October 7, 2022
15 mins read

አማራ ሆይ በድርድር ስም እዳትሸወድ!! – ተዘራ አሰጉ

Amharaድርድር ፣ ሽምግልና ፣ ሰላማዊ ውይይት ፣ ከተቀናቃኞች ፣ ከተፋላሚዎች ፣ ከተቀያየሙ ከዚያም አልፎ ደም ከተቃቡ ባለአንጣዎች ፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ጋር ማከናወን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ቀደምት ባህላዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ሃይማኖታዊ ፣ ቤተሰባዊና በሕግ ማዕቅፍ ተካቶ የሚካሄድ የተቀደሰ  ነባራዊ ኩነት ነው።

ኢትዮጵያዊያን የቤተሰብ ሽምግልና ፣ አውጫጭኝ፣ አፍርሳታ ፣ ጉማ ፣ የዕርቅ ኮሚቴ ወዘተ እያሉ የተለያየ ስያሜ ቢሰጡትም ዞሮ ዞሮ ኢትዮጵያ ዕምቅ የሆነ የድርድርና የዕርቅ መቸቶች እንዳሏት ልብ ሊባል ይገባል።

“ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች” እንዲሉ ሆነና ሃገረ ኢትዮጵያ  በኮንጎ ፣ በቲሪፖሊ ሊቢያ፣ በኮሪያ ፣ በሱዳን ፣ በሩዋንዳ ወዘተ ሰላም አስከባሪ ፣ የመጀመርያዋ የተባበሩት መንግስታት League of Nations” የአፍሪካ ብቸኛ ተወካይ ፣ አደራዳሪ ፣ አስታራቂና ችግር ፈች ሃገር እንዳልነበረች “ የጉድ ጉዶችና አዋራጆች” ተፈጠሩና ከነበረችበት ማማ እያወረዷት ይገኛሉ።

“ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል “ እንዲሉ ነፃነታቸውን በደማችን ያስከበርንላቸው ፣ የአፍሪካ አንድነትን (OAU)ን አቋቁመን “ በክብርና በነፃነት ኑሩ” ብለን ጀባ ያልናቸው አፍሪካዊያን እኛኑ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ባለቤትና ኩሩ ሕዝቦችን ፣”ኑ – እናስታርቃችሁ” እያሉን ነው ፣ ዘይገርም ነው።

ጊዜ ያመጣውን ጊዜ እስኪመልሰው “ “ይሁን” ከማለት ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል ጎበዝ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታላቁ ኢትዮጵያዊ ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና በአጋር ጥቂት አፍሪካዊያን በሳል የዘመኑ መሪዎች የተቋቋመው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት /OAU/ የህውሃትን ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ የገነገነ ተንኮል ፣ ስግብግብነት ፣ ተስፋፊነት ፣ የመሬት ነጣቂነት ፣ ዘራፊነት ወዘተ በጥልቅ ሳይገነዘቡና ሳይብራራላቸው በደረቁ ይህን ስር የሰደደ ችግር ሊፈቱት ይቻላቸዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ በአፅንኦት መልስ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ ነው እንላለን።

ግፍ ፣ በደል ፣ ሞትና መፈናቀል ለደረሰበትና ለዓመታት ከህውሃት ጋር ፍልሚያ ላይ ለነበረ የአማራ ሕዝብ “ ከህውሃት ጋር መደራደር ጉም እንደ መዝገን” ና “ ውሃ ቅዳ ፣ ውሃ መልስ” መሆኑን አስረግጠን እንናገራለን።

በድርድር ስም እነ ኢዲዮን ፣ ኢሕአፓን ፣ እራሱን ደርግን ፣ ኢሰፖ ተብየውንና መሪዎቻቸውን ሁሉ ቅርጥም አርጎ የበላ ብልጣብልጥና መሠሪ ቡድን ልብ ገዝቶ ይደራደራል ማለት ዘበት ነው። ለማዘናጋት ፣ ትንፋሽ ለማግኝትና ጊዜ ለመውሰድ ካልሆነ በቀር ።

“ግራ ነፈሰ ቀኝ” ግን አሀን ባለው ተጨባጭ ሀኔታ  የድርድር ህሳቤው በራሱ ለህውሃት “ሠርግና ምላሽ” ሲሆን ለሰላም ፈላጊው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በተለይ ለአማራው ሕዝብ “መርዶ ተነግሮት ሃዘን ላይ ቁጭ የሚባልበት” ክስተት ነው እንላለን ። ምክንያቱም ቢሉ ህወሃት እንደ ኢሰፓ ፣ ኢሕአፓ ፣ መሄሶን፣ ኢዲዮ ወዘተ ታሪክ ሁኖ ካልከሰመ በቀር ኢትዮጵያ የሰላም እንቅልፍ ትተኛለች ብሎ ማሰብ ዘበት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፍሪካ አንድነት /OAU/ የተወሰኑ በግጦሽ መሬት መገፋፋት ፣ በብሄሮች መካከል በሚነሳ ግጭት ፣ በዘር ማጥፋት ወዘተና በመሳሰሉ ምክንያቶች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ሞክሯል ፣ የተሳካለት ሁኗል ለማለት ግን ፍፁም አይቻልም።

ነገር ግን በአፍሪካ ሆነ በዓለም ታይቶ የማያውቅ በአንድ ሃገር ውስጥ እየተኖረ ለም መሬት በመፈለግ ብቻ የወልቃይትና የራያን ምድር በማናለብኝነት ነጠቆ ታላቂቷን ትግራይ የመመሥረት እኩይ ዓላማ ይዞ የተነሳው ቡድን ይህ ተንከሲስ ዓላማው ለአደራዳሪዎች በጥናት ተደግፎ በግልፅ እስካልተነገራቸው ድረስ እንዲሁም ለክፋትና ለመሰሬ አላማው ባፀደቀው ሕገ-መንግስትና ለሰላሳ ዓመታት ወልቃይት ፣ ጠገዴና ራያ በትግራይ ስር ያለአግባብ አካቶ በመኖሩ ይህን መሰሬ ኩነትና አካሄድ ተከትሎ ያለፈና የነበረው ሕገ ወጥ እካሄዱ /status quo ante/ ይጠብቅ የሚለውን  የቅዥት : ጉንጭ አልፊ የዘወትር ልፈፋውን በማንሳት ይቀጥልልኝ ስለሚል ይህንንም ድብቅ ዓላማውን አወያዮቹ አፍሪካዊያን በግልፅ ሊያውቁትና “አይሆንም  “ይህ አጉራ ዘለል ህሳቤ ለድርድር አይቀርብም” ሊባል ይገባዋል እንላለን።

“የድርድሩም ቅድመ ሁኔታ በዚህ መሰረተ ሃሳብ ታንፆ ሊጀመር የግድ እንደሆነ” እኛ መላ ኢትዮጵያዊያንና የአማራ ሕዝቦች እናሳስባለን ፣ እናስጠነቅቃለን ።

ቀደምት የኢትዮጵያ ፣ የአማራና የትግራይ ታሪካዊ ፣ ባሕላዊና ጆግራፊያዊ አቀማመጥን በተመለከተ  አደራዳሪዎች አፍሪካውያን በግልፅ ሊያውቁ ፣ ሊብራራላቸውና ግንዛቤ ሊኖራቸው የግድ የሚል ይሆናል እንላለን።

አይበለውና ድርድሩ ከተካሄደ ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ድርድሩ አካታች (Inclusive)ና የተዋጣለት ይሆን ዘንድ የአማራ በተለይም የጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ፣ የወሎ ራያ የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የአፋር አባቶች ፣ የታሪክ አዋቂዎች ፣ ሙሁራንና የሚመለከታቸው ተቋማት ሁሉ ሊሳተፉ የግድ ይላል።

ከዚህ ጋር አያይዞ እንደአለመታደል ሆኖ አፍሪካዊያን ፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና መሪዎች /OAU/ አደራዳሪ በሆኑበት ወቅት ያጋጠመውንና በዚህ ድርድር ሊያጋጥመው የሚችለውን መሰናክሎች  ችግሮችና እፀፆች መዳሰሱ ከወዲሁ ሊከሰት የሚችሉ ሰንኮችን ለመገንዘብ ይረዳ ዘንድ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ተደራዳሪዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።

አፍሪካ አንድነት ድርጅት /OAU/ በቡርንዲ፣ በሱማሊያ ፣ በሊቢያ፣ በኮንጎ ፣ በኮትዲቪያር ፣ በደቡብ ሱዳንና መሰል የአፍሪካ ሃገሮች ግጭቶችን ለማብረድ የድርድርና የውይይት መድረኮችን አዘጋጅቶ ነበር።

አፍሪካ አንድነት ድርጅት /OAU/ መሰል ድርድሮች ሲያካሂድ ያጋጠመው ዋነኛው ችግር ድርድሩን ለማከናወን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረትና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የምግብና የመልሶ ማቋቋም ድጋፎች የማድረግ አቅም ማነስ ዋናው ማነቆው እንደነበር የጥናት ዳሰሳዎች ያስረዳሉ።

ሌላው ተደራዳሪዎችን አስመልክቶ እውነተኛ፣ የተሟላ ፣ ወጥና ሙሉ መረጃ አደራዳሪዎች ማግኘት አለመቻል ትልቁ ክፍተትና ፈተና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት /OAU/ እንደሆነበት የምርምር ዳፋዎች ያሳያሉ።

ከዚህ ባሻገር አደራዳሪዎች በሙስና እንደሚዘፈቁ ፣ ለወዳጅ ቡድኖች የማድላትና የመወገን ብሃሪና አካሄድ እንደሚታይባቸው የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ይተነትናሉ።

በዚህም ምክንያት በአፍሪካ አንድነት (OAU) የሚከናወኑ ድርድሮች አሰልች ፣ የተራዘመ ጊዜ የሚወስድ ፣ የይስሙላና እጃቸው በረዘመው ምዕራባውያን ሃገሮች የሚዘወር የመሆን ምልክቶችን እንዳሉ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው።

በዚህም የተነሳ “ ከድጡ ወደ ማጡ” እንዲሉ ታላቋን የአፍሪካ ቅምጥል ሃገር ሊቢያን መቀመቅ እድትገባ ምክንያት የሆነ ፣ ሱማሊያ በእርስ በርስ ግጭት እድትታመስ፣ በተፈጥሮ ሃብት ተወዳዳሪ የለላትን የኮንጎን ምድር የምድር ሲኦል እድትሆን መንስሄ የሆነው በአንድ እግሩ ያልቆመው፣ እንደ ፈረስ ተጋላቢውና አሻጉሊቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት /OAU/ መሆኑን የሃገሬ ህዝብ ሊያውቅ ይጋባዋል እንላለን።

የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው በመምራት የሚደራደሩት የአማራው ብልፅግና መሬ የሆኑት የተከበሩ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሆይ “ እንግዲህ ፈረሱም  ሜዳውም ይሄው” እንዲሉ ፣ እንደዚህ በፊቱ ተጋድሎዎትና ቆራጥ አቋምዎት ወያኔ -ህውሃት የኢትዮጵያን ድንበር ለሱዳን ታልፎ ይሰጥ ዘንድ ፊርማዎን ያስቀምጡ ሲባሉ “ የኢትዮጵያ መሬትን አሳልፌ ለሱዳን መስጠት አይዋጥልኝም ፣ አሻፋረኝ” እንዳሉት ሁሉ ፣ አሁንም “ ወልቃይት ፣ ጠገዴ ፣ ሰቲት ሁመራና ራያ  “ የአማራ እንጂ የትግራይ ሆኖ ፣ አያውቅም ፣ ሉድርድርም አይቀርብም “ በማለት ለሃገርና ከማህፀኗ ለውጡበት የአማራ ሕዝብ ዘብ እንደሚቆሙና የታሪክ አሻራዎን በድጋሜ ያድሳሉ ብለን   እንጠብቃለን ፣ “አደራ በምድር ፣ አደራ በሰማይ”  እኛ ኢትዮጵያዊያንና የአማራ ወገኖችዎ ከልብ በመነጨ እሳቦት  እናሳስበዎታለን።

በመጨረሻም የአማራ ሕዝብ ሆይ በድርድር ስም የተዘጋጀልህን ወጥመድ እድታውቅ ፣ እድትረዳና ጉዳዩን በአፅንኦት እድትከታታል በአደራ ስም እናሳስባለን ።

አምስት ሚሊዮን የማይሞላ አማፂ ፣ ዘራፊና ስግብግብ ህወሃት የተባለ ቡድን ለድርድር ሲጠራ ከአምሳ ሚሊዮን በላይ የሆንከው የአማራ ሕዝብ እንዲህም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ሰው ሰራሽ ግጭት ገፈት ቀማሽ የሆንከው ትሁቱ የአፋር ሕዝብ በድርድሩ ያልተካታታችሁበትን መንስሄና የጀርባ ውጥን ሴራን ልትመረምሩ የግድ ይላል እንላችኋለን።

በመጨረሻም “ጀሮ ያለው ይስማ” እንዲሉ የህውሃት የአራት ኪሎ የሚኒልክ ቤተመንግስት ህልም እንደ ጉም ቢትንም ፣ የወልቃይትና የራያን ጉዳይ ለድርድር ማቅረቡ አይቀሬ ስለሚመስል ፣ አራት ኪሎ የከተሙት የዘመኑ ሹመኞች ሥልጣናቸውን የሚቀናቀን እስከሌለ ድረስ የወልይቃት ፣ ጠገዴና የራያን ጉዳይ ለድርድር ቢቀርብ ጉዳያቸው እንደማይሆን ህሳቤ ስላለ የአማራ ሕዝብ ሆይ “  በድርድር ስም እዳትሸወድ” ጥንቃቄ አድርግ ብለን እንመክራለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop