የማንኛውም ትግል መሰረት የገዥዎችን ማንነት፣ መነሻና መድረሻ ብሎም ዓላማ ማወቅና፤ ገዥዎች ሥልጣን ላይ ለመቆየት፤ ለነጻነትና ለአንድነት የሚደደረገውን ትግል የሚጠቀሙበትን ስልትና አጀንዳ ማክሸፍ ነው። ገዥዎችን ለመታገልና ለድል ለመብቃት ደግሞ በትግሉ ዓላማ ማመን፣ በራስ መተማመን መደራጅትና ብቃት ያለው መሪ መፍጠር ብቻ ሳይሆን ለመሰዋአትነት መዘጋጀት የግድ ይላል።
ለምሳሌ የኢትዮጵያ የዘመኑ ገዥዎች ወያኔዎች ”ትግራይ ሪፕብሊክ” ኦነጋዊ- ብልጽግና ደግሞ ”ኦሮሚያ” የምትባል አገር ለመመስረት የሚጠቀሙት፤ ኢትዮያዊነትንና አማራነትን ፤ ሲያስፍልጋቸው ነጥለው፤ ከላያ ደግሞ ጨፍልቀው ያጠቁታል። ኦሮሞን ከአማራ ፤ አማራን ከትግሬ፤ አማራን ከሊሎቹ ነገዶች ጋር፤ ከፋፍለው ያለ-ስም ስም እየሰጡ፤ በህዝቡ ዘንድ ባይሳካላቸውም ”ምሁር” ነኝ የሚለውን ርስ በርስ ያባሉታ። አንዳንዴም ስለ አንድነትና ስለ እኩልነት እየሰብኩ፤ በተግባር ግን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ሁለገብ ጥቃት ይፈጽማሉ። ለአገዛዛቸው ኢ-ፍታዊነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው መጣንበት ለሚሉት ጎሳና መንደር ተቆርቋሪ በመምሰል ”ሊያጠቁህ ነው! አንተን ስለሚጠሉህ ነው!” በሚል ህዝብን ለማጋጨትና ልዮነት ለመፍጠር በየመድረኩና በብዙሃን መገናኛዎች ሌት-ተቀን ይለፍፋሉ።
ስለዚህ ለኢትዮጵያዊነትና ለኢትዮጵያ፤ ለእኩልነትና ለዜጋዊ ፓለቲካ ቁሚያለሁ ወይም እታገላለሁ የሚለው ፤ የገዥዎቹን ማንነት በቅጡ ስይረዳና በጎሰኞች አጀንደ እየተጠለፈ፤ መርህና ጽናት አልባ በመሆኑ፣ እስከ አሁን ትግሉን አቅጣጫ የሚያሲዝ ድርጅትም ሆነ መሪ ማፍራት ስላልተቻለ፤ የወያኔንና የኦነጋዊ ብልጽግና የቤት ሥራ እየተቀበለን፤ በስሜትና በሆሆታ በመንጎድ ፤ እነሱ በቀደዱልን ቦይ እየፈሰስን፤ አሁን ካለንበት አጥፍቶ የመጠፋፋት ገደል ጫፍ ላይ ደርሰናል።
ባለፋት ዓመታት ገዥዎቻችን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳከምና ህዝብን የመከፋፈል ሴራ ከፋሽስት ጣሊያን የአምስቱ ዓመት ወረራ የቀዱትን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየተጠቀሙበት ይገኛል።
እንደ ምሳሌ ግራዚያን ለሙሰለኒ የጻፈው ደብዳቤ፣…
” ለእኛ ለጣሊያኖች የአቢሲኒያን ምድር ቅኝ እ’ዳንገዛ እንቅፋት የሆኑትና የሚታገሉን፤
1/ ምሁራን => ልብ ካለን… … እንደ አሁኑ ምሁር ዘርና ጎሳ የለውም፡፡ እንደ አሁኑ በገንዝብ የተሸመተ የምስክር ወረቀት የለውም። ኢትዮጵያ አገሩ ነች። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉም እኩል ሰውና ወገኑ ነው።
2/አማራ => ልብ ካልን መለስ ዜናዊ ሳይከልለውና ለከለለው ክልል ”አማራ” የሚል ስም ሳይሰጠው ፤ በዘመኑ አልገዛም ያለና በመንግሥታዊ አስተዳደር በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁሉ ዜጋ አማራ ነው። ለዚህ ደግሞ የአቶ አሰፋ ጫቦን መጸሃፍ ”የትዝታ ፈልግ” ማንበቡ በቂ ነው።
3/ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት => ልብ ካልን– – የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሺ ዘመናት የቆየ ተቋም በመሆኑና የህዝብን አንደነት ያለምንም ልዩነት በማስተሳሰሩ፤ እንደ ፋሽስቶች፤ በዘመኑ ገዥዎቻችንም ዘንድ እንደ ጠላት በመቆጠሩ ፤ መዳከምና መጥፋት አለበት ተብሎ ተወስኖበት እየተሰረ ነው። ለዚህም ነው ”የኦሮሚያና የብሔር-ብሔረስቦች ሲኖዶስ ” የተቋቋመልን። በነገራችን ላይ ይህ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን አቅም ለማወቅ የተደረገ ሙከራ፤ የኦነጋዊ ብልጽግና ከወያኔ ጋር የትግራይን ኦርቶዶክስ ለመነጠል የታቀደ የጠ/ሚ አብይ ”ሳይንሳዊ የመጀመሪያ የሙከራ ጥናት” ነው። ቀጣዩን አጀንዳ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።
4ኛ/ የኢትዮጵያ አርንጓዲ፣ ቢጫ፣ ቀይ፤ ሰንደቅ ዓላማ ለጣሊያኖች የኢትዮጵያዊያን ጥብቅ የአንድነት ምልክት መሆኑን ስለተርዱ ፤ ባገኙበት ቦታ ሁሉ ያቃጥሉትና ይዞ የተገኘውንም ዜጋ አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣት አልፈው ይገሉም ነበር። ልብ – እናድርግ ጣሊያን ቢያደርገው አይደንቅም ፤ ወያኔና ኦነጋዊ ብልጽግና የእንድነታችንና ለኢትዮጵያዊነታችን ምልክት ለሆነው ሰንደቅ ዓላማ ያላቸው ጥላቻ በርግጥም ከጣሊያን ይበልጣል። በቀሚስ መልከ የለበሱ እናቶችና አንገታቸው ላይ በማተብ መልክ ያስሩ ወገኖቻችን የህይወት መሰዋትነት ከፍለውበታል። እየከፈሉም ይገኛሉ።
ለዚህም ነው ካለፈው ታሪካችን በመነሳት ዛሬ ላይ በርግጥ ” እንዴት ለዚህ በቃን? ጠላቶቻችን እናውቃቸዋለን?” በማለት ለመጠየቅ የተገደድኩት። ታዲያ የጣሊያንን ወረራ የቀለበሰውና ጠራርጎ ሙጃ እያስበላ ያባረረው፤ አርበኛው ታጋይ መጀምሪያ የጠላቱን ማንነት በመገንዝቡና የተጠቀመበት የከፋፍለህ ግዛው ስልት በማክሸፋ ነው። ለምሳሌ እንደ አሁኑ ዘመን ” አማራ ታርደ! አማራ ተሳደደ! ኢትዮጵያን አፈረሷት! ኦርቶዶክስን ከፋፈሉት፡ መስጅዱን አፈረሱት፡ ቤት-ክርስቲያን ነደደ! የሚያደራጀን አጣን! ወዘተ —–” እያለ እያላዘነ ሳይሆን፤ መንግሥት በሌለበት፣ ራሱን በራሱ አደራጅቶ፣ መሪና ተመሪ ሆኖ፣ ቤት ንብራቴ፣ ልጀ ሚስቴ ሳይል፣ ለህይወቱ ሳይሳሳ፣ በመላው አገሪቱ ያለው ዜጋ፤ ተጠራርቶና ተናቦ ፤ ጎሳና ሃይማኖት ሳይለያየው፤ በዱር በገደሉ ስለተጋደለና ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞትን ስለመረጠ ነው።
የትላንትናዎቹ ወያኔዎችም ሆኑ የአሁኖቹ ባለተራ ብልጽግናዎች የሁለቱም ዓላማ ከቻሉ ህዝብን እያባሉ መግዛት፤ ካልቻሉ ደግሞ በየፊናቸው በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ እነሱ የሚገዙት አገር ማዋለድ መሆኑ፤ አሁን ያለበትና የሚሰሩት ሴራ ገሃድ አድርጎታል። ታዲያ ከዚህ ላይ መሰመር ያለበት ወያኔ ፤ ወያኔ እንጅ በምንም መስፈርት ቢሆን የትግራይን ህዝብ እንደማይወክል ሁሉ፤ ባለተረኞቹም ኦነጋዊ ብልጽግናዎች በኦሮሞ ስም ስልጣን ይዘውና በስሙ ይነግዱበት እንጅ ፤ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ስብዕና አይወክሉም።
ትላንት ወያኔ በየጎሳው በመለመላቸው በምስለኔዎች እየተጠቀመ እንደ ገዛ ሁሉ፤ ኦነጋዊ ብልጽግናዎችም፤ እንደ ጡት አባታቸው ተመሳሳይ መንገድ ተጠቅመውል። በ’ርግጥ የአማራ ምስለኔዎችን የተለዩና ከሰው ልጅ የተፈጥሯዊ ባህሪ ውጭ የሚደርጋቸው፤ በጠላትነት ተፈርጀው ሳለ ”ጠላቶች ነን” ብለው ተቀብለው፤ የገ’ዛ ወገናቸውን ማረዳቸውና ማሳረዳቸው ሲሆን፤ ነገ ልጆቻቸውና የልጆቻቸው አገር አልባ እንድሚሆኑ እያወቁ”የህዳር እህያ” መሆነቸው ነው።
ወያኔና ኦነጋዊ-ብልጽግና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ የሚያደርጋቸው ”አማራ ኢትዮጵያ ” በሚሉት ህዝብ ላይ ያላቸው ዓመለካከትና የሚፈጽሙት ግፍና በደል ብሎም ፤ ከሌላው ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲፈረጅና የዘር ማጽዳት እንዲፈጸምበት ህግ-መንግሥት አርቅቀውና መዋቅርና ዘርግተው ጠንክረው መስራታቸው ነው።
ከዚህ ላይ በመቶ ሺዎች ከጨረሰውና ሚሊዮኖችን ቤት አልባና ተፈናቃይ ካደረገ የሁለት ዓመቱ ጦርነት በኋላ ፤ እንዴትና በምንስ ተዓመር ነው ”የመቀሌው ወያኔና የአዲስ አበባው ብልጽግና ” ሰላም ያወርዱት፤ ብሎ የሚገረም ካለ፤ የጠ ሚ አብይ አህመድ አገዛዝ ከአራት ዓመት በፊት ”ለኦሮሞ ነጻነት እንታገላለን ” የሚሉትን ድርጅቶችና ፓርቲዎች በሚስጢር ናዝሪት ላይ ሰብስቦ እቅዱን ያስተዋወቀብትን ለግንዛቤ ያህል ከዚህ ላይ ማንሳቱ እስፈላጊ ነው። መልዕክቱ ሲጨመቅ ፤ ”—- የምንሰራው ስራ ሳይንሳዊ መሆን አለበት። ለምሳሌ እናንተ የፊንፊኔን የባለቤትነት ጉዳይ ታነሳላችሁ። እዎ!
…
[Message clipped]View entire message
One attachment • Scanned by Gmail