Hiber Radio: ኤርትራ ሕወሓት አስቀድሞ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገች – አሜሪካ ኤርትራን አስታርቃለሁ አለች

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሰኔ 5 ቀን 2008 ፕሮግራም

<...በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ግድያ ፣በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በአደባባይ ሲፈጸም የነበረው ቶርች፣ወታደሮች በግልጽ ሲገሉ ሲተኩሱ ጭምር እየታየ ይሄ ስርዓቱ የፈጠረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰደው ማለቱ የሚያሳፍር ሪፖርቱም ተቀባይነት የሌለውና ራሳቸው ይሄን ተቋም በገንዘብ የሚደግፉም ምዕራባውያን ጭምር የማይቀበሉት ነው ...አውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አካባቢ አንዳንዴ የፓርላማ አባላቱ አንዱ እኔ ለኦጋዴን መብት ብቻ ነው ብሎ ይጠይቃል፣ሌላው እኔ ለኦሮሞ ብቻ አንዱ ደሞ እኔ ለዚህ ብቻ ይላል ይሄን ማስተካከልና ቢያንስ በደላችንን ለማሰማትና ለመደመጥ መተባበር አለብን።ይህ ካልሆነ ግን...> አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም መቀመጫውን ቤልጂየም ያደረገው በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚሰራው ማህበር ዋና ዳይሬክተር የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ያወጣውን ሪፖርትና የፓርላማውን ውሳኔ በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<...የወያኔ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት ራሳቸው ገለው ራሳቸው አጣሪ የሆኑበት ጉዳይ በምንም መንገድ ተቀባይነት የለውም። ሌላው ቀርቶ አቶ ሀይለማሪያም በፓርላማ ስህተቱ የእኛ ነው ሲል የነበረውን የካደ በኦሮሚያ በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተመጣጣኝ እርምጃ ነው ያለ በየትኛውም ሕግ ፊት ተቀባይነት የሌለው ሪፖርት ነው ...በሕግ መርህ አንድን ጉዳይ ራሱ ባለጉዳዩ ወይም በደል ፈጻሚው አያጣራም በገለልተኛ አካል ነው መጣራት ያለበት የወያኔ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን የራሱን ወንጀል ለመሸፈን ያልቻለ ተራ ሪፖርት ነው። ይሄን ተቀባይነት የሌለው ሪፖርት ግን መቃወምና የሚፈጸመው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ላይ ትርጉም ያለው ተጽዕኖ እንዲደረግ በጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን።... > አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር የአገዛዙ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<...የታክስ ወቅት መጥቶ ባለፈ ቁጥር በየዓመቱ የተለያዩ የማጭበርበር ስልቶች ተግባራዊ ይሆናሉ አይ.አር.ኤስ ሳይቀር ዘንድሮ ከፍተኛ ማጭበርበር ደርሶበታል። ህብረተሰባችን ለእነዚህ በተለያየ መንገድ መረጃችን እጃቸው ለሚገባ አጭበርባሪዎች መጠንቀቅ አለበት።እነዚህ ተጭበርብረው ቀርበው ራሳቸውን ማስተማሪያ ያደረጉትን ከእኛ ስህተት ሌላው ይማር ያሉትን ሳላመሰግን አላልፍም...> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ ቲኬ ሾው አዘጋጅ በኤይ.አር.ኤስ ስም ስለሚያጭበረብሩ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያድምጡት)

ሟቹ መለስ ዜናዊ የቀመሩት የተቃዋሚዎች እግሮችን የመቁረጥ እቅድ ከኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ(ኦፊኮ)ቢሮ ዘልቋል።በርካታ የኦሮሞ ታጋዮች በሰበብ ባስባቡ ወደ እስርቤት ሲወረወሩ የፓርቲው መሪው ዶ/ር መረራ ጉዲና ግን እስከ አሁን ድረስ ለምን አልታሰሩም ? ዶ/ር መረራ ለጥያቄው አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተውበታል (ልዩ ጥንቅር)

በፍሎሪዳ በኢሚግሬሽን እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን መካከል ከእስር ቤት ከወጣው ከአንዱ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ(ያድምጡት)

በቬጋስ የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ኩባንያዎቹ የገቡትን ቃል ለመፈጸም አልቻሉም ራሳችንን በማህበር ማደራጀት አለብን ብለዋል(መልዕክታቸውን ይዘናል)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የኤርትራ መንግስት በጾረና ግንባር የሕወሓት ወታደሮች ጥቃት ሰነዘሩ ሲል የኢትዮጵያው አገዛዝ የካደውን ጦርነት ይፋ አደረገ

የአገዛዙ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰሞኑ ሪፖርትና የፓርላማ ውሳኔ በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደሌለው ተገለጸ

በኢትዮጵያ አትሌቶች መካከል የመከፋፈል ደመና ማንጃበቡ ተሰማ

“ፌዴሬሽኑ ለብራዚሉ የኦሎምፒክ ውድድር የመረጣቸው አትሌቶች እራሳቸውን ከአነ አትሌት ሃይሌ እና ከእነ ቀነኒሳ እራቁ፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰበር ዜና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ 

“አትሌቶቹ ወደዚህ ለምን እንዳልመጡ ጠንቅቀን እናውቃለን”አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ

በአውስትራሊያ ሜልቦርን አቶ አባይ ወልዱ የተገኙበት ስብሰባ በተቃው ተበተነ

የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኤርትራ መንግስት ላይ ያወጣው ሰሞነኛ ሪፖርት ምሁራኖችን እያነጋገር ነው

አሜሪካ ኤርትራ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደትተባበር ጥረት አደርጋለሁ አለች

በኢትዮጵያ ውስጥ 5.5 ሚሊዮን ህጻናት ለጉልበት ብዛበዛ መዳረጋቸው ታወቀ

የተመድ እና ግብጽ በሶማሊያ ስለወደቁት 60 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

የኢሕአዲግ መንግስት ግን “የሞተብኝ ሆነ የቆሰለብኝ ወታደር የለም ፣በአልሽባብ ላይም ድልን ተቀዳጅቻለሁ”ይላል

እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Share