የኦህዴድ ብልፅግናና ከበስተጀርባ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ “ትርክት፣ አላማና ግብ”

ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል

የኦህዴድን ብልጽግናን እንደ ሥራ አስፈጻሚ ሾሞ ሐገሪቱን አሁን እያስተዳደር የሚገኘው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ፣ ጥርሳቸውን በኦሮሞ ፖለቲካ ያወለቁትን እነ ሌንጮ ለታንና ዲማ ነገዎን፣ የወያኔን አንጋፋ ተላላኪ አባ ዱላ ገመዳን፣ የኦሮሙማን “የኬኛ” ዘመቻ ለማሳካት ብላችሁ ከኋላችን ተሰልፋችሁ የሚያስፈልጋችሁን ጥቅምና ጥቅም እያገኛችሁ እርዱን የተባሉትን በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግንና በስሩ የሚንቀሳቀሰውን የሸኔ ወታደራዊ ግንባር፣ ጁዋር መህመድ ከተቀላቀለው በኋላ ክብደት እየጨመረ የመጣውን ኦፌኮንና፣ በውጭ ያሉትን አክራሪ የኦሮሙማ ልሂቃኖች ክምችትንና አማካሪዎችን ያካትታል። ለዛም ነው ዳውድ ኢብሳም ሆነ ጃዋር መሃመድ (የአብይ አህመድ አንደኛ መንበር ተቀናቃኝ) የቆፈሩት የቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ መሽገው፣ መጪው ምርጫ ደርሶ ለመንበሩ ለመፎካከር አንገታቸውን ብቅ የሚያደርጉት። “እሳት ቢዳፈን የጠፋ ይመስላል” እንዲሉ።

ግልጥ ያለውና መሬት ላይ ያለው ሃቅ፣ የኦህዴድ ብልፅግናና ከበስተጀርባ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ ትርክትና ወቅታዊ አጀንዳ እንደሚቀጥለው ነው። መቆመር (Gamble)ማስፈራራት (Blackmail)ማደናገር (Confuse)ማሳመን (Convince)

1ኛ) የመጀመሪያው ወሳኝ አጀንዳ ምንድነው? አማራንና ትግራይን የማያልቅና የማያቋርጥ ጦርነት ወስጥ መዝፈቅ። እንዴት? ወልቅያትንም ሆነ ራያን “በሬፈረንደም” አሳቦ ወደትግራይ ማጠቃለል። አማራ በሪፌሪንደም አልስማማም ብሎ እንዳያፈንግጥ፣ የልዩ ሃይል ስልጠናውን እንዲያቆም በፊት እንደተደረገው ጫና ማድረግ። የወያኔ ሃይል በፊት እንዳለ ተጠንክሮና አሁንም እየተዘጋጀ በመሆኑ ድሉ ወደነሱ እንዲይደላ ማስደረግ። ለምን? አንደኛ፣ ሁለቱም ቀንደኛ የሚላቸው የሴም ጠላቶቹ እርስ በእርሳቸው ይጨራረሱለታል። ሁለተኛ፣ ኦሮሙማ የአማራና ትግሬ (የሴም) ሃይል ሳያሳስበው፣ ሌሎቹን ክልልሎች ሁሉ በመቆጣጠር በፖለቲካ፣ በኤኮኖሚና፣ በሚሊታሪ ወሳኝ የሆነ ቦታ ይይዛል።

2ኛ) ባለፉት አራት አመታት እንዳደረገው ሁሉ፣ ኦሮምያን መጀመሪያ ከአማራ፣ ቀጥሎ ደግሞ ከሌሎች ብሔረሰቦች ያጠራል። ባለፉት አራት ዓመታት ባካሄደው አማራን ከወለጋ የማፅዳት ዘመቻ ትልቅ ስኬት አምጥቷል። አሁን ደግሞ የአዲስ አበባን ዙርያ ጠፍንጎ በመያዝ መውጭያ መግቢያውን እየተቆጣጠረ ነው። የአዲስ አበባ አስተዳደር ከኦሮሙማ ቁጥጥር እንዳትወጣና፣ የከተማ ቦታዎችም ሆኑ ንብረቶች ሁሉ በኦሮሞሙማ ብቻ እንዲጠቀለሉ ይሰራል።

3ኛ) ሀገሪቱን አሁን የሚቆጣጠረው የኦህዴድ ብልፅግና በመሆኑ፣ ላሚቷም ኦሮምያ ክልል በመግባቷ፣ ማንኛውንም ትላላቅና ወሳኝ ፕሮጀክቶችን ኦሮምያ ወስጥ እንዲተገበሩ ያደርጋል። ከነዚህም ውስጥ በአለም ግዙፍ የሆነ አየር ማረፊያ፣ የኦሮሙማ ቤተ መንግሥት፣ ፈጣን ጎዳናዎች፣ የእርሻ ፕሮጀክቶች እንዲተገበሩ አድርጓል። ባንኮችንና ባለ ሃብቶችን በኦሮሙማ መንግሥትና ባለሃብቶች ቁጥጥር ሥር እንዲገቡም እያደረገ ነው።

4ኛ) ከዚህ በላይ ያሉትን አላማዎች ማሳካት ካልቻልን፣ ልዩ ሃይላችንንና ታናሽ ወድንድማችን ሸኔን በልካችን በሰፋነው መከላከያችን ጎን አሰልፈን አዲስ ሐገር እንመሰርታለን። አየር ሃይሉም፣ የምድር ጦሩም በኛው ቁጥጥር ሥር ነው።

እንግዲህ፣ ከላይ የተጠቀሱት አጀንዳዎች፣ ግልፅ በሆነ መንገድ በኦህዴድ ብልፅግናና እሱንው ከበስተጀርባ ሆኖ በሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ እየተገበሩ ይሚገኙ ጉዳዮች ናቸው። የኦህዴድ ብልፅግናና ፖሊት ቢሮው፣ ለጊዜው አግኝተንዋል ያሉት የፖለቲካ ሀይል ክፉኛ ልባቸውን ስላሳበጠው፣ ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያሳዩት ቅጥ ያጣና የወረደ ንቀት ምልክት ነው።

የኦህዴድ ብልፅግናና እሱንው ከበስተጀርባ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ፣ ቅድመ አጀንዳው “አማራ የኦሮሞ ጠላት” ነው ይሚል ነው። ለምን?

መልስ፡ አማራ ትምክህተኛ ነው። አማራ “ነፍጠኛ” ነው። አማራ “ፅንፈኛ” ነው። ኦርቶዶክስ ደግሞ አማራ ነው። ግዕዝም አማራ ነው። አማርኛም የአማራ ነው። ፊደልም የአማራ ነው። የዘመን መቁጠሪያውም አማራ ነው። ስለዚህ እነዚህ ይተጠቀሱት በሙሉ፣ እኛ አጥብቀን ከምንጠላው የሴም ነገድ ጋራ ቢያያዙም፣ “ሻቢያም ሆነ ወያኔ ባስተማሩንና በፃፉልን ትርክት” መሰረት ግን፣ ዋናው ጠላታችን አማራው ነው። ይህንን ስንል የሴም ነገድ ባላንጣችን አይደለም ማለታችን አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ አይደለም" - አብርሃ ደስታ (ከአዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ)

ታድያ ምን ይሁን ትላላችሁ? ለሚለው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ መልስ …

የአማራን አከርካሪ ሰብረን፣ የነገደ ሴምን ታሪክ አጥፍተን፣ ኦሮምያን በምትመስል ኢትዮጵያ፣ የነገደ ኩሽ ሐገር እንመሰርታለን። ካልተቻለም፣ ሁሉንም ንብረት “በኬኛ” ፍልስፍና ኦሮሚያ ውስጥ አሰባስበን ለብቻችን ሐገር እንሆናለን።

እንዴት? የሴም ነገድን ከፋፍለንና እርስ በእርስ አዋግተን የዘላለም ጠላቶች እንዲሆኑ ማድረግ። መሰረተ ልማታቸውን ሁሉ በተደጋጋሚ ለማወደም እንዲቻል፣ ወልቃይትንና ራያን እንደገና ለትግራይ አሳልፎ ሰጥቶ እነዚህ የሴም ነገዶች የማያባራ ጦርነት ውስጥ እንዲዘፈቁ ማድረግ። ኦርቶዶክስ በመሃል እንደሚሰነጠቅ በትንቢተኞቻችን ካስለፈፍን በኋላ ኦሮሙማ የሚመራው ተቀናቃኝ የኦርቶዶክስ ሲኖዶስ፣ በብሔር ብሔረሰቦች ሽፋን ማቋቋምና ቀስ እያሉ ማጥፋት። ከዚያም ይህን ቆሞ ቀር ኦርቶዶክስ የምዕራባውያን ለጋሾቻችንን ለማስደሰት ወደ በፕሮቴስታንት ሀይማኖት መተካት፣ ቋንቋውን፣ ፊደሉንና የዘመን መቁጠሪያውን ወደ ኦሮምያና ወደ ላቲን መቀየር። በመጭረሻም አዲስ አበባን ወደ ፊንፊኔ በመለወጥ፣ በኦሮምያ ሕገ መንግሥት መሰረት የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ የሚመራት፣ የሚገዛት፣ የሚበለፅግባትና ባለቤት የሆነባት፣ የኦሮምያ የሆነች ኢትዮጵያ መመስረት ።

ለመሆኑ ይህ ይቻላል? በደምብ ይቻላል እንጂ። ለአምስት አመት ያካሂድነው የፖሊሲና የፕሮፓጋንዳችንን ውጤት ማየት ብቻ በቂ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ በአንጋፋዎቹ የኦሮሞ የትግል መሪዎች አስተባባሪነት (የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ መስራቾች) ሁሉም የኦሮምያ የፖለቲካ ቡድኖች ኦሮምያን አስቀድመው በአንድነት ቆመዋል። አማራን በቅድሚያ “ኦሮማራ” በሚል መርሆ አወናብደን፣ ከዚያም ሊፎካከሩን የሚችሉትን ጄኔራል አሳምነውንና የዶ/ር አምባቸውን ቡድን ከጫወታ ውጭ በማውጣት ቁማሩን ከበላን በኋላ፣ ላሚቷን ኦሮምያ ውስጥ አስገብተን ማለብ ጀመርን።

ወያኔ ስልጣናችንን ካልተሻማሁኝ ብሎ ጦርነት ቢከፍትብንም፣ ደም ያቃባንውን የሴም ወንድሙንና ከጎኑ ያለውንና አውቀን ያስወረርነውን የአፋርን ሕዝብ አሰልፈን አፈር አበላነው። አሁን የኢትዮጵያ መከላከያን የሚመራው፣ ከመከላከያ ጀምሮ እስከ ጠ/ሚ ያለው ኦሮሞ ነው። ሁሉም ክልልሎች የኦሮሙማ ተላለኪዎች ናቸው። ሿሚዎችም፣ አውራጆችም፣ አሳሪዎችም። ገዳዮችም አሁን እኛው ነን። የአማራ ክልልን ለማስፈራራት ሰሞኑን በባህርዳር የላክናቸውን የጦር አይሮፕላኖችንና ሄሊኮፕተሮች ማየት ብቻ በቂ ነው። ኦሮምያ ልዪ ሃይሏንም፣ አማራን ከኦሮምያ የሚያፀዳላትን ሸኔንም፣ የሐገር መከላከያውንም የምትቆጣጠር ኦሮምያ በአሁን ወቅት በምስራቅ አፍሪቃ ማንም ሊወዳደራት የማይችል ሃያል ሐገር ሆናለች። አዎን ሐገር። ለምን አጣዬ ለ10 ጊዜ ስትወረርና የወለጋን የዘር ማፅዳት ዘመቻ አላስቆማችሁም እንደዚህ አይነት ሃይል ካላችሁ? ለሚለው ጥያቄ፣መገመት ካልቻላችሁ መልሱን በቅርቡ ታገኙታላችሁ። እየተስፋፋን ነው ጓዶች። ማንም አያቆመንም።

በኤኮኖሚም ቢሆን፣ ላሟ ኦሮምያ ወስጥ በመግባቷ፣ ሁሉም የሚታለበው የኢትዮጵያ ሀብት ኦሮምያን ለማሳደግ ይወላል። በጠ/ሚንስትራችን፣ አ/አበባ (የወደፊቷ ፊምፊኔ) ወስጥ የሚደረገው ሁሉም ፕሮጀክት የኦሮሙማ ይሆናል። በአፍሪካ የሚዋዳደረው የሌለ የኦሮሙማ ቤተመንግሥት ልንሰራ ነው። በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው አለም አቀፍ አየር ጣቢያ ወደ ቢሾፍቱ አካባቢ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት እንሰራለን። በሐገሪቱ ብቸኛው ፈጣን የመኪና መንገድ የተነጠፈው ኦሮምያ ውስጥ ነው። ገና በየከተማው ይነጠፋል። በየትኛው ክልል እንደዚህ አትይነት መንገድ አይተሃል? የባቡር መንገዱም ቢሆን እንደዚሁ ነው። ታዲያ እኛ የሴም ነገዶችን የወደሙ ሆስፒታሎች፣ ፋክተሪዎች፣ ት/ቤቶች፣ ወዘተ አሁን ለኦሮምያ በሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ልናሰራ ነው? ቀልደኛ። ሁሉም የኛው ነው። መንገዱም፣ ፋክተሪውም፣ እርሻውም ከኦሮምያ ውጭ አይሆንም፣ ለማሳሳቻ ካልሆነ በቀር።

  • “እርካብና መንበርና” ላይ በፃፍንው መሰረት፣ ሁሉንም በጥቅምና በማስፈራራት ጠፍረን የዘንዋል። ካድሬዎቻችንን በገንዘብም በሃብትም አበልፅገን ከኋላችን ይዘናል። ከይኒቨርሲቲ አስተማሪዎች 10 እጥፍ ደመወዝ እየከፈልን። ከላይ እስከታች ያለውን መዋቅር፣ የእንጀራ አባታችን ወያኔ ባስተማረን መንገድ፣ አንድ ለአምሥት ይሁን አንድ ለሦሥት አዋቅረንዋል። በፕሮፓጋንዳወም ቢሆን፣ ከኦሮምያ ሚዲያዎችም አልፎ፣ ከሰላሳ በላይ የሶሽያል ሚዲያዎች ከፍተን አጀንዳችንን እያስፈፅምን እንገኛለን። የግራ ማጋብቱንና አጀንዳ መስጠቱን ሥራ በደንብ ስለምንሰራ፣ ሕዝቡን አደንዝዘንዋል። ሕዝቡ ምን ደረጃ ላይ እንኳን እንዳለን ለማወቅ አልቻለም። ለመስማት የሚፈልገውን እየደጋገምን ስለምንነግረው፣ ሀቁን ከቁማር ለይቶ ማወቅ እንኳን አልቻለም። በፈለገን ጊዜ ከጎናችን አሰልፈን ሙትልን ብንለው ለመሞት የሚችል መንጋ አድርገንዋል። አጠገቡ ልጁ፣ አጠገቡ እናቱ፣ አጠገቡ የሐይማኖት አባቱ በጥፊ ሲመቱ ተመልካች የሆነ፣ የራሱ መሪና ደራሽ ያጣ፣ ያልተደራጀና የተከፋፈለ፣ በመጭረሻም መከራና ግፍ የማይቆረቁረው ሆኖ የደነዘዘ ማህረሰብ እየፈጠርን ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጭራቅ አሕመድ ሆይ እርምህን አውጣ፣ የመዋጋት አለመዋጋት ምርጫ ያንተ ሳይሆን ያማራ ሕዝብ ሁኗል

እድሜ እናቱና ሚስቱ አማራ ለሆነችው፣ ሃይለኛ ሰባኪ፣ የኦሮሙማን አላማና ግብ አስፈፃሚው ጠ/ሚንስትራችን!! “አማቾቼ” እያለ፣ የኢትዮጵያን ሥም በየሰአቱ እየጠራ፣ በዚያው ልክ ደግሞ አማራውን ከኦሮምያ ስናፀዳ ዛፍ እየተከለ፣ ፋክተሪ እያስመረቀ አጀንዳ ያስቀይርልናል። ከአሁን በኋላ ማንም አይችለንም። እውሸት መሰላችሁ? አሁንም ይህንንም ፅሁፍ እየነበበ “ያለ አቢቹ የሚያሻገረን የለም” የሚል አይኑና ልቡ የታወረ ተከታይ አለን። ኦሮምያ ውስጥ፣ አሁንም ወደፊትም፣ ፊንፊኔን ጨምሮ፣ ያለፈቃዳችን የሚጋባም የሚወጣም አይኖርም። እንዲያው ምክንያት ብንሰጥ እውነት መሰለህ እንዴ? ኦሮምያ እኮ፣ ኢትዮጵያን በራሷ መልክ እየጠፈጠፈች ሐገር እየሆነች ነው። በቅርቡ ያለቪዛ ላናስገባህ እኮ እንችላለን። አሁን የምንለው ገባህ? አንት የደነዘዝክ ፍጡር? ምን ለታደርግ ትችላለህ? እዚያው እንደለመድከው አልቅስ እንጂ።

እንግዲህ ብልፅግናን ከበስተጀርባ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮና የስልጣን ኮርቻ ያሰከራቸው አፍላ መሪዎቹ በእንደዚህ አይነት ትቢት ተወጥረው ይገኛሉ።

እነዚህ በከፍተኛ የዘር ጥላቻ የታመሙ አደገኛ አክራሪዎች፣ የሕዝብ መሪ መሆናቸውን እረስተው፣ በአደባባይ ጥላቻንና ዘረኝነትን እያቀንቀኑ የሕዝብ እርስ በርስ እልቂት ለማስነሳት ከጫፍ ላይ ደርሰዋል። ዋናው የዘር ጥላቻ ድርሰትና ትርክታቸው መሰረትም አማራው ላይ ያቀነቀነ ነው። ቀደም ብሎ “ትምክህተኞች” ብለው ጀመሩና፣ “የነፍጠኛን” አከርካሪውን ሰብረንዋል ብለው በአደባባይ አበሰሩ። ያው ትምክህተኛውም፣ ነፍጠኛውም አማራው ነው። ኸረ ሕዝብ እያለቀ ነው። ድረሱልን እያሉ ነው። መንግሥት የሕዝብን ሰላም ማስጠበቅ አቅቶታል እንዴ ሲሉዋቸው፣ ካድሬዎቻቸውን በአደባባይ አስልፈው “ዳውን ዳውን ነፍጠኛ፣ ዳውን ዳውን አማራ” የሚል ልፈፋቸውን ያስተጋባሉ።

በቅርቡ ደግሞ “ፅንፈኛ” ወደሚባለው ሌላ የዘር ማጠልሸት ስድብ ላይ ተዛወረዋል። ወያኔ ጉልበታቸውን ሰብራ ስታብረከርካቸው፣ ህይወቱን ገብሮ ነፍስ የዘራላቸውን የአማራ ፋኖና ልዩ ሃይል፣ ለኦሮሙማ የኬኛ ፍልስፍና እንቅፋት ይሆናል ብለው፣ የፈጠሩት የጊዜው የፖለቲካ ማህደር ነው። ስለዚህ ይህ ፅንፈኛ የሚሉት ቃል በፊትም ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉት የፈረደበት ለአማራ የተሰጠ ስም ነው። እስላም ይሁን ክርስትያን፣ አማራ ሁሉ ጠላት ነው። ወደ ሃያ የሚደርሱ የእስልምና አማኞች በጎንደር እረብሻ ህይወታቸውን ሲያጡ፣ ሟቾቹ አማራ ክልል በመሆናቸው፣ ከመቅፅፈት አፀፋዊ እርምጃዎች ተወስደው ቤተክርስትያኖች ተቃጠሉ። ብዙ የሰላማዊ ሰዎችም ሕይወት ጠፋ። በምትኩ ግን በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ሙስሊሞች ወለጋ ውስጥ (ኦሮምያ ውስጥ) በዘግናኝና ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ሲጨፈጨፉና ሲቃጠሉ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ ሲፈናቀሉ፣ አንድ

የኦሮምያ ሙስሌም፣ ባለሜጫውን ጃዋር መሐመድን ጭምሮ፣ አንዲት ቃል የተነፈሰ አልነበረም። የተጨፈጨፏትና የተቃጠሉት የኦሮሞ ሙስሊሞች አይደሉምና። የወሎ እስላም አማራዎች ብቻ በመሆናቸው ደጋፊ አጥተዋል። ከዚህ የከረፋ፣ አይኑን በገሃድ ያፈጠጠ ዘረኝነት የለም። ይህ እንግዲህ ብልፅግናን ከበስተጀርባ ሆኖ የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮና የስልጣን ኮርቻ ያሰከራቸው አፍላ መሪዎቹ የሚያስፈፅመት፣ እስካሁንም ድረስ በገሃድ እየተካሄደ ያለ የዘር ማፅዳት ተልእኮ ነው። ፍርድ ትዘገያለች እንጂ መምጣቷ አይቀሬ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃገራዊ ጥሪ ከ 2007 ምርጫ በፊት!

ዛሬ ደግሞ፣ ኦርቶዶክሳዊው ላይ (ያው አማራ ነው ስለተባለ)፣ በፖሊሲ ደረጃ የተጠናና በመንግሥትም ድጋፍ የተቀነባበረ የገሀድ የጥላቻና አማራን የማጥፋት ዘመቻ “በፅንፈኛ” ሥም እየተገበረ ይገኛል።

ትላንትና ሽመልስ አብዲሳ፣ ኦርቶዶክስ ፅንፈኛ ነው ብሎ በገሃድ አውጇል። ያው እንደተለመደው የኦሮሙማ ብልፅግናን ከበስተጀርባ ሆኖ ለሚመራው፣ አክራሪውና ትርክተኛው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ፣ አማራ ማለት ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛና ፅንፈኛ ማለት ነው። ኦርቶዶክስ ማለትም አማራ ማለት ነው። ግዕዙም (የትግረ፣ ትግርኛ፣አማርኛ፣ ቋንቋ) አማራ ነው የሚሉት። ፊደሉም፣ ካሌንደሩም፣ ቅዳሴውም፣ ኦርቶዶክስም አማራም ነው ተብሎ የትርክት መፅሐፉ ታትሞ ከተሰራጨ ቆይቷል።

አፍላውና፣ የኦሮሞ ሕዝብ የታሪክ ጉድፍ የሆነው ሽመልስ አብዲሳ፣ በአደባባይ ኦርቶዶክስን “ቆሞ ቀር” የፅንፈኛ ቡድን ብሎ ተሳድቧል። ያው አማራውን ማለቱ ነው። “ንፍጥ ለባለቤቱ ቅቤ ነው” እንዲሉ፣ ይህ ከገማው አፉ የወጣው ቅሌትና አልባሌነት የተጠናወተው የቃላት ንፍጥ፣ ትርጉሙም የገባው አይመስልም። ቀጥሎም ይህ የኦርቶዶክስ ፅንፈኛ “የበታችነት ስሜት ያጠቃው ቡድን ነው” ይላል። “የአብዬን ወደ እምዬ” እንዲሉ ማለት ነው። አሁን እንግዲህ የኦሮሞ መሪ ነኝ ከሚል ሰው ይህ ይጠበቃል? የሩዋንዳን የዘር እልቂት የከፋ ደረጃ ላይ ያደረሱት “የዘረኝነት ትርክት” አእምሮዋቸውን ያዞራቸው፣ አይናቸውን ያወራቸውና ልቦናቸውን የደፈነባቸው፣ እንደነሽመልስ አብዲሳ ያሉት የሩዋንዳ መሰሪ መሪዎች በአደባባይ በሚተፏቸው መርዝ ነበር። ለነገሩ ሌላኛው የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስቴርም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ መላው ኢትዮጵያ እየሰማው “የአዲስ አበባ ሕዝብ ኦሮሞ ጠል ነው” ብለዋል። በአዲስ አበባ የሚኖረው ሱማሌውም፣ አፋሩም፣ ሲዳማውም፣ ጋምቤላውም፣ አማራውም፣ ትግሬውም፣ ወላይታውም፣ ጉራጌውም፣ ሃድያውም፣ ከምባታወም፣ ወዘተ ኦሮሞ ጠል ነው ብሏል የኢፌድሪ ጠ/ሚንስተር። ይህ እንግዲህ ጠ/ሚንስተራችን፣ በየመንደሩ የሚልዮኖች የ አ/አበባ ነዋሪዎችን በር እያንኳኳ ያገኘው መረጃ ነው? ወይንስ ከተለመደውን ዘርና ዘርን በማጋጨት በ“ከፋፍለህ ግዛው” መርሆ ስልጣን ላይ ለመደላደል የተተረበ መርዝ?

 

ሽመልስ አብዲሳ ሆይ! የአማራ ሕዝብ ጥፋት ኖሮበት ሳይሆን፣ እንደዚህ በጥላቻ ልብህ ያሳበጠው ውስጥህን እየበላ ያለው የራስህው “የበታችነት ስሜት ነው”። ለዚህም ነው፣ እንደ አንተ ያለው ባለጌ ከመወለዱ በፊት፣ ጨዋው የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ ተከባብሮ፣ ተዋልዶ፣ አብሮ ለሐገሩ ሞቶ ለዘመናት የኖረው። የታሪክ አጋጣሚ እንጭጭና ያልበሰልለ አስተሳሰብህን ለማጋለጥ መድረክ የሰጠህ፣ እወክላሉኝ የምትለውን ታላቅ የኦሮም ሕዝብ የምታሳፍር እባጭ ነህ። እጅጉን የሚያሳዝነው ነገር፣ እንደ አብይ አህመድና እንደ አንተ አይነቱ የውጭ ሃይሎች አጀንዳ አስፈፃሚ፣ ዘርና ሐይማኖትን እየከፋፈል በሰላም አብሮ የቆየውን ሕዝብ ወደማያባራ እልቂት ለመውሰድ እየሰራ በመሆኑ ነው። ከ45% ብላይ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኦርቶዶክስ ተከታይ ነው። ይህ 60 ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ፣ የመንግሥትን ደምወዝ ከፋይ የሆነ ሕዝብ፣ በራሱ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱት የራዲዮና የቴሌቪዝን ጣቢያዎች እንኳን ይህን ያጋጠመውን ታላቅ ችግር እንዳይዘግቡ ተለጉመው ነበር።

 

የወያኔና ብአዴን ወቅታዊ ብያኔ።

የኦህዴድ ብልፅግና ሸፍጥ ሰለባ መሆን? ወይንስ የሰሜኑን ሕዝብ ህልውና መታደግ?

የፖለቲካ ጨዋታውን እስትራቲጅያዊ የሚይደርገው፣ በምዕራቡ አለም እርብርብ በይፋ ተደግፎ፣ ለሁለት ዓመታት ተቆልፎበት ከነበረው ጂኒ ውስጥ በድንገት የተለቀቀው ወያኔ፣ በምን መልኩ የፖለቲካወን መድረክ እንደሚያቀልመው መተንበዩ ነው።

“ለጨለማ ጊዜ መብራት፣ ለመከራ ጊዜ ብልሃት” እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ የሰሜኑን ሕዝብ ህልውና ለመታደግ ሲባል የትግራይና የአማራ ሕዝብ ከፊት ለፊታቸው የተደቀነውን እልቂት ለመግታትስ ምን መደረግ አለበት? ብአዴንም፣ ሊወጋ የመጣ ባላንጣ፣ ጌታዬ ቢሉት ስለማይመለስ፣ ቁርጡን አውቆ ከሕዝቡ ጎን በመቆሞ መታገል ይኖርበታል። ሌላ ምርጫ የለም።

 

ይቀጥላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share