ተንኮል እና በቀል አገር “ነቀል ወይስ በቀል” …?

#image_title

ኢህአዴግ ከሶስት አሰርተ ዓመታት አስቀድሞ ከተበተነበት ሰብስቦ ፣ ከወደቀበት አንስቶ መንገድ መርቶ እጁን ይዞ ለማዕከላዊ ስልጣን ኮርቻ ያበቀዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የሰሜን ምዕራብ እና መኃል ኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን የሚዘነጋም ሆነ የሚካድ አይደለም ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ከዚያ በፊት ከተማ ላይ በ1960ዎች ህዝባዊ ለዉጥ እንቅስቃሴ ማግስት የበሄር ጭቆና ትግል በሚል በተለያየ አደረጃጀት የህዝብ ልጂ ካፋጁ በኋላ ማጣፊያዉ ሲያጥራቸዉ ዕግሬ አዉጭኝ ያሉት ከአዲስ አበባ አስከ ጎንደር እና ትግራይ በርሀ የታደገዉ ይሐዉ ህዝብ ነበር ፡፡

ነገር ግን ከ1983 ዓ.ም ግንቦት ሀያ ቀን ጀምሮ የጥፋት እና ፍጂት አዋጂ የታወጀበት ይኸዉ እጁ አመድ አፋሽ የሆነዉ ኢትዮጵያዊ ነዉ ፤ነበር ፡፡

በየትኛዉም ዓለም የራሱን አገር እና ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ የሚያገል የፖለቲካ ስርዓት እና ድርጂት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ከኢትዮጵያ ኢህአዴግ በቀር ፡፡

አዲስ አበባ እንደገባ ኢህአዴግ ብሄራዊ የህዝብ ዘብ የሆነዉን መከላከያ በትኖ የፓርቲ አግልጋይ  እና የፖለቲካ ስልጣን ማስጠበቂያ የሚሆን  አደረጃጀት ተመሰረተ፣ ገጠሩን ያማከለ ልማት በሚል የአዲስ አበባን ነባር እና ኗሪ በክልል አደረጃጀት እና ልማት ስም በተለይም ዓማራዉን ከአዲስ አበባ የነግፋት ተግባር ተከናወነ ፣ በከተማ ልማት ስም በከተማ ቦታ እና መሬት ልማት ማፈናቀል ፣ማግለል እንዲሁም የነበረዉን ስብጥር ለማዛባት ብዙ ተሰርቷል፡፡

ይህም በአንድ አገር የተለያየ የዜግነት ደረጃ እየወጣ ባለቤትነት እና ባይተዋርነት በተለያየ ማደናገሪያ ሽፋን ዜጎችን በማንነት ፣በባህል ፣ በስነ ልቦና ፣ በዕምነት እና ኢትዮጵያዊነት የተለያየ የፖለቲካ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲያርፍባቸዉ ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለአቶ አዲሱ አረጋ አድርሱልኝ - ገለታው ዘለቀ

ይህ ሁላ የሆነዉ በጥላቻ እና ቂም በቀል ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ህዝቦች የነበራቸዉን ጥልቅ ቁርኝት በመግታት ከፋፍሎ እና አንበርክኮ የስልጣን ጊዜን ለማራዘም ነበር ፡፡

ሆኖም ይህ ባጎረስኩ ተነከስኩ ሆኖ ዛሬም ብዙኃን ኢትዮጵያዉያን ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት በማንነታቸዉ የደረሰባቸዉ ዘርፈ ብዙ ጥቃት ( ማፈናቀል ፤ ስደት ፣ ዉርደት ፣ሞት ….) አልበቃ ብሎ ከእናት አገራቸዉ ኢትዮጵያ ለመለየት ባለአገሩን ከአገሩ የመንቀል  የጥፋት ጉዞ ቀጥሏል፡፡

 

አበዉ“ ጠላት በመቶ ዓመት  የወተት ጥርስ  ነዉ” እንዲሉ  ለዘመናት በዜጎች እና በአገር ላይ የደረሰዉ መከራ እና ግፍ ፍትህ ባልተገኘበት እና ተጠየቂነት ባልተረጋገጠበት ፣ወንጀለኛ ባልተጠየቀበት ፣ ተበዳይ ባልተካሰበት ሠፊዉ እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ  ዕምብርት የሆነዉን ዓማራ በተደጋጋሚ ለአመታት በሴራ ባዶ እጁን ሆኖ ራሱን እና አገሩን እንዳይከላከል የነፍስ ወከፍ መሳሪያ አዉርድ ማለት ከፀረ-ኢትዮጵያዊነት ተልዕኮ ዉጭ ሌላ አይሆንም ፡፡

ብዙኃኑን የዓማራ ህዝብ የርኩስ መዉጊያ በማድረግ ለስልጣን ጥም እና ምኞት የመከራ ዘመኑን ለማራዘም የሚደረግ ጊዜ ያለፈበት የፖቲካ ሸፍጥ በቃ አለማለት ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ከዓማራ ህዝብ ለይቶ ማየት ልጂ ለናቷ….አስተማረች እንዳይሆን ህዝብ በማፈናቀል እና በከንቱ ዉዳሴ መደለል በንግግር አገር በቀል በተግባር በሚደጋገምባት ፣ መግባባት እና ትምምን በሌለባት አገር እጂ ወደላይ “ተጨፈኑ ላሞኛችሁ  ” ለኢትዮጵያዉያን ለዚያዉም ለብዙኃኑ ዓማራ ህዝብ ለአገር መሰረት ፣ዕድገት እና አንድነት በተለያዩ ዘመናት ያደረገዉ አበርክቶት በክህደት እና በጥፋት መመለሱ ለዚህ ህዝብ በዚህ በ21ኛዉ ክ/ዘመን የሚመጥን አይደለም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen Amber

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  በወለጋ በተከታታይ ለሚካሄደው የአማራ ሕዝብ እልቂት ተጠያቂዎች የኢትዮጵያ ፌደራል መንንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው  - አክሎግ ቢራራ (ዶር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share