April 10, 2023
5 mins read

ሥራ መፍታት አገር ለመፍታት እንዴት ምክነያት ይሆናል  ?

Untitle56666564 1 1

ኢትዮጵያ  እና ህዝቧ በታሪካቸዉ ጠላቶቿ ሳይቀሩ የሚመሰክሩት  ብዙ ዕዉነታዎች ይጠቀሳሉ ፡፡

ለዚህም አገረ መንግስት ለመመስረት እና አገር ለማፅናት ፣ ዳር ድንበር በማስጠበቅ፣ ቅዥ ግዛትን አጥብቆ በመታገል ፣ ለነፃነት እና ለብሄራዊ እና ክፍለ ዓለማዊ ነፃነት ተጋድሎ ትልቁን ሚና በመጫዎች የባርነትን እና ተገዥነት ቀንበር በመስበር የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ናቸዉ ፡፡

እኮ እንዲህ ዓይነቱን ኢትዮጵያዉያን ጊዜ አልፎ በተተካ የኢትዮጵያዉን እና አገር ባለዉለታዎች በበላይነት እና የቅዥ ግዛት ናፋቂዎች እና ተላላኪዎች ሲካዱ እና ሲዋረዱ የዘመናት ክፉ ልማድ ሆኗል ፡፡

ካሳለፍናቸዉ የመከራ እና የጨለማ ዘመናት ሳንማር እና ሳንመክር በአፈ ጮሌዎች የሚጫን የእንወቅልህ እና እንናገርልህ አለንልህ ማታለል እና መደለል መልኩን መቀያየር አገር እና ህዝብ በአገሩ እናበራሱ ተስፋ እንዲቆርጥ ግድ ሆኖበታል ፡፡

ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ ቁስሉ ሳይሽር፣ ዕንባዉ ሳይተበስ ፣ ደሙ ሳይደርቅ  ሳይደርቅ ፣ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ የከፈሉት ዋጋ ከምንም ሳይቆጠር ህይወታቸዉን  የሰዉት ከህዝብ ትዉስታ እያሉ ዳግም አገር ለመፍታት የአንድን ህዝብ ራሱን እና አገሩን ለመከላከል ያለዉን ተፈጥሯዊ መብት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መግፈፍ ድርጊት ከስራ መፍታት የሚመነጭ አገር የማስፈታት አካል ሆኗል ፡፡

ይህም በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ ታሪካዊ የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች ጥርስ ዉስጥ የመግበታቸዉ የዘመናት ጥላቻ እና ቂም በቀል ነዉ ፡፡

ምዕራባዉያን በምስራቁ ዓለም እና በኢትዮጵያ ላይ በጥርስ ከማኘክ የዉስጥ ጉዳይን በማወክ ሳይደክሙ ማኘክ ምኞታቸዉን ያደረጉ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያን ለመለያየት እና ለማፋታት ከዉስጥ እና ከዉጭ ፤ ከቅርብ እና ሩቅ ሆነዉ የሚያደርጉት ሴራ ኢትዮጵያን ከድጥ ወደ ማጥ እንዳይሆን ኢትዮጵያን ከማስፈታት እና ከመፍታት ጠላትን እና ፀረ -ኢትዮጵያ የሆኑት የሕዝብ እና የአገር አንድነት ጠንቆችን ተስፋ ማስፈታት እና አደብ ማስገዛት ከፍተኛ ስራ የሚደረግበት ወርቃማ አጋጣሚ እና ጊዜ ነዉ ፡፡

እናም ጠላት  የጥፋት እና የክፋት ስራዉን ያቆመ ወይም ስራ የፈታ በመሰለዉ ቁጥር  አገርን እና ህዝብ ለማፋታት እና ተፈጥሯዊ ማንነቱን እና ኢትዮጵያዊነቱን ከኢትዮጵያ ለማፋታት ፣ቀኙን ከግራዉ ለመለያየት መጣር ፀረ ኢትዮጵያዊነት አባዜ መቆም ለመላ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሚበጂ ነዉ ፡፡

ዛሬ በዉጭ እና በዉሥት አፍራሽ ኃይሎች ሴራ በመድማት እና በመቁሰል ላይ የሚገኙትን ህዝብ እና አገር አሜን ባይ እና ተንበርካኪ በማድረግ ጠላትን ማድለብ እና መንከባከብ ለኢትዮጵያ ቀርቶ  ለአፍሪካ ጠንቅ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዉያን መረዳት አለብን ፡፡

የኢትዮጵያዉያን እና የኢትዮጵያ የአንድነት እና የህልዉና መስተጋብር ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ ጠላቶች የጥፋት ስራ መፍታት  ጊዜ እየተሰጠዉ ለአገር መፈታት ምክንያትነት ቀርቶ  የጠላትን ሴራ መስበር እና እና የኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያን ክብር እና ዳር ድንበር ማስከበር ትኩረት እና ተግባር መጠናከር ይገባል ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

 

Allen Amber !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop