ይድረስልኝ ላንተ በቁምህ ለሞትከው በደም ተጨማልቀህ ገምተህ ለሸተትከው February 9, 2023 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ይድረስልኝ ላንተ በቁምህ ለሞትከው በደም ተጨማልቀህ ገምተህ ለሸተትከው ክቡር አልልህም ክብር የት ታውቅና ዶክተር አልልህም ምኑን ተማርክና ሃገር ሞተች እንጂ ባንተ ድድብና እስኪ ልጠይቅህ ማነው ያለህ በርታ እንደዚህ አርክሶ ያጣላህ ከጌታ እንዳሻህ ገደልከን እንደጉድ ሞትንልህ ቤተ እምነት አቃጠልክ አልቅሰን ዝም አልንህ በርሃም ቀጣኸን ላንተም ጸለይንልህ ማን አይዞህ ብሎህ ነው አሁን የለየልህ ባንተ ዘመን እኮ አባቱን ያልሰዋ ወንድም ያልቀበረ እህቱ ተደፍራ ቅስሙ ያልተሰበረ እናቱ ታርዳበት በደም ያልሰከረ በጦቢያዬ ምድር ሰው የለም ነበረ ግን… ሁሉንም አልፈናል አዝነን ብናለቅስም ያሁኑ ድፍረት ግን አያለሳልስም ቤተ እምነቷ ሲነድ ይሁን ያልፋል ባለች ሃገር ሲተራመስ ምህላ በያዘች ካንተ ክፉ እንዲርቅ ጾማ በጸለየች ልጆቿን ሰብስባ ይቅር በሉ ባለች ፍቅር ባስተማረች ምኗ ቀሎህ ይሆን ባንተ የተደፈረች አላወክም እንጂ ኦርቶዶክስ መሆን የሃይማኖት ጥጉ ለእምነቱ መሞት ነው ወግ እና ማረጉ የአቡነ ጴጥሮስ የእየሱስ ልጆች ነን በሞት ውስጥ ነው ትንሳኤን ያገኘን ስለዚህ አንፈራም እመነን አንተ ሰው ረጋ በል ሰከን ሞትክን አታርክሰው። “የመጨረሻው ደብዳቤ” ፀጋየ ወልኪቴ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ የሚደርሰውን አፈናና በደል በ አስቸኳይ የማይቆም ከሆነ ከስልጣኔ በፍቃዴ እለቃለሁ Next Story የት ሄደች ኢትዮጵያ (አንዱ ዓለም ተፈራ)