ቲማቲምን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

• ቲማቲምን መመገብ ለቆዳ ጥራት ጠቃሚ ነው፡፡
ቲማቲም በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር ለቆዳ ተስማሚ የሆነ ሲሆን ቲማቲምን ልጦ የልጣጩን ውስጠኛ ክፍል በፊትዎ ላይ በመለጠፍ ለ10 ደቂቃ በማቆየት መታጠብ ንፁህና የሚያበራ ፊት እንዲኖርዎ ያደርጋል፡፡
• ቲማቲም የተለያዩ የካንሰር ዓይነቶችን ይከላከላል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ሊኮፒን የተባለ ንጥረ ነገር በፕሮስቴት ካንሰር፣የጨጓራ እና የአንጀት ካንሰርን የመከላከል አቅም አለው፡፡
• ጠንካራ አጥንት እንዲኖረን ያደርጋል
ቲማቲም በውስጡ ካልሲየም እና ቫይታሚን ኬን የያዘ ሲሆን ሁለቱም ንጥረ ነገሮች አጥንትአጥንት እንዲጠነክር ያደርጋሉ።
• ቲማቲም ለልባችን ጠቀሜታም አለው
ቲማቲም በቫይታሚን ቢ እና በፖታሺየም የበለፀገ ሲሆን ኮሌስትሮልን እና የደም ግፊትን የመቀነስ አቅምም አለው፡፡ ቲማቲምን በዕለት ተዕለት የምግብ ስርአትዎ ውስጥ ማስገባት ከድንገተኛ የልብ ሕመም እና ኮሌስትሮል እራስዎን ይከላከላሉ፡፡
• ለፀጉርዎ ጠቀሜታ አለው
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ፀጉርዎን ጠንካራና ያማረ እንዲሆን ያደርጋል።
• ቲማቲም ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ ዕድልዎን ይቀንሳል
• ለዓይንዎ ጥራት
በቲማቲም ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ኤ ለዓይንዎ ጥራት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡
ጤና ይስጥልኝ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ እንዴት በምግብ መመረዝ ሊሞቱ ይችላሉ? - በምግብ መመረዝ የሚከሰቱ 4ቱ ገዳይ በሽታዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share