን እና  በተለይም ሁሉም ራሱን እና አገሩን ከገባርነት እና ከባርነት ቀንበር መላቀቅ የሚሻ የኢትዮጵያ ጉዳይ  በተባበረ ክንድ እንጂ ከዚህ በተቃራኒ ካለ ኃይል መዉደድ ስለማይሆን የተባሉት የወሰን እና ማንነት ጥያቄ የሚመለሱት በራሱ በህዝቡ ለህዝቡ በብርቱ የአንድነት ክንድ እና የታሪክ ግንድ ብቻ እጂ በኃይል የወሰደን ፈቃድ መጠየቅ እያዩ መዘፈቅ ነዉ ፡፡

የየትኛዉም የዓለም ህዝብ ማንነት ፣ነፃነት፣ ሉዓላዊነት እና ህልዉና በጥረት እና እንደ ብረት በጠነከረ አንድነት የሚገኝ እንጂ በዕብሪተኞች እና በስግብግቦች  በጎ ፈቃድ እና ችሮታ ኖሮም ፤ሆኖም አያዉቅም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር የ2007ን ምርጫ ጠቅልሎ ለመውሰድ ያደረገው መጀመሪያው ርምጃ ነው!!! (አንድነት ፓርቲ )

በኢትዮጵያ እና በራሱ ጉዳይ ሁሉም ዘብ የሚቆም እንጂ እንደ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች አንድ ጋት የኢትዮጵያ ግዛት ሆነ አንድ ዜጋ የአንድ አካባቢ እና የአንድ ሠዉ ችግር አድርጎ ማለፍ ዛሬ አገር እና ህዝብ እየከፈለ ያለዉን ዋጋ ማሳነስ ነዉ እና አንድ ጋት የኢትዮጵያ ግዛት ሆነ አንድ ሠዉ የሁላችንም ጉዳይ መሆኑን ነግ በእኔ ብሎ በትኩረት ማየት ያስፈልጋል ፡፡

ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛቶች እና ዜጎች የኢዮጵያ የነበሩ እና ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉ ከማንም በላይ ለህዝብ እና ለታሪክ መተዉ አለበት ፡፡ ታሪክን በማሳከር ዕዉነተኛ የአገር ገጽታን እና ነባር የዜጎችን ማንነት ለማዛባት መድከም ጥፋት እንጂ ዕድገት እና ህልዉና ስለማይሆን የኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ዕንቅፋት እና ጋሬጣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ስለሚያደናቅፍ ከመነቃቀፍ ለአንድነት እና ለዕዉነት መደጋገፍ ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡

“አበዉ ዶሮ ከቤት ሲኖር ቆቅ ከዱር ይያዛል “እንዲሉ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እና የዜጎች የማንነት እና ነፃነት ጉዳይ በተባበረ የአንድነት ክንድ ዕዉን ሲሆን ያኔ እንኳን ዓለም ሠይጣን ዕዉቅና (ያምናል) ይሰጣል ፣ ገንዘቡም ከአገር ዉስጥ ቀርቶ ከዓለም ይጎርፋል አለህ የምሠተዉ  (ለራሱ ሲል) ዋናዉ ነገር እንደያዙ መጓዙ ነዉ ፡፡

እናም ለወልቃይት፣ ለራያ……..ዕዉቅና .መስክር.፣ ለስራ ማስኪያጃ ገንዘብ ይለቀቅ…..እያሉ ቀማኛን በመጠየቅ መባዘን ጊዜ ማጥፋት ብቻ ሳይሆን የደም እና አጥንት ፣ የአካል እና የህይወት ዋጋ ተከፍሎ የተገኘን የብርቱ ተጋድሎ የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሞት ሽረት ዉጤት(የተመለሰ ማንነት እና ዳር ድንበር)  ለጠላት አሳልፎ መስጠት እና መንበርከክ እንዳይሆን በእጂ የገባን ድል በአላፊ እና ጠፊ ጉዳይ መርሳት እና መዘናጋት አያስፈልግም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Alem

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share