የአማራ ክልል የጦርነት ውሎ፣ ሐሙስ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ/ም – ግርማ ካሳ

ህወሃት ትጥቅ ባልፈታበት፣ የኦነግ ታጣቂዎች በነ ከሚሴ በስፋት እየተንቀሳቀሱ ባለበት፣ በወለጋ ያሉትም ጠምንጃ ባልዘቀዘጉበት እና ህዝቡን ለአደጋና ለእርድ ለማጋለጥ፣ “ትጥቅ እናስፈታለን” በሚል በአማራ ክልል ላይ ተረኞቹና ዘረኞቹ እነ አብይ አህመድ የጀመሩት ጦርነት ስድስት ቀናት አሳልፎ ሰባተኛ ቀን እየገባን ነው፡፡

በጦርነቱ ንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች፣ ፋኖዎችና መኮንኖች ሳይቀሩ የአገዛዙ መከላከያ አባላት፣ ሞተዋል፡፡ “የለም ፣ ተበትኗል” ያሉት የአማራ ልዩ ኃይል ፣ አብዛኛው ብርጌዶች ከህዝብ ጋር ቆመዋል፡፡ የፋኖ መሪዎችን፣ ዋርካው ምሬ ወዳጆን፣ አርበኛ ሻለቃ መሳፍንትን፣ አርበኛ አጋዬ አዳማሱና ሌሎችን ለመያዝ፣ ከፍተኛ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ኃይል አሰማርተው ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራዎች አልተሳካላቸውም፡፡ በርካታ የመከላከያ አባላት ህዝብ ላይ አንተኩስም እያሉ የተወሰኑ ጥለው እየሄዱ ነው፡፡ የተወሰኑ አዛዥ አዋጊዎቻቸውን አንታዘዝም እስከማለት ደርሰዋል፡፡ የተወሰኑ ከጀርባ አልተዋጋችሁም ተብለው ተገድለዋል፡፡ በብዙ ቦታዎች በአጀሬ ጃኖራ፣ በአንጾቂያ ገምዛ፣ በሸዋ ሮቢት ፣ በደብረ ሲና ፣ በማጀቴ በተደረጉ ከፍተኛ ውጊያዎች የአገዛዙ ታጣቂዎች ከፍተኛ ሽንፈት አጋጥሟቸዋል፡፡ የያዙት ከባባድ መሳሪያዎቻቸው በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም፣ ከሽንፈት አላዳናቸውም፡፡

አብይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ አሁንም ከግትርነታቸው አልተመለሱም፡፡ አሁንም የመከላከያ አባላትን፣ ሲያጎርሳቸው በነበረው ህዝብ ላይ እንዲተኩሱ እያደረጓቸው ነው፡፡ ከህዝቡ ጋር ደም እያቃቧቸው ነው፡፡ የአማራ ብልጽግና የሚባሉት የአማራ ክልል መንግስት ነን ባዮች፣ ክልሉን ለቀው አዲስ አበባ ሄደዋል፡፡ ይልቃል ከፍያለ መልቀቂያ አስገብተዋል ነው የሚባለው፡፡ ጀነራል አበባው ታደሰ አብይ ማኖ አስነክቶት፣ ተጠቅሞበት፣ በህዝብ አስጠልቶት አዋርዶ ወደ ጎን ጥሎታል የሚል ጭምጭምታ አለ፡፡ በብልጽግና ውስጥም ሰዎቹ ውስጥ ውስጡን አብይ አህመድ መናገር ፈርተው አፋቸውን ዘግተዋል እንጂ ትልቅ ፍርሃት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ከፍተኛ አመራሮቾ ቤተሰቦቻቸውን ከአገር ማስወጣት ጀምረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀጥታ - ምን እናድርግ? ታየ ቦጋለ ዝምታቸውን ሰበሩ በእነ ታማኝ ፊት | የቀጥታ ስርጭት ከዋሽንግተን ዲሲ |

እነ አብይ አህመድ የለኮሱት ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጦርነቱ ሕዝባዊ ጦርነት እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የህዝብ ፣ የገበሬ ሰራዊት አባላት መሳሪያዎቻቸውን ወልውለው፣ ትጥቅ ሊያስፈታ የመጣ ወራሪ እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም ብለው ተነስተዋል፡፡ አገዛዙ ሲያቀብጠው የተኛውን አንበሳ ነው የቀሰቀሰው፡፡ የአገዛዙ ታጣቂዎች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ በአማራ ክልል ያሉ መንገዶች በህዝቡ መዘጋት ጀምረዋል፡፡ የአማራ ኃይሎች በነፍጥ ራሳቸው ለመከላከል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ፣ መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ/ም ተጀምሮ የነበረውንና በበዓላት ምክንያት እንዲቆም የተደረገው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዘመቻ እንደገና ተጀምሯል፡፡ ከአዲስ አበባ ደሴ ፣ ከጎንደር ጠለምት ፣ ከጎንደር ባህር ዳር ያሉ መንገዶች ተዘግተዋል፡፡ በጎንደር፣ በዳባት፣ በደባርቅ፣ በሽዋ ሮቢት፣ በደብረ ሲና፣ በማጀቴ በመሳሰሉ ከተሞች ህዝብ ተቃውሞዉን አስምቶ የአማራ ኃይሎች ከተሞቹን የተቆጣጠረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

የብርሃኑ ነጋ ኢዜማን ጨምሮ አንዳንድ አካላት በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት እንዲቆምና ውይይቶች እንዲደረጉ ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ መልካም ነው ውይይት፡፡ ሆኖም ችግሩ ሰላም የሚፈልግ አይደለም አራት ኪሎ የተቀመጠው፡፡

የአማራ ኃይሎች “እነርሱ ሊያጠፉን መጡ እንጂ፣ እኛ አልሄድንባቸውም” በሚል፣ የአብይ አገዛዝ በአማራ ክልል ለጥፋት ያሰማራቸውን ታጣቂዎች ካስወጣ፣ አማራዉን ትጥቅ እናስፈታለን ያለውን አዋጅ ከሻረ፣ ያሰራቸው፣ ከ35 አመት ሺህ በላይ ሰላማዊ አማራዎችንና ፋኖዎች ከፈታ፣ በሌሎች የአማራ ማህበረሰብ በሚጠይቃቸው መሰረታዊ ጥያቄዎቹ ዙሪያ ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ እየገለጹ፡፡

“ውይይትና መነጋገር” የሚሉ አካላት ፣ የአገዛዙ መደለያና ማዘናጊያ መሳሪያ መሆን የለባቸውም፡፡ ለማያዋጣ ነገር ራሳቸውን ባያዋርዱ ጥሩ ነው፡፡ በርግጥ ለእውነተኛ ውይይት ቁርጠኝነት ካላቸው፣ አንደኛ በግልጽ ያድርጉት፡፡ ሁለተኛ ሰላም የማይፈልገውን፣ ሰላም ባለበት ቀውስና ግጭት እንዲኖር እያደረገ ያለው፣ ቀውስና ግጭት ጠማቂውን በጣም ክፉና ጨካኝ፣ አታላይና ጸረ ህዝብ የሆነውን የአብይ አገዛዝን፣ ከቻሉ ማሳመኑና ማግባባቱ ላይ ይስሩ፡፡ ለቀባሪው አደሩት እንደሚባለው፣ ሰላም የሚፈልገው ማህበረሰብ፣ እንዴት ስለሰላም ሊመክሩትም ሆነ ሊያግባቡት ይመጣሉ? ብርሃኑ ነገም በኢዜማ ስም መግለጫ ከሚያወጣ፣ አብሮ አይደለም እንዴ ከአብይ አህመድ ጋር የሚያመሸው የሚውለው፣ የረጅም ጊዜ የትጋ=ግል አጋሮቹን እንደ አንድርጋቸው ጽጌንና ን ዓምን ዘለቀን ክዶ ? ለምን ተው እረፍ አይለው ? ህሊና ካለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ችግር አይፈታም አለ

የአብይ አህመድ አገዛዝ ህወሃቶችን ለመስበር የአማራ ኃይሎችንና የኤርትራ ወታደሮችን እንደተጠቀመው፣ አሁን ደግሞ እነ ጌታቸው ረዳን በመሸለምና በመሸላለም ፣ ለስልጣኔ ስጋት ነው ያላቸውን የአማራውን ማህበረሰብ ለመምታት እንዲያግዙት እየጣረ ነው፡፡ ህወሃቶች በአማራ ክልል እየሆነ ባለው ነገር ተከፋፍለዋል፡፡ በአንድ በኩል ፣ “በዚህ አጋጣሚ እነ ወልቃይትን እንይዛለን” በሚል፣ አብይ እየወሰደ ያለውን አሳፋሪ ተግባራት የሚያበረታታ ተግባር ብለው በመጥራት፣ ወታደሮቻቸውን ወደ ወልቃይት ድንበር፣ እንደገና የትግራይ ወጣትን ለመገበር እየተዘጋጁ ነው፡፡ በሌላ በኩል፣ በተለይም የአብይ ጦር ለስድስት ቀናት በተደረጉ ውጊያዎች ያስመዘገበውን ውጤት፣ ከነ ብርሃኑ ጁላ ፉከራ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ያልጠበቁት ሆኖባቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ ለአብይ ብለን እንደገና የአማራ ሃይሎችና ኤርትራዊያን ጦርነት እንዲከፍቱብን ማድረግ የለብንም በሚል ጣልቃ መግባቱ ላይ እያመነቱ ነው፡፡

በዚህም ሆነ በዚያ አብይ አህመድ ውጥኖቹ ሁሉ ወና እየሆኑበት ነው፡፡ ድንፋታው፣ ፉከራ የትም አላደረሰውም፡፡ የአማራ ክልል ተራሮች፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ወይንም ፓርላማ አይደለም እንደፈለገ የሚፈነጭበት፡፡

ሰውዬው፣ ላይ ላዩን መናፈሻ፣ ፓርክ እያለ አገር ስላም እንደሆነ ነው ለማሳየት እየሞከረ ያለው፡፡ የአንደኛውን ዙር የህወሃት ጦርነት ተከትሎ፣ መከላከያ ሰኔ 21 ቀን 2012 ዓ/ም ነበር ከትግራይ ለቆ የወጣው፡፡ መከላከያ ለቆ ወጣ ሲባል፣ ብዙዎቻችን ትልቅ ድንጋጤ ነበር የተሰማን፡፡ ለማመን ነበር የከበደን፡፡ ለምን እነ አብይ አህመድ በትግራይ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ህዝቡን ደብቀውት ስለነበረ፡፡ እያወቁ አገር ሰላም ነው ብለው ስለ ምርጫ ነበር የሚያወሩት፡፡ አሁንም እንደዚያው ነው እያደረጉ ያሉት፡፡ ኢቲቪ፣ ፋና ወዘተ አገር ሰላም እንደሆነ ሊያሳዩ ይሞክራሉ፡፡ ግን ወገኖች ነገሮች ከአብይ አህመድ ቁጥጥር ውጭ እየሆኑ ነው፡፡ የርሱ ሜዲያዎች ያለውን ሁኔታ ለመደበቅ ቢሞክርም፣ ጉዳዩ ሊደበቅ አይችልም፡፡ አልቻለምም፡፡ የአማራ ክልል ከዚህ በኋላ ለአብይ አህመድ አይገዛም !!!! አራት ነጥብ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ

1 Comment

  1. ግርማ ካሳ ብርሃኑ የተናገረውን አላጤንከውም መሰል ከመልካምነቱ ክፋቱ ያመዝናል ፋኖ በለስ ከቀናቶ 10% ሲሆን አብይ እንዳይቆጣው 90% አድርጎ ነው መግለጫ ያወጣው አማራውን ጥላቻ አሁንም መግለጫው ውስጥ ተካትቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share