June 11, 2016
4 mins read

አገዛዙ አለኝ የሚለውን ህገ መንግስት በተግባር ቀዶ ጥሎታል!

blue party

blue party
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

አገዛዙ ራሱ ያፀደቀው ህገ መንግስት አንቀፅ 15 ማንኛውም ሰው በህግ በተደነገገው ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ህይወቱን አያጣም በማለት ቢደነግግም ለአንድ ቀንም እንኳ ህግን አክብሮ የማያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን በጠራራ ፀሀይ መግደሉን ዋና ስራው አድርጎታል፡፡ በተመሳሳይ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 21 በጥበቃ ላይ ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰባዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት እንዳላቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸውና ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው ከሃኪሞቻቸውና ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም ዕድል የማግኘት መብት እንዳላቸው ቢገልፅም አገዛዙ በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የመፃፍ፣ የመናገርና የመደራጀት መብታቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው ብቻ በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ያለምንም ክስ ከአምስት ወራት በላይ ማዕከላዊ በሚባለው የዜጎች ማሰቃያ ጣቢያ ቆይቷል፡፡

እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ እና ከእሱ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች በማንነታቸው ብቻ በደል እንደሚደርስባቸው በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት ቢናገሩም አገዛዙ ከማስተካከል ይልቅ ለምን ተናገራችሁ በማለት በጨለማ ክፍል ወስጥ አሰሯቸው ይገኛል፡፡ አመፅ አነሳስታችኋል በሚል ክስ የቀረበባቸው ምክትል ሊቀመንበሩን አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮችና አባላት በቀጠሯቸው እንዳይቀርቡ ከመደረጉም በላይ የእስረኞችን ስነ ልቦና በሚጎዳ ሁኔታ ልብሶቻቸውን ተቀምተው በባዶ እግራቸውና በወስጥ ልብሶቻቸው ፍርድ ቤት ለመቅረብ ተገደዋል፡፡

በቂሊንጦ ማጎሪያ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አግባው ሰጠኝ ፣ዮናታን ተስፋዬ፤ ፍቅረማሪያም አስማማውና ብርሃኑ ተክለያሬድ በአሁኑ ሰዓት በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው የሚገኙ ሲሆን በቅርብ ዘመዶቻቸውና በጠበቆቻቸው እንዳይጎበኙ ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ አገዛዙ የራሱን ዜጎች በመግደልና በማሰር በስልጣን ለመቆየት መወሰኑን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የፈፀመው ወንጀል ያረጋግጣል፡፡ ስለሆነም ከዚህ አስከፊ አገዛዝ ተላቀን ህዝባዊ አስተዳደር መገንባት የምንችለው ሁላችንም ለመታሰርና ለመሞት ቆርጠን ስንነሳ ብቻ መሆኑን ተገንዝበን ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል

ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

bewketu seyoum hagere mariam maryland usa must listen
Previous Story

የዳያስፖራዎች ቤት ግብዣ | በእውቀቱ ስዩም

Next Story

Hiber Radio: ኤርትራ ሕወሓት አስቀድሞ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገች – አሜሪካ ኤርትራን አስታርቃለሁ አለች

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop