በላይነህ አባተ ([email protected])
እስከ ዛሬ የሆነውን ሁሉ አስተውሎ አቶ ሊዮ ኦከሬ “…Machinations For ‘Amharafrei’ Ethiopia” በሚል ርእስ ያስተላለፉትን ጥብቅ መልእክት ይህንን ተጭኖ* https://tinyurl.com/3bhuy5ua አንብቦና ተገንዝቦ ዛሬም አማራን የማያነቃና የማያደራጅ የአማራ ወይም ኢትዮጵያዊ ምሁር ተኝቶ ወይም እያዘናጋ አማራ ባዶ (AmaraFrie) ኢትዮጵያን እየጠበቀ መሆኑን ይወቅ፡፡
አቶ ሊዮ ኦከሬ ከአንድ ተኩል ሚሊዮን በላይ ጨፍጭፈውና ከአስራ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አፈናቅለው ኬንያ የተስማሙት ክፉዎች የተሰማሙት አማራ ባዶ (“(Amara Frie) አገር ለመመስረት መሆኑን በጥኑ አሳውቀው ታሪካዊ ሐላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ በአማራ መቃብር ላይ መንደር ወይም ሪፐብሊክ እንመሰርታለን እያሉ ሲደራጁ የኖሩትን “ነጣ አውጪ ነን ባዮችን” ኬንያ ውስጥ ያስማማቸው አቶ ሊዮ ታሉት ውጪ ይሆናል ብሎ የሚያስብ ዘልዛላ ካለ አማራ ሳይደራጅና ራሱን ሳይከላከል ይጥፋ ብሎ የጥፋቱ ተባብሪ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
የአማራ ምሁራን ሆይ፡- እንደምታውቁት የአማራ ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የእምነት አባቶችን ከእነሱ ቀጥሎም ምሁራንን ያምናል፡፡ በተለይ ከሰላሳ አመታት በፊት የእምነት አባት የተናገረው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል፣ ምሁር የተናገረው ሁሉም እውነትና እውቀት ይመስለው ነበር፡፡ ይኸንን እየተሸረሸረ የመጣውን የእምነት ትስስር የእምነት አባቶችም ሆነ ምሁራኑ እንደገና መገንባት ይኖርባቸዋል፡፡ የእምነት አባቶችም ሆነ ምሁራን በዘሩ ምክንያት በመላ አገሪቱ የሚታረደው የአማራ ነፈሰ-ጡር፣ ህፃን፣ ባልቴት፣ ሽማግሌና ወጣት እንቅልፍ ሊነሳቸውና ሕዝቡ ራሱን የሚከላከልበትን መንገድ መትለም ይጠበቅባቸዋል፡፡
አማራን በጠላትነት የፈረጁ ሌሎች “ምሁራን ነን ባዮች የምድጃ ወሬና ተረት ተረት ወሬ እየተረኩ በመደራጀት አማራን ማጥፋት ተጀመሩ ግማሽ ክፍለ-ዘመን አልፏቸዋል፡፡ አማራ አንገቱ ተቆርጦ መሬት ሲጎተት፣ ቤተክርስቲያንና መስጊድ ሲፀልይ በእሳት ሲቃጠል፣ በአገሩ ውስጥ እየተፈናቀለ እንደ ዘፀአት ሰዎች ሲሰደድና ተሰዶም ተመንገድ እንኳ እንዳይተኛ ሲከለከል በዓይኗ በብረቷ ያዬ የእምነትም ሆነ የዓለማዊ ትምህርት የአማራ ምሁር የግማሽ ዘመኑን ግፍ መርምሮና የሁኑን አጢኖ የወደፊቱን በመተንበይ ሕዝቡን እንደ አሲሪያን ሕዝብ ከመጥፋት ለማዳን እንደለገመ ሕዝቡም አግዚአብሔርም ያውቃል፡፡
ቲሞቲ ስናይደር የተባለ የየል ዩንቨርሲቲ ሊቅ እንደሚያስተምረው ዛሬ እሚታየው ምልክት የነገውን እውነታ ያሳያል**፡፡ ፕሮፌሰር ስናይደር እንደፃፈው ናዚዎች አይሁዳውያንን ለመጨፍጨፍ ሲወጥኑ እንደ ለገጣፎና ሱሉልታ ገዥዎች በአይሁዶች ግድግዳዎች “አይሁድ በጀርመን ቦታ የለውም” የሚል ምልክት ለቀለቁ፡፡ ይኸንን የተለቀለቀ ምልክት ያነበቡ አይሁድ ምሁራን ግን እንደ ዛሬው አማራ ምሁራን “የጥቂት ጋጠ ወጦች ተግባር!” እያሉ አለፉ፡፡ እንደዚህ እይነቱ ጋጠወጥ ጋጠወጥን ከሚደግፍ ማህበረሰብ ውጪ እንደማይኖር ረሱ፡፡ በዚህ ችልታቸውም አይሁዳንን ሳያስጠነቅቁ በመደዳ አስጨፈጨፉ፡፡
ይህም ቢሆን አይሁዳውያን ተዚያ ስህተታቸው ትምህርት ቀስመው፣ ያለፈውን በሚገባ መርምረው፣ የወደፊቱን እየተነበዩ ራሳቸውን ዳግም ከመጥፋት ለማዳን እየተጉ ይገኛሉ፡፡ አይሁዳውያን በብዙ አገሮች የአይሁዳውያንን ጭፍጨፋ የሚያንፀባርቅ ብዙ ሐውልት ከተጨፈጨፉት ሰዎች ፎቶና ሥም ጋር ገንብተዋል፡፡ ተቆጥሮ የማያልቅ እልቂቱን የሚያንፀባርቅ ተንቀሳቃሽና ተቀማጭ ቅርስ አከማችተዋል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ጥበብ ሕዝባቸው ዳግመኛ እንደዚያ አይነት እልቂት ውስጥ እንዳይገባ ይረዳዋል፡፡
በናዚ ዘመን ያለቀው የአይሁዳውያን ቁጥረ ስድስት ሚሊዮን ነበር፡፡ ሆን ተብሎ በማምከን ሳይወለድ የቀረው ተትቶ በአለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ በዘሩ ምክንያት የጠፋው የአማራ ሕዝብ በትክክል ቢቆጠር ቢያንስ በናዚ ዘመን የጠፋውን የአይሁድ ቁጥር እጥፍ ይሆናል፡፡ አማራ እንዲህ እየጠፋ የእምነትና የዓለማዊ ትምህርት አማራ ምሁራን ግን አማራ የዘር ፍጅት እየተፈጠመበት ነው ለማለትም ባቄላ እንደጎረሰ ዶሮ ጉረሯቸውን ያንቃቸዋል፡፡ በግልጥ አነጋገር አብዛኛው የአማራ ምሁራን ለእውነታና ለሚያልቀው የአማራ ነፍስ ግድ የሌላቸው ባእዶች ሆነዋል፡፡
የአማራ ምሁራን የበሬ እንትን ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደኖረችው ቀበሮ በአጉል ተስፋ መንዘላዘሉን ትተው እውነታውን መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ እንደ አለመታደል አማራ የገጠመው ችግር በዚህ ወይም በሚቀጥለው ትውልድ ብቻ የሚያበቃ አለመሆኑን የአማራ ምሁራን ማጤን ይኖርባቸዋል፡፡ በናዚዎች የተፈጠመው ጭፍጨፋ ለአይሁዳውያን ትምህርት ሆኖ ጠንካራ እንዳደረጋቸው ሁሉ ለሰላሳ ዓመታት በአማራ የተፈጠመው የዘር ፍጁት በኣንድና በሁለት ትውልድ ብቻ የሚያበቃ አለመሆኑን ተገዝቦና ለአማራ ትልቅ ትምህርት መሆኑን አጢኖ አማራ የበለጠ ጠንካራ በመሆን ከራሱ አልፎ እንደ በፊቱ ለሌሎች የሚተርፍበትን መንገድ መቀየስ ይኖርበታል፡፡
የአማራ ፍጅት የአካል፣ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የቅርስ፣ የእውቀት፣ የታሪክና ሌሎች እሴቶች ስለሆነ ሁሉም የሚሳተፍበት የተወሳሰበ ቋሚና ዘላለማዊ የትግል ዘርፍ ይጠይቃል፡፡ ለመንደርደሪያ ያህልም፡-
፩. የእምነት ምሁራን “እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ፈጠረው ከሚለው ትምህት በተጨማሪ እግዚአብሔር ስውን በአምሳሉ ቢፈጥረውም ከተፈጠ በኃላ ሰይጣን ሊነጥቀውና ዘር አጥፊ ሊያደርገው ስለሚችል ከዘር አጥፊ ራስን መከላከል የሙሴ የኢያሱና የሌሎችም የእግዚአብሔር ሰዎች የቅድስና ተግባር መሆኑን ማስተማር
፪. መስቀል የተሸከሙ የሃይማኖት የአማራ ምሁራን መስቀል እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ምሁራን የተሰውበት የመስዋአትነት ምልክት መሆኑን ማመንና ለመስቀሉ መገዛት
፫. ዲግሪ አለን የሚሉ ምሁራን ዲግሪቸውን የምግብ መጠቅጠቂያን መንደላቀቂያ ተማድረግ አሳማዊ ባህሪ ተላቀው የሕዝባቸውን እልቂት ለማየት አይናቸውንና ጆሮዋቸውን በመክፈት የሰላሳ አመቱን እልቂት በጥናትና በምርምር ለሕዝባቸውና ለዓለም ማሳወቅ
፬. ምሁራን ባዳበሩት እውቀት
ህ. አማራ አሁን ብቻ ሳይሆን ወደፊትም የሚደርስበትን ችግር ከወዲሁ በተለያዬ መንገድ በማስተማር ማንቃት
ለ. አማራ ራሱን ከአካላዊና መንፈሳዊ ዘር ፍጅት ለመከላከል የሚያስችል ጥኑ ድርጅታዊ መዋቅር መዘርጋት
ሐ. በአለፉት ሰላሳ ዓመታትም ሆነ አሁን በዘራቸው የተጨፈጨፉትን፣ የተፈናቀሉትን፣ የተሰደዱትን፣ የተጠለፉትን፣ ሆነ ተብሎ ዩንቨርስቲ እንዳይገቡ የተከለለሉትን በምስል፣ በሥም፣ በእድሜ፣ በፆታና በሌሎችም መስፈርቶች ያካተተ ማህደር ማጠናቀር
መ. በውጪም ሆነ በአገር ቤት ይኸንን ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ ማስታውሻዎች መገንባት
ሠ. የአማራን ዘር ፍጅት ወይም የህልውና ተጋድሎ የሚዘክር በበላሙያ ጋዜጠኞች የሚመራ የሕዝብ መገናኛ (ራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ዌብ ሳይትና ሌሎችም) ማቋቛም፡፡ የትያትር ሰዎችም የምዕራባውያንን ግሳንግስ እየቀዱ ወጣቱን ማዘናጋቱን ትተው የዘር ማጥፋቱን የሚመመለከት ታሪካዊ ሥራ ሰርተው እንዲያልፉ መወትወት፡፡
ረ. በአማራ ዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉትን አረመኔዎች አጣሪና መዝጋቢ ቡድን መገንባት
ሸ. በዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉትን ሕግ ፊት የሚያቀርብ ቡድን ማቋቋም
ቀ. የአማራን የዘር ጭፍጨፋና የህልውና ተጋድሎ ለዓለም ሕዝብ የሚያሳውቅ የዲፕሎማሲ ተቋም ማቋቋም
፭. ሕዝቡ ምሁራን በመከተል
ሀ. እንኳን ሙሉ አካል ያለው የሌለውም እያንዳንዱ አማራ ዘሩ፣ ሃይማኖቱ፣ ባህሉ፣ ታሪኩና ቅርሱ እንዳይጠፋ የሚያበረክተው አስተዋፅዎ እንዳለ ማመን
ለ. ምሁራን የሚያቋቁማቸውን ቋሚ ተቋማት በጉልበት፣ በሐሳብና በገንዘብ መርዳት
ሐ. ተጎልቶ አንድም ሰው ጠፋ እኮ እያሉ ማጣወር ራስን አንደ ሰው አለምቁጠርና ራስን ሰው መሆን የማይችል የአንግዲህ ልጅ አድርጎ መቁጠር መሆኑን ማጤን፡፡ አባቶች ይሉት እንደነበረው ግፍ ሲበዛና ልብ ስትቆርጥ ማንም ጀግና ሊሆን አንደሚችልና ሜዳውም ሆነ ከተማው ወደ ጫካነት ሊቀየር አንደሚችል ማመን
መ. ጀግና ሲፈጠር በመቅቡጥ፣ በአድርባይነት፣ በባንዳነትና በፍርሃት አየተሽመደመዱ አሳልፎ አለመስጠት
ሠ. ጊዜው የቴክኖሎጅ ስለሆነ ሁሉም አማራ በምስል፣ በድምጥና በጽሑፍ የተደገፈ እውነተኛ መረጃ በመሰብሰብ ሥራ መሰማራት
ረ. ተመዋሸት፣ ተስንፍና፣ ተስርቆት፣ ተክህደት፣ ግፍ ተመስራትና ሌሎችም እርኩስ ሥራዎች ራስን መጠበቅ
ሰ. ተጅብ ተርፎ የሰነበተ ጥንብ የአህያ ሬሳ የባሰ የሚከረፋውን መንደርተኝነት የሚባል ደዌ አንድ ሺህ ሜትር ጉድጓድ ቆፍሮ እስከ ዓለም ፍጣሜ አንዳይነሳ አርጎ መቅበር
ሸ. ዳግመኛ የዘር ጭፍጨፋ ኢላማ ሆኖ ላለመገኘት በዓለት ላይ የተመሰረት ኃይል መገንባት
የአማራ ምሁራንና የአማራ ሕዝብ ሆይ! እንደምታውቁት የአማራ ዘር ፍጅት ቁማር ከሰላሳ ዓመታት ወዲህ በግልጥ ይፈጠም አንጅ የተሸረበው ከአውሮጳውያን የቅኝ ግዛት ሽንፈት በኋላ ነው፡፡ የአማራ ዘር ፍጅት በአንድና በሁለት ትውልድ ብቻ ይቆማል ብሎ ማሰብ በጠራራ ፀሐይ ቅቤ በራሱ ተሸክሞ ተሄደው ማሞ ቂሎም ማነስ ነው፡፡
የአማራ የአካል፤ የሃይማኖት፤ የባህል፤ የቅርስ፤ የትምህርትና የታሪክ ዘር ፍጅት ከውጪም ከውስጥም ሥር ያለው ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ዘላለማዊ ሰይጣናዊ አቅድ ነው፡፡ የአማራ ምሁራንና ሕዝብም እንደ አያቶቻቸው አራት አይና ሆነውና ይኸንን ተገንዝበው የጥፋት ሴራውን የሚቋቋም ጥኑ ዘላለማዊ ተቋም መገንባት አለባቸው፡፡ ዘር መጥፋትን መከላከል ሰውነት ነው፤ ምሁርነት ነው፤ ቅድስናም ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
** on tyranny: Twenty Lessons from The Twentieth Century chapter 4
ተጨማሪ ጽሑፎች፡
1. A Message to Amara Elites: Never Allow Ethnic Cleansing of Amara Again! https://www.zehabesha.com/a-message-to-amara-elites-never-allow-ethnic-cleansing-of-amara-again/?fbclid=IwAR39-VVEyK9B3K4qyv40xVyKLFAQ4yQd3NZ5gdVLLEIf-OL3BW8pyuuTAWI
- Please Stop Predisposing Amaras to Continue Perishing in Cities and Rural Areas!
- The Ethiopian Elites Have Failed to Follow The Principles of Our Forefathers! https://www.zehabesha.com/the-ethiopian-elites-have-failed-to-follow-the-principles-of-our-forefathers/?fbclid=IwAR2vDSOkwZ2-A8HUa-iajOYFrvb49Z2rdD62jLkfLA_T7p2V6vWcco9gEIk
4. በስልጣን ሰክሮ ያበደን ካድሬ ውይይትና ምክር ሊፈውሰው ይችላልን? https://welkait.com/?p=19399&fbclid=IwAR1PGGrvShRVdWUA5_-QmXlhonXcdrFDR-J6pIJv3LWBYPyRq9vwJLcWYYY
5. አማራ ሆይ! ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቀው?
https://welkait.com/?p=17552&fbclid=IwAR1eqGmFZYQ_aO5tKOaJXsFZzW–Hi6PULfLQMJuSvh067CnTy-MMzFduuo
6. ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው!
7. አማራ ዳግም አትታለል እንደ ላሜ ቦራ!
https://welkait.com/?p=16336&fbclid=IwAR3TucrZU-L98xi7BHvmfy72coFWall47VWRKXYQs3OAlGT3_yttzFuqEns
8. ወጣት ሆይ! እደግ! ተመንደግ! – በላይነህ አባተ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94987?fbclid=IwAR16KT0YJujEAGRuw2Qum3Thw7GD6WvIp8TfLCXeETm6ptbZ2BRBzqJiL2g
9. ወጣት ሆይ! ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%89%B5-%E1%88%86%E1%8B%AD-%E1%88%88%E1%88%85%E1%88%8D%E1%8B%8D%E1%8A%93%E1%88%85%E1%88%9D-%E1%88%86%E1%8A%90-%E1%88%88%E1%8A%AD%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%85-%E1%8B%88%E1%8B%B0/?fbclid=IwAR0tsEDbDAQaE5BkeeJpzHCv3j30RxoxKtsV4ybfgBg8PTatn0eJmmIQSz0
10. አማራ ሆይ! ሰው እንሰሳም ነው! https://welkait.com/?p=19311&fbclid=IwAR15eJVKUJ_b6SBFd-Sz8_mJ4wDOCGfJ4a6gVy8HQJdTigeXypyWG7KTwSc
11. የአማራ ጨቋኙ አቀንቃኞች እምቢኝ አረፋውን ባህሪ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8C%A8%E1%89%8B%E1%8A%99-%E1%8A%A0%E1%89%80%E1%8A%95%E1%89%83%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%88%9D%E1%89%A2%E1%8A%9D-%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8D%8B%E1%8B%8D/?fbclid=IwAR06hGmzfyvYp0pamjEv2M4Oo3U4k5Lh1ucqE_NFHVb1MGmMet2mr-YUpeU
12. አማራ ከጅብ መንጋጋ ተላቆ ከእስስት አፍ ገብቷል! (በላይነህ አባተ) https://www.satenaw.com/amharic/archives/64345?fbclid=IwAR186W_UWnfZoS9_NhCKQ6hRHdx-c_W7HT3r0oLNVu1fzZhmad9LwyAsndY
- ለአባትዮውለገሰቦንድ ለልጁ ፓስተር አቢይ ፈንድ! https://welkait.com/?p=19088&fbclid=IwAR1mqyYRoNVg3ZCVPhEbSzxYZU3FGf1QH5siUhRwKdaKla-0Q6Ly4lKx7dY
- ሕዝብእንዲሰማህሰፊ አፍ ይኑርህ! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/94149?fbclid=IwAR0531t6KCkF-TywMIFjVmqx-jZyabuh_Ourw5vqSlrFVACc8DH6ROXJgA8
15. በአማራ ሰማእታት የተፈጠመው ግፍ በቅዱሳን ሐዋርያት ከተፈጠመው ግፍ ይከፋል! (በላይነህ አባተ)
16. ይሁዳ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር ሸጠው! (በላይነህ አባተ )
17. Urgent Message to Amara Elites: Speak Up Against The Ethnic Cleansing of Amara!
የካቲት ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.