February 12, 2023
2 mins read

“ሕይወት ለሀገር” ኢትዮጵያችን ቅጽ 6 ቁጥር 2

Ethiopiachinየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየጊዜው የደረሰባትን እና የሚደርስባትን መከራ በአምላክ ቸርነት፣ በአባቶች እና በምዕመናኑ ጥንካሬና እምነት እየተወጣች ዛሬ ላይ ደርሳለች።ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕጋዊውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶስን በመናቅ ሌላ የዘር እና የክልል ሲኖዶስ በህገወጥ መልኩ ሲሰየም “ከሰደበኝ ደግሞ የነገረኝ” እንዲሉ የጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ያሳዩት ተጨማሪ ንቀትና ትዕቢት የተሞላበት መግለጫ የተሰጣቸውን የውሃ ልክ በመዝለል ከፈጣሪ ተጋጩ። እምነት ማለት ምን እንደሆነ የሚማሩ ከሆነ እስኪያንገሸግሻቸው ድረስ የአባቶቻችን ጥንካሬ፣ የምዕመናኑን አንድነት ከሰሞኑ እንቅስቃሴ ሊገነዘቡት  ይገባል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደምት አምባገነን ገዥዎች ያስለመዱንን አምባገነናዊ መግለጫ ከማክተልተል ባለፈ መልኩ ምዕመናን በጥይት ቢቆሉ፣ ቢደበደቡ አካል ጉዳተኛ ቢያስደርጉ፣ ቀሳውስት በጥፊ ቢጠፈጠፉ፣ ልብሳቸውን አስወልቀው ቢቀጠቅጧቸው ወይ ፍንክች! ካለው ሕዝብ ያገኙት “ድል” ቢኖር ፍርሃት፣ መርበትበት፣ የአገዛዙ መናጋት፣ በሠራዊቱ ውስጥ “እኔም ለእምነቴ” ስሜቶች ለመሆኑ ቀጣይ ሂደቶች  እንደሚመሰክሩ መገመት አያዳግትም። —-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]…

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop