1) ጦርነቱ
ላለፉት ስድስት ቀናት በአማራ ክልል የሚደረገው ውጊያ የሌላ ትልቅ ጦርነት እና አካል መጀመሪያ ነው። ጦርነቱ የተከፈተው የአማራ ክልል መዋቅርን ሙሉ በመሉ ለመቆጣጠር የተደረገው ሙከራ መክሸፍ ተከትሎ ነው። የአብይ አስተዳደር ከወራት በፊት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የእኔ በሚላቸው ሰዎች ቁጥጥር ውስጥ አድርጎ ለመቆጣጠር [domestication] ያደረገው ሙከራ አባ ሳዊሮስ የፈለጉትን ቦታ በማጣታቸው በጉልበት ቤተ ክርስትያኗን ለማንበርከክ ሞክሯል። የኦፕሬሽኑ ስትራቴጂ ሲከሽፍ ወደ ከፍተኛ የሀይል እርምጃ የተኬደበት ስሌት የሀይል እርምጃው በሚፈጥረው ሽብር ላይ የተመሠረተ ነበር። ሆኖም ሽብሩ የበለጠ ለተቃውሞ መነሳሳትን በመፍጠሩ ምክንያት አላማው በተፈለገው መልኩ ሳይሳካ ቀርቷል።
በአማራ ክልልም በተመሳሳይ መልኩ በልል የሀይል አጠቃቀም የደህንነት ተቋሙን እንደ ዋና መሳሪያ ይዞ የመዋቅር ቁጥጥር ለማድረግ ተሰርቷል። ኦፕሬሽኑ [ sabotage and subversion tactics ] በመጠቀም እንዲሁም ልዩ ወዳጅ እና የልዩ ጠላት ዳይኮቶሚ በመፍጠር የታቀደ የፖለቲካል ኮንትሮል ነበር። በዚህ ስትራቴጂ አብይ ትልቅ ድል አግኝቶ የክልሉን ኦውቶኖሚ መሸርሸር እና በከፊል ገባሪ አስተዳደር ለመፍጠር ችሎ ነበር።
ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ባልተጠበቀ መልኩ ከኤርትራ ጋር በፍጥነት ያደገው ተቃርኖ የአብይን የቁጥጥር ፍላጎት በከፍተኛ መጠን አሳድጎታል። ይህን ተከትሎ መዋቅሩ ላይ ፍጹማዊ ቁጥጥር [Absolute control] ለመያዝ ተንቀሳቅሷል። የቁጥጥሩ ዋነኛ አላማ በመጀመሪያ የአማራን ፖለቲካ እና አቅሞቹን ማኮላሸት እና ፍጹም ገባሪ ማድረግ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ክልሉን የውክልና ጦርነት ባለቤት አድርጎ የውጊያ መነሻ ሜዳ [staging area] ማድረግ ያለመ ነው።
ይህን አላማ ለማሳካት የአማራ ክልል አስተዳደርን የምስለኔ ሚና ያለው [Vasal state] እንዲሆን ሞክሯል። ሆኖም ይህ ውሳኔ የውስጥ ተቃርኖ ከመፍጠርም ባሻገር ለውሳኔው መተግበር ልዩ ሀይሉን እና ፋኖን በጠላትነት መበየኑ አደገኛ መዘዝ ነበረው። የክልሉን አስተዳደር በፖለቲካዊ እና የደህንነት መሳሪያዎች ለመቆጣጠር የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ከፍተኛ ሀይል ተጠቅሞ ለማንበርከክ እየሞከረ ይገኛል። [ Due to a failure of the original plan of grand cooption, a swift transition from administering soft power toward hard power measures, using overwhelming military force, has undertaken.] እንደ ከዚህ በፊቱ ከፍተኛ ሀይል ተጠቅሞ አሸብሮ የማስገበሩ አላማ እጅግ ወደ ተባባሰ ተራዛሚ ግጭት እና ተደራራቢ ተቃርኖ እያደገ ይገኛል።
ሆኖም ይህ ውጊያ ከላይ እንደተጠቀሰው አማራ ክልል ተጀምሮ እዚያው የሚጠናቀቅ ሳይሆን ሌላ ታሳቢ ኮንቨንሽናል ውጊያ ማድረግን ታሳቢ አድርጓል።
2) ለጦርነቱ ምላሻችን
የአማራ ህዝብ በዚህ ወቅት ተገዶ በገባበት ጦርነት መንትያ አላማ አንግቦ የሚታገል ይሆናል። አንድም የተጋረጠበትን ህልውና አደጋ መቀልበስ ሲሆን ሁለት ደግሞ የፖለቲካ አቅሙን አደርጅቶ የህዝቡን ፍላጎት በሚገባው ልክ በሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል ነው።
በዚህ አላማ እና ፍላጎት ልክ ለመንቀሳቀስ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን ባማከለ መልኩ ምክክሮች እና አደረጃጀቶች መፍጠር ይገባል። መፍጠን አለብን። ጊዜ የለንም ብቻ ሳይሆን ጊዜ ከእኛ ጋር ሆኖ አያውቅም በሚል መንፈስ በፍጥነት መስራት አለብን።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከፋሽሰት ኢጣሊያ ጀምሮ በተከታታይ በመጡ ፋሽቶች በተከፈተው ጦርነት የተጋረጠብንን አደጋ መቀልበስ እና የመጨረሻውን ጦርነት ለማድረግ \
ዝግጁ መሆን አለብን። ከዚህ በኋላ የምንጠብቀው መዳንም ሆነ የተሻለ ጊዜ የለም።
አዎ …. ጊዜው አሁን ነው !
ድል ለአማራ !
ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር