ሁለቱ ብልጽግናዎች ባደረጓቸው ጥሪዎች እያስደመሙን ነው!!!

የኦሮሚያው መሪ በፓርላማ አሸባሪ የተባለውን ” ሸኔ ” ን ፈቃድህ ከሆነ እንደራደር ሲሉ የአማራው ብልጽግና ደግሞ “ያለፈ ታሪክ ምርኮኛ “ያሏቸው ቡድኖች ” ሊበታትኑን ስለሆነ በጋራ እንታገላቸው ” ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አድርገዋል። በቀደመውና ባልቀደመው ስርዓት የበረከት ስምዖን ቃል አቀባይ የነበረ ሽመልስ ከማል የተባለ ጭሰታም በአንድ ወቅት ስለ ጸረ-ሽብር ህጉ ተጠያቂነት ሲያብራራ “በመንግሥት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ሠው ጋር የተገናኘ፣ አብሮ የተቀመጠ፣ ሻይ ቡና ያለ እሱ አሸባሪ ነው” ብሎን ነበር ፤ እንግዲህ ሳንሰማ ህጉ ተቀይሯል መሠለኝ ኦቦ ሽመልስ አሁንም ድረስ ንጹሀን ገበሬዎችን ሴትና ህፃናት የሚገድለውን ኦነግን እባክህ ና ብለውታል በርግጥ የፌደራል ፖሊስም ሆነ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ዜጎቹን ከመታረድ መታደግ ካልቻለ የንጹሀንን ሞት ከማስቀረት አንጻር (ማስቀረት ከተቻለ) የኦሮሚያው ብልጽግና ጥሪ አልጎረበጠኝም።

የገረመኝ የአማራው ብልጽግና ጥሪ ነው ኧረ ለመሆኑ ጥሪ ያደረጋችሁለት የኢትዮጵያ ህዝብ የትኛው ነው ? አንገረብ ወህኒ ቤት ያጎራችሁትን ነው? “የታሪክ ምርኮኞች አገራችንን እንዳይበታትናት ኑ አብረን እንታገል”ያላችሁት

ዘመኔ ካሴና መሰል ፋኖዎችን አስራችሁ ጥሪው ለማን ነው ? ኦነግ ሸኔ በጨፈጨፋቸው ዜጎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች ላይ ” ጥላ እንዲሆናቸው ዛፍ እንተክልላቸዋለን”እናንተ ግን ኑ አና በጠረጴዛ ዙሪያ እንደራደር እየተባለ ባለበት ወቅት መንግስት ድረስልኝ ብሎ ያደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ ለአገሩ መስዋዕትነትን የከፈለ የፋኖ ታጣቂን በየ ማጎሪያው አስራችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ ያደረጋችሁት ምን ዓይነት ሞራል ቢኖራችሁ ነው? ወይንስ ምን አጭሳችሁ ነው? ማን ከማን ያንሳል ብላችሁ ከሆነ ለኦሮሚያው ብልጽግና ጥሪ የሚመጣጠነው ጥሪ በጎ እንደሰራ ሁሉ ደርሳችሁ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፊጥ ከማለት አጠገባችሁ ላለው ለፋኖ ጥሪ አድርጉለት መጀመሪያ ያሰራችኋቸውን ፍቱና እዛው ተወያዩ። የማወራው ስለ Priority ነወ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጦማሪያኑን እና ጋዜጠኞቹን በተመለከተ ችሎቱ ለፖሊስ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላለፈ

ከ ሃኒ ገፅ የተወስደ

http://amharic-zehabesha.com/archives/180004

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share