February 12, 2023
1 min read

የእሁድ እንጉርጉሮዬ – የእሁድ እንጉርጉሮዬ

የእሁድ እንጉርጉሮዬ

Abiy ahmed zinjero 1ጨለማው ረዘመ~ ምንም አልታየን፣
ጀንበር ብልጭ ብላ~ቀን በወጣልን።
በረጅም ሩጫ ~ ኖረን ስናሸንፍ፣
ወደ ሁዋላ ሆነ ~ላጭሩ ስንከንፍ ።
በጊዜ ውንበዳ~ መላ የለው ዘንድሮ፣
ቤተሰላም ሆነ~ጉልት ላምባጉሮ።
ስንበሌጥ ከመርን~ በጊዜ ገለባ፣
ድንጋይ ቤት አፍርሰን~ጎጆ ልንገነባ ::
ጸጥተኛ ቦታ ~ የነበረ ብቻ፣
በድንገት ሆነብን ~ አመጽ መዶለቻ።
ምን ይለው ነበረ~ ዋናው አስተማሪ፣
ትምህርቱ ሲጠፋ ~ ሳይቀር ፍርፋሪ?
ከመቶዎች በፊት ~ታሪክ መዝገቦታል፣
ጠብ መንጃና መስቀል~አንድ ላይ አይቶታል።
ማነው ተው የሚለው~ ሰላምን መካሪ፣
ሽማግሌ ሆኖ ~ዋናው ጸቡን ጫሪ ?
እንዴት ይጸለያል~ወዴት እንባ ይረጫል?
አስታራቂ የነበር~ ቀን በቀን ያጋጫል።
መለዮውን ጥለው~ ሥልጣን ላይ ሲወጡ፣
እልቂትን ነው እንጂ~ሰላም መቼ አመጡ?

አሸናፊ ዋቀቶላ፣ ሕ/ዶ – ፌብሩዋሪ 11፣ 2023

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop