February 21, 2023
5 mins read

የመጽሐፍ ምረቃ ጥሪ: የካቲት 24 ቀን 2015 በጊዮን ሆቴል – ያሬድ ኃይለማርያም

 

u94895989 1

የተከበራችሁ ወዳጆቼ እና የመገናኛ ብዙሃን አባላት፤ በሰብአዊ መብቶች ትግል ውስጥ ከሁለት አሥርት አመታት በላይ ባሳለፍኩት የትግል ጊዜ ውስጥ የገጠሙኝን ውጣ ውረዶች እና ሌሎች ከዚህ በፊት ለማንም ያላካፈልኳቸውን ገጠመኞቼንና በርካታ ትውስታዎቼን የከተብኩበትን ባለ 392 ገጽ መጽሐፍ የካቲት 24 ቀን 2015 ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 1:30 ድረስ በጊዮን ሆቴል ግሮቭ ጋርደን መናፈሻ አስመርቃለሁ። በዕለቱ መጽሐፉን ቀድመው አንብበው የግምገማ ሃሳባቸውን የሚያቀርቡ ሦስት እንግዶችም ተጋብዘዋል። ዶ/ር ዳዲሞስ ኃይሌ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ መለስካቸው አመሃ እና የስጽነ-ሥሑፍ መምህርና አንጋፋ ገጣሚው ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በመድረኩ ላይ ይሰየማሉ። ለእኔ ታላቅ በሆነው በዚህ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ስፍራ ተገኝተው የመጽሐፌ ምረቃ ታዳሚ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ባልሰፈነበት እና የሕግ የበላይነትም ባልተረጋገጠበት፤ እንዲሁም ነጻና ገለልተኛ ተቋማት በሌሉበት አገር ለሰብአዊ መብቶች መታገል የእራስን እና የቤተሰብን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል። በተለይም አምባገነናዊ ሥርዓት በሰፈነበት ሥፍራ ሁሉ ለሰው ልጆች መብት የሚታገሉ ሰዎች ብዙ ፈታዎችና ውጣ ውረዶች ይገጥሟቸዋል። እኔም እንደማንኛውም የመብት ተሟጋች ብዙ ፈተናዎችን እና ክፉ አጋጣሚዎችን ሁሉ አልፌያለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የመብት ተሟጋቾችም እኔን ከገጠሙኝም እጅግ የከፉ ችግሮችን አስተናግደዋል። በዚህ መጽሐፌ ማሳየት የፈለኩት የመብት ተሟጋቾች በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለዘመናት ሲፈጸም በቆየበት አና አሁንም አስከፊ የመብት ጥሰት በሚፈጸምበት አገር የሚገጥሟቸው ችግሮች ምን እንደሚመስሉ፣ ከምን የመነጩ እንደሆኑ ለመጠቆም እና እኔም በግሌ የገጠሙኝን ችግሮች በምሳሌ እያጣቀስኩ ለማሳየት ነው።

 

ይህ መፅሐፍ፤ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ መጠን እግረ መንገዴን ያሬድ ኃይለማርያም ማነው? የት ተወልዶ፣ እንዴት እና የት አደገ? እንዴትስ ወደ ሰብዓዊ መብቶች ትግል ገባ? ለምን? ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትስ በሰብዓዊ መብቶች ትግል ውስጥ እንዴት ሊቆይ ቻለ? ምን ምን ተግባራትን አከናወነ? ምን ውጤትስ አመጣ? ምንስ ማድረግ ሲገባው ሳያደርግ ቀረ? ምን ስሕተቶች ሠራ? ወጣቶች፤ በተለይም በሰብዓዊ መብት ትግል ውስጥ ለመቀላቀል እና የመብት ተሟጋች ለመሆን የሚፈልጉ ሰዎች ከእኔ የሕይወትና የትግል ተመክሮ ምን ይማራሉ? የሚሉትን እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን እያሰላሰልኩ የጻፍኩት መፅሐፍ ነው። እነዚህንና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችንም ለመመለስ የተለመ የሕይወት ተሞክሮ ማካፈያ ጽሑፍ ቢባል ይቀላል። በዚህ መፅሐፍ ውስጥ በተቻለ መጠን በሰብዓዊ መብቶች የትግል ጉዜዬ ውስጥ ትልቅ አሻራ ጥለው ያለፉ ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችን እና ወሳኝ የምላቸውን ኩነቶች ለማንሳትና ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ከአገር ውስጥ እስከ አለም አቀፍ መድረኮች የነበሩኝን ተሞክሮዎችና ገጠመኞች አስተማሪ በሆነ መልኩ እንደ የአግባቡ አነሳለሁ።

 

የካቲት 24 ቀን 2015 በጊዮን ሆቴል ግሮቭ ጋርደን እንገናኝ!

 

አክባሪዎት ያሬድ ኃይለማርያም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop