“በትላንት የታሪክ ምርኮኞችና በነገው ተስፋችን ቁማርተኞች ሕልውናዋን የማታጣ ሃገር መገንባት ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው”- የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መግለጫ

በምድራችን ካላፉት የሥርዓተ መንግሥታት ታሪክ ውስጥ በራሳቸው ሕዝብ መካከል ተቃርኖን እየሸመኑ አንዱን የማኅበረሰብ ክፍል ከሳሽ፣ ሌላኛውን ደግሞ ተከሳሽ የሚያደርግ ጥልፍ በመጎንጎን የሀገረ መንግሥትነት ሕልውናቸውን ያጸኑም ሆነ ዘላቂ ሰላምና እድገታቸውን ያረጋገጡ መንግሥታት ተብለው ለአብነት ያህል እንኳ ስማቸው የሚጠቀስ ነገሥታትም ሆኑ መንግሥታት የሉም።

እንዳለመታደል ሆኖ ከታሪክም ሆነ ከአሁናዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ የአንድ ሀገር ሕዝብን በአንድነት እና እኩልነት ላይ በተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ሕዝብና ሀገራቸውን ለመለወጥ ከመታተር ይልቅ፤ በየሚዲያው የጥላቻ ተረክን እየነዙ ፖለቲከኞች በፖለቲካ ገበያው ውስጥ ናኝተው ይታያሉ፡፡

መታወቅ ያለበት ሃቅ የትላንት መጥፎ ታሪክ ጠበቃዎች አይደለንም። ልንሆንም አንችልም። ሁኖም ግን ታሪክ ትምህርት ቤት መሆኑን እናምናለን። የትላንት ታሪካችንም ቢሆን መጥፎ ብቻ አይደለም። መጥፎ ታሪክ ካለም ለመጥፎ ታሪኩ ጠበቃ የመሆን ፍላጎት የለንም። ይልቁንም የትናንትናውን መጥፎ ታሪክ ላለመድገም እንጥራለን አብዛኛውን በጎውን የጋራ ታሪካችንን ደግሞ አሻሽለን ትውልድን ለመጥቀም እንተጋለን። ነገር ግን የትላንት የታሪክ ምርኮኞች ሆነን ህዝባችንን ለፖለቲካ በሽታ የማጋለጥ ፍላጎቱም ትልሙም የለንም። አላማችንም አይደለም።

ይሁን እንጅ አሁን አሁን የትላንት ታሪክ ምርኮኛ ፖለቲከኞች ታሪክን እያዛቡ በማመንዠክ ዛሬያችንን ስለነገው ተስፋችን ከመሥራት ይልቅ ስለትላንቱ ተረከ-ታሪክ እሰጥ-አገባ መቆም የትውልዳችን ወትሯዊ ውሎ ሲሆን ይስተዋላል፡፡

የትላንት ታሪክ ምርኮኛዎች ትናንትን ከዛሬ በዉል ለይቶ ወደ ነገ መሻገር ሲሳናቸዉ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ቁሞ ቀር የፖለቲካ አስተሳሰብን ማመንዠክ ልዩ ክህሎትና መገለጫቸው እየሆነ መጥቷል፡፡

ጀንበር መሽቶ በጠባ ቁጥር ልብስና ወንበር እየቀየሩ በተቀናጀ እና በተናበበ መንገድ የሚረጩት መርዛማነቱ ከልብስና ወንበራቸው ጋር አብሮ ያልተቀየረ የከፋፋይነት እርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ የሀገርና የሕዝብን ሰላም፣ አብሮነት እና ልማት ምን ያህል እያቀነጨረው እንደሆነ ሊገነዘቡት አልቻሉም ወይም አልፈለጉም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አባይ ወልዱና ደብረጽዮን ሽጉጥ ተማዘው ነበር - የአባይ ቡድን በሁለት ተከፈለ (አብርሃም ደስታ - ከመቀሌ)

ይህን መሰሉ ፖለቲካዊ ግልሙትና በሕዝብ ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ ስሁት ትርክት እየነዙ ደም አፋሳሽ በሆነ መንገድ በሥልጣን ለመኖር ወይም ወደ ስልጣን ለመምጣት ቅጽበታዊ እድል ለማግኘት ካልጠቀመ በስተቀር ለሀገር አንድነትና ሕልውና ፋይዳ ቢስ ስለመሆኑ ከሥርዓተ መንግሥታትና ከነገሥታቱ ታሪክም ሆነ ከዘመናዊው የፖለቲካ ሳይንስ አስተምህሮት መማር ይቻላል፡፡

በዚህ ወቅት በሰፊ ሀገርና በታላቅ ሕዝብ ውስጥ እየኖሩ የጠበበ ግላዊና ቡድናዊ የጥቅም ፍላጎትን የሕዝብ አስመስሎ በማቅረብ፣ በጥላቻ ላይ ተመስርቶ ፤ ስሁት ትርክትን ተደግፎ ግጭት እየዘሩ፤ መከራን ኮትኩተው ሞት እያሳጨዱ ቡድናዊ ጥቅሜን አስቀጥላለሁ ብሎ ማመን ከትናንቱ ታሪክና ከነገው ተስፋ ጋር ተጻራሪ መሆንን ከማስረገጡ ባሻገር ዛሬን በሕይወት የመኖር ጸጋን ለመንፈግ የፖለቲካ ቁማር ቋሚ ሰልፈኝነትን ያስረዳል፡፡

ይህን መሰሉ አሰላለፍ የአፍታ ተዝናኖት ይሰጥ ካልሆነ በቀር የጀንበር ማብቂያ ያህል እድሜ ያለው ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ሕልውነትን አይሰጥም፡፡ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ያደረ ጥያቄ እና ያልበረደ ፍላጎት ያለውን ሕዝብ እየመሩና ለመምራት እየሻቱ በተቃራኒው የሴራ ፖለቲካ እየሸመኑ፤ ዘረኝነትን እያቦኩ መኖር የሚቻልበት እድልም ጊዜም የለንም፡፡

ለዘመናት ተዋዶና ተዋህዶ በፍቅርና በአንድነት፣ በብሔርና በጎሳ ሳይከፋፈል፣ በቋንቋና ባህል ልዩነት ሳይለያይ፣ ብዙኅነቱን ተቀብሎ ለዘመናት ክብሩንና ታሪኩን ጠብቆ የኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የትላንት ታሪክ ምርኮኞች የሚከውኗቸውን ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ እና በዘር የሚከፋፍሉና ሕዝባችን ውስጥ ቅራኔና ጥላቻ የሚፈጥሩ ንግግሮችንና ተግባራትን እንደ አንድ ሕዝብ አምርሮ ሊቃወም፣ ሊታገልና ከውስጡ ሊያገላቸው ይገባል፡፡

ይህ ወቅት መላው ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ልብ ተባብሮ የታሪክ ምርኮኞችን መታገል የሚያስፈልግበት ወሳኝ ምዕራፍ እየሆነ መጥቷል። ሞቅ ቀዝቀዝ በሚል የትግል ሂደት ጠማማ የታሪክ ምርኮኞችና ቅን ልቦና የተሳናቸው የፖለቲካ ቆማሪዎች በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ላይ የጋረጡትን አደጋ ማስቀረት የሚቻለው ለእውነትና መርህ በመገዛት መታገል ሲቻል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት 11 ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ

ስለሆነም የእስካሁኑ የትግል ስልትና አካሄድ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ሁሉን አቀፍና አሳታፊ፣ ተጠያቂነት ያለው ህዝባችንን ያማከለ፣ በመልካም ዓላማ ሀገር ግንባታን ማዕከል ያደረገ፣ ወጥነት ያለው፣ የሀሳብና ዴሞክራሲያዊ ፍትሐዊ ትግል ማድረግ የሁላችንም የሁል ግዜ መደበኛ ሥራ ሊሆን ግድ ይላል።

በትላንት የታሪክ ምርኮኞችና በነገው ተስፋችን ቁማርተኞች ሕልውናዋን የማታጣ፤ በጠንካራ የሕዝብ አንድነትና እኩልነት ላይ የፀና ሀገረ መንግሥት ለማቆም መረባረብ ከሁላችንም የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው፡፡

የምናልመው ለውጥና ስኬትም ሆነ የሕዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በምኞትና በፍላጎት ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ አለመሆናቸው ታውቆ ሁሉም ዜጋ ችግሮቻችንን ውጫዊ በማድረግ የሆነን አካል ብቻ እንዲፈታ ከመጠበቅ ወጥቶ፤ የበኩሉን ድርሻ በማድረግና በመተጋገዝ ተደማምጦ በአንድነት ለለውጥና ስኬት በመታገል ተስፋና ለጋ ውጤቶቻችንን በማዝለቅ እንደ ሕዝብ ለገጠመን ፈተና ደግሞ የጋራ መፍትሔ እያበጁ መሄድ ይገባል። አማራጩም ይሄው ነው!!

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

All reactions:

514

\

4 Comments

 1. “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

  Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the master key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

  Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context did not work.

  As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and the size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be – if not already – the tail of the whole world by all standards of measure.

  So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

  The Belgian model of confederation which appears to help advance Amhara interests is something to explore.

  In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.change of government at federal level is not the answer for these problems.

  In private, Tigreans have floated the idea of confederation – reserving separation for later, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears justified. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

  Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tgreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

  It is outdated for Amharas to hang on “emama Ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

  Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amhara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take amharas anywhere.

  Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate us, Oromos too from our bloody distructive path poised to takie everybody else down with us. »

 2. Last time, the war started with a series of Meglachas and counter-Meglachas. Are you guys (EPRDF/PP/TPLF/OLF) gearing up to engulf the country in war again? Since Abiy Ahmed claims to have a degree in conflict resolution, all he wants to do is create conflicts and act like he tries to resolve them? I am sure he drafted this letter himself.

  Minallebet selam bitsetun?

 3. ደንቆሮ የሰማ ለት ያብዳል።
  የሆዳም ብቻ ሳይሆን የደናቁርት ስብስብ እንደነብሩ የሚያመለክት ከንቱ የሰቆቃ ድምጽ ነው። ግማሽ አካል እሳት ውስጥ እየነፈረ የተሰማ — ከተጣሉበት ጉድጓድ ውስጥ የጎነ ባዶ የጥርስ ማፋጨት ሊባል ይችላል። አይን እና ጆሯቸውን ደፍነው ሆዳቸውን ሲያዳምጡ ከርመው አሁን የጣእር ድምጽ ማሰማታቸው ሦስት እግራቸው ገደል በመግባቱ ተቀስቅሰው ይሆናል። በሬ ሆይ እያለ መዝሙር ሲያስጠናቸው ከርሞ ጭድና ሲበላና አሞሌ ሲልስ የከረመ በሬነታቸውን ዛሬ ገና ከተረዱ የሚያሳዝነው በስሙ የሚነግዱበት ሕዝብ እንጂ እነሱ አይደሉም።

 4. አስተኳሹ ብአዴን ምን እያለ ነው?
  የቀብር አፋፍ ኑዛዜ ወይስ የአስተኳሹ የተለመደ ጨዋታ?
  በቀፋፊ ሐውዜናዊ ድራማ የታጀበው የኢህአዴግ ቁ 1 እና ቁ 2 ንግሥና ከእያንዳንዱ የሚመደረክ ተውኔት ጀርባ ምን የድራማ ሥራ እንደሚሠራ እንድንመረምር ያስገድደናል።
  በአማራ ሕዝብ ላይ የሚነጣጠሩ ተኩሶች ዒላማቸውን እንዳይስቱ ከውስጥ አስተኳሽ ሆኖ የአማራን ሕዝብ ሲያስጠቃ የከረመው ብአዴን አዲስ የማስመቻ ስትራቴጂ ይዞ ብቅ ብሏል። እውነትስ አዲስ ነው ወይ? ከዚህ በፊትስ በተደጋጋሚ አልተጠቀመበትም ወይ ካልን የአስተኳሽ አስመቺነት ስትራቴጂ ተደጋግሞ ጥቅም ላይ የዋለ ነው። አዲስነቱ አስተኳሹ ወደ ጠላት ካምፕ አብሪ ጥይት የተኮሰና ጠላት ለሚያደርገው ጥቃት ማስመቺያ ሰበብ ወይም ተኩስ ማስጀመሪያ ምክንያት ወይም የጥቃት ዒላማ ማስተካከያ መምሰሉ ነው።
  ግልጽ ያልተደረገው መግለጫ መንስኤ ምን ይሆን? ምን ያመላክታል? ምን ሊያመላክት ይችላል?
  1. በአማራው ላይ ለሚፈጠር የኦህዴድ/ኦነግ ተጨማሪና ከበድም ያለ ጥቃት ግብዣ?
  2. ለግጭት ቱጃሩ ለአቢይ አህመድ የመግቢያ ቀዳዳ (ከኦህዴድ/ኦነግ ካምፕ ከሚሰጠው ግብረ መልስ በኋላ) ለመፍጠር?
  3. ወደ ኤርትራ ለሚታሰበው ጦርነት የፈረደበትን አማራ ለዳግም እርድ የሚነዱበትን ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት ለማስጀመር (የአቢይንም የብልጽግናንም የብአዴንንም ቅቡልነት ከወደቀበት በማንሳት)?
  4. የሀገር ፍርሻ የመጨረሻ ሰዐት ደወል በብአዴን ጭንቅላት ውስጥ ደውሎ ከሆነ ከመጪው ሕዝባዊ ቁጣ ራስን የማዳኛ የብለናል እኮ የመፍጨርጨሪያ ጥሪ ይመስላልን?
  5. ቁ4 እውነት ከሆነ ብለናልም ከማለትና ከመጪው ቁጣ ከመትረፍም አልፎ ሀገሩ ሲበተን በስሙ የሚነግድበተን የአማራ ክልል በተቆርቋሪ ስም የማስተዳደር አባዜ/የፍላጎት መግለጫ ይሆን?
  6. የሕወሃትና ኦነግ/ኦህዴድ ጥምረት የነሱን መመታት እርግጥ ያደረገበት፣ ከበድናዊ ሕልውናቸው የሚቀሰቅስ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው? ይሄ ከሆነ ጩኸቱ የሞት አፋፍ መንፈራገጥ ወይም ኑዛዜ ይሆንን?
  የብአዴንን ሎሌያዊ ታሪክ ላስተዋለ የኦህዴድና የኦነግን የሴልፊ ድግስ ለማድመቂያ የፌስታ ተኩሶችን ማስጀመሪያ ተኩስ የተኮሰ ነው የሚመስለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share