October 7, 2022
14 mins read

የኤፍሬም ማዴቦ ሸፍጥ፤ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ – መስፍን አረጋ

Ephrem Madebo

“በዛሬዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ግልጽ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሁለት ትልልቅ ቡድኖች አሉ፡፡  እነዚህ ሁለት ኃይሎች … አማራ ብልፅግና እና ኦሮሞ ብልፅግና ውስጥ ካሉ ኃይሎች ጋር በቅርብ የተሳሰሩ ናቸው፡፡  ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው የፖለቲካ ምስቅልቅል እነዚህ ሁለት ኃይሎች … የሚያደርጉት ትግል ውጤት ነው፡፡”  ኤፍሬም ማዴቦ

Ephrem Madebo

የአማራ ሕዝብ ዋና የሕልውና ጠላት ወያኔም ኦነግም ሳይሆኑ ጭራቅ አሕመድ እንደሆነና፣ ጭራቅ አሕመድም የአማራን ሕልውና ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው በጉዳይ አስፈጻሚው በብአዴን አማካኝነት እንደሆነ የአማራ ሕዝብ ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ ተረድቷል፡፡  በተለይም ደግሞ ከዘመኔ ካሴ እስር በኋላ፣ የአማራ ሕዝብ ብአዴንን በድን አድርጎ ወደ መቃበር በመሸኘት፣ ጭራቅ አሕመድን ጉዳይ አስፈጻሚ አሳጥቶ ሕልውናውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ መነሳሳት አሳይቷል፡፡

አማራ የሚድነው ብአዴንን በመግደል ብቻ ስለሆነ፣ የብአዴን በድን መደረግ ሁሉንም ፀራማሮች እጅጉን ያስጨንቃቸዋል፡፡  ከነዚህ የብአዴን በድን መደረግ እጅጉን ከሚያስጨንቃቸው ውስጥ ደግሞ አንዱ ኢዜማን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው የብርሃኑ ነጋ አንጃ ነው፡፡  አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ኦ-ብልፅግና … አ-ብልፅግና በሚል ርዕስ በቅርቡ የጦመራት ጦማር ደግሞ ሌላ ምንም ሳትሆን የዚሁ የኢዜማ ጭንቀት መግለጫ ናት፡፡

የአማራ ሕዝብ በብአዴን ጉዳይ አስፈጻሚነት በኦነጋውያን ሲጨፈጨፍ ኤፍሬም ማዴቦ ድምጹን አጥፍቶ ተቀምጦ ነበር፡፡  የአማራ ሕዝብ አስጨፍጫፊውን ብአዴንን በድን ለማድረግ በነቂስ ሲነሳሳ ግን፣ ኤፍሬም ማዴቦ የሸፍጥ ብዕሩን አንስቶ የአማራ ሕዝብ በኦነጋውያን መጨፍጨፍ የሚያሳስበው መስሎ ብቅ አለና፣ የአማራ ሕዝብ የሚጨፈጨፈው የኦሮሞ ብልፅግና እና የአማራ ብልፅግና በሚያደርጉት ትግል ሳቢያ ነው አለ፡፡

ስለዚህም፣ በኤፍሬም ማዴቦ ምክር መሠረት የአማራ ሕዝብ ከመጨፍጨፍ የሚድነው የአማራ ብልፅግናን (ማለትም ብአዴንን) ካዳነ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡  ኤፍሬም ማዴቦ በጦማሩ ማስተላለፍ የፈለጋት መልዕክት ይችና ይች ብቻ ነች፡፡  የመልዕክቷ ብቸኛ ዓላማ ደግሞ ለብአዴን ጥብቅና መቆም ነው፡፡

ብአዴን ማለት የአማራ ሕዝብ ወኪል ነኝ የሚል፣ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት የሆነው ወያኔ የመሠረተው፣ ስማቸው አማራዊ ቢሆንም ከወያኔና ከኦነግ በላይ አማራን የሚጠሉ ፀራማራወች የተሰባሰቡበት፣ የአማራን ሕዝብ በግፍና በገፍ የሚያስጨፈጭፍ ፀራማራ ድርጅት ነው፡፡  ኢዜማ ደግሞ ሕብረብሔራዊ ነኝ እያለ የአማራን ብሔርነት የማይቀበለው አንዳርጋቸው ጽጌ እና፣ ዜግነትን አራምዳለሁ እያለ አማራ መጤ ነው የሚለው ብርሃኑ ነጋ የመሠረቱት ፀራማራ ድርጅት ነው፡፡  ስለዚህም ኢዜማ ለብአዴን ጥብቅና ባይቆም እንጅ ቢቆም አያስገርምም፣ ያይጥ ጠበቃዋ ድንቢጥ ናትና፡፡

ብአዴን ግን የአማራ ሕዝብ አንቅሮ የተፋው አክታ ነው፡፡  የተተፋ አክታ ደግሞ ተመልሶ አይዋጥም፡፡  ብአዴን ግን የአማራ ሕዝብ አሽቀንጥሮ የደፋው ግም ውሃ ነው፡፡  የተደፋ ውሃ ደግሞ ተመልሶ አይታፈስም፡፡  የአማራ ሕዝብ ማድረግ ያለበትና የሚችለውም አክታውን መጠራረግ፣ ግማቱን ማጥፋት ብቻ ነው፡፡  ይሄን ለማድረግ ደግሞ በነቂስ ተነሳስቷል፡፡  አንዴ አማራ የሚባል ብሔር የለም፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አማራ መጤ ነው እያለ ራሱን በራሱ የሚቃረነውን፣ የብአዴን አጋር የሆነው ኢዜማን ክፉኛ ያስጨነቀው ደግሞ የአማራ ሕዝብ ባስጨፍጫፊው በብአዴን ላይ በነቂስ መነሳሳቱ ነው፡፡

ኤፍሬም ማዴቦ የአማራን ሕዝብ ለማጭበርበር አማራ ብልፅግና ቢልም፣ እውነታው ግን የአማራ ብልፅግና የሚባል ቡድን ከናካቴው የሌለ መሆኑ ነው፡፡  ያለው ብልፅግና አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም የኦሮሞ ብልፅግና ነው፡፡  የአማራ ብልፅግና የሚባለው ስብስብ የኦሮሞ ብልፅግና፣ በተለይም ደግሞ የበላዔ አማራው የጭራቅ አሕመድ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጅ ራሱን ችሎ የቆመ ድርጅት አይደለም፡፡  ይህ ራሱን የአማራ ብልፅግና የሚለው የጉዶች ስብስብ፣ የኦሮሞ ብልፅግና አሽከር እንጅ አጋር አይደለም፣ ሊሆንም አይችልም፡፡  ወያኔ ብአዴንን ሥራየ ብሎ የፈጠረው ካሽከርነት ውጭ እንዳይታየው አድርጎ ስለሆነ፣ ብአዴን አሽከር እንጅ አጋር ወይም ተገዳዳሪ ለመሆን ተፈጥሮው አይፈቅድለትም፡፡  

የብአዴን አለቃ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ቢባል በቤተመንግስት አጥር ዘሎ ይጠፋል ሲል አንድ ታዋቂ ግለሰብ የተናገረው፣ የብአዴኖችን አሽከራዊ ሰብዕና ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል፡፡  አንዴ ብአዴን ሁሌም ብኣዴን፣ አንዴ አሽከር ሁሌም አሽከርአንዴ ሎሌ ሁሌም ሎሌ፡፡

ዐይጥ ወልዳ፣ ወልዳ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ እንዲሉ፣ የብአዴን አባል የነበረ ሁሉ ካሽከርነት ወጣ ሲባል፣ ጅራቱ እስኪቀር ከጠበቁ በኋላ ወያኔና ኦነግ እጁን ቀስ አድርገው ይዘው በቀላሉ ወዳሽከርነቱ ይመልሱትና እውር ቢሸፍት ጓሮ ለጓሮ ብለው ይዘባበቱበታል፡፡  ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የተፈጠርኩት ላሽከርነትና ላሽከርነት ብቻ ነው ብሎ በሙሉ ልቡ እንደሚያምንና፣ አሽከርነት ይቅርብህ ቢሉት እንኳን እምቢ አሻፈረኝ እንደሚል ስለሚያውቁ ነው፡፡  ለዚህ ደግሞ የብአዴኑ አገኘሁ ተሻገር ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡  አገኘሁ ተሻገር አሽከርነት በቃኝ ያለ መሰሎ ወልቃይትን ብሰጥ አንገቴን እሰጣለሁ አለ፡፡  የኦነግ ጌቶቹ ፊታቸውን ኮስተር ሲያደርጉበት ግን ኩምሽሽ ብሎ ወደ አሽከርነቱ ተመለሰና፣ ወልቃይትን የሚጠብቁትን ፋኖወች ማሳደድ ጀመረ፡፡

በረከት ስምዖን በአማራ ሕዝብ ላይ ለፈጸመውና ላስፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በስቅላት መቀጣት ያለበት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ቢሆንም፣ የግለሰቡን የሰውን ምንነት የማንበብ ችሎታ ግን አለማድነቅ አይቻልም፡፡  የሎሌነት ሰብዕና ክፉኛ የተጸናወታቸውን ደመቀ መኮንንን፣ ተመስገን ጡሩነህን፣ አገኘሁ ተሻገርንና የመሳሰሉትን ለይቶ አውቆ፣ ከየቦታው አሰባስቦ የቅርብ ሎሌወቹ ማድረግ ልዩ ክሂሎትን ይጠይቃል፡፡

አወ፣ ብአዴን ሲባል ሎሌነት በተፈጥሮው የተጠናወተው፣ ላሽከርነት የተፈጠረ ዘላለማዊ አሽከር ነው፡፡  አሽከር ደግሞ የታዘዘውን ሁሉ አሚን ብሎ ይፈጽማል እንጅ አይገዳደርም፡፡  እገዳደራለሁ ካለ ደግሞ እድለኛ ከሆነ እንደነገዱ አንዳርጋቸው ይባረራል፣ ዕድለኛ ካልሆነ ደግሞ እንደነ ዶክተር አምባቸው ይገደላል፡፡  ስለዚህም አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የአማራ ሕዝብ የሚረጋገጠው በኦሮሞ ብልፅግና እና በአማራ ብልፅግና ሽኩቻ ሳቢያ ነው ሲል፣ እየሸፈጠ ነው፡፡  ሸፍጠኝነት ደግሞ የቀድሞቹ ኢሕአፓወች ያሁኖቹ ኢዜማወች ጥርሳቸውን የነቀሉበት ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በልቶ የማይጠረቃ አረመኔ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ የአማራን ሥጋ የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብአዴኖች ናቸው፡፡  በተለይም ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች (ማለትም ረዝመው ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ፣ canines ) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡  በመሆናቸውም፣ ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ መብላት አቅቶት፣ የሰው ሥጋ ጠኔ ናላውን አዙሮት፣ ራሱን ስቶ እንዲወድቅ ብአዴናዊ ጥርሶቹን ማርገፍ ብቻ በቂ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ መንጋጋወቹን እነ ግርማ የሽጥላን እና ሰማ ጡሩነህን መንቀል፣ ክራንቻወቹን ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህን ደግሞ መመንገል የግድ ነው፡፡

የየቀበሌው ደመላሽ ፋኖ ዋና ሚና መሆን ያለበት ደግሞ በየራሱ ቀበሌ ላይ የተተከሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች ባስፈላጊው መንገድ መንቀል፣ መመንገል፣ ማፍለስ፣ ማወላለቅ ነው፡፡

የነ ኤፍሬም ማዴቦ ጥረት ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ብአዴናዊ ጥርሶች እንዳይነቃቀሉበትና፣ የአማራን ሕዝብ እየቆረጣጠመ መሰልቀጡን እንዳያቆም ነው፡፡ ይህን ጥረታቸውን ለማሳካት የሚሞክሩት ደግሞ ለአማራ ሕዝብ የሚያስቡ መስለው፣ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሁነው በመቅረብ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ ሕልውናህን ማስጠበቅ የምትችለው፣ የሕልውናህ ጠላቶች የወያኔና የኦነግ ጉዳይ አስፋጻሚ የሆኑትን ብአዴንን እና ኢዜማን መስማት አቁመህ ራስ፣ በራስህ፣ ለራስህ ስትቆም ብቻ ነው፡፡ በእውነተኛ አማራዊ መሪ እየተመራህ፣ የአማራ፣ በአማራ፣ ለአማራ ብለህ ከቆምክ ማንም ከፊት አይቆምም፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

4 Comments

  1. በውነቱ አንድ ግራ የገባኝ ነገር አለ? ኤፍሬም ማዲቦ ከደቡብ ብርሃኑ ነጋ ከጉራጌ ይመስሉኛል ወደፊት ሰክን ብለን የ ዲ ኤን ኤ ምርመራ በሃገር አቀፍ ደረጃ እስከምናደርግ ይህ የዘውግ ፖለቲካ ሁሉም የኔ ነው በሚል እምነት ሁሉንም በማጋበስ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ የብርሃኑና የማዴቦ የጎራጌና የደቡብ ህዝብ አማራው ጠፍቶ እነሱ ምን ሊበጃቸው ነው? አዲስ አበባ በጋሙ ተወላጆች ላይ የደረስውን ማስታወስ ተገቢ ይመስላል ይህ በትንሹ ነው፡፡ በዚህ ላይ ማዴቦ ኤርትራ ምድረ ባንዳ ቁሞ ያጨበጨበለትንም አንረሳውም፡፡ ይህን አስመልክቶ አቶ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) ስለዘገበው ማመሳከርም ይቻላል፡፡ ስለዚህ አዛውንቶች አደብ ግዙ ያላችሁ እድሜ በጣት የተቆጠረ ስለሆነ ስለ ሃገር አንድነት ስለ ሰብአዊነት ኑሩ አማራው ተጎሳቁሎ፤ተገድሎ፤ተጨፍጭፎ ማንም ይመቸዋል ብለህ አታስብ፡፡ ኢትዮጵያ ካልኖረ ማንም አይኖርም ለኢትዮጵያ መኖር ደግሞ ተወደደም ተጠላም ለኢትዮጵያ መኖር አማራ ዋልታ ነው ፤ሚዛን አስጠባቂ ነው፤ ሚዛናዊ ፍርድ ሰጭ ነው፡፡ ትህነግ የሰጠህን ሳታላምጥ እየዋጥክ አገር ጤና አትንሳ አማራው ትግሬ ያደረገውን ኦሮሙማ ያደረገውን አድርጎ ቢሆን ዛሬ ጠቅላላ ኦርቶዶክስ ጠቅላላ አማርኛ ተናጋሪ በሆነ ነበር ለዚህ ነው አማራ ይሉኝታ ያለው ህዝብ ነው የምልህ፡፡ ከዚህ በፊት የሰጠኸው መግለጫ አንዱም ሳይቀር በማህደራችን ተቀምጧላ እድሜ ለኢትዮጵያ ልጆች፡፡ አዛውንት የግምቦት 7 የናንት ስራ አልተነካም የተረሳም አይምሰላችሁ ፍትህ እስኪመጣ እየባነናችሁ ትኖራላችሁ ኦሮሙማ አያድናችሁም ኦሮሙማ ሊያስጠልለው የሚችለው አንዳርጋቸው ጽጌን ሊሆን ይችላል እሱም መኖር ከቻለ፡፡

  2. I hate to say but I have to say that these guys are in state of total political stupidity and moral bankruptcy! The only way out to the people of Ethiopia is to carry out a well-determined, coordinated and targeted political struggle so that the political system they (these guys) stick with must be defeated and a true system of democratic transition must be realized! The rest is just the politics of garbage in and garbage out !

  3. አቶ መስፍን ለመሆኑ አቶ ኤፍሬም የጻፉው ገብቶሃል? እኔ በፍጹም የገባህ አልመሰለኝም፣ ወይም መልስህ ብጭፍን ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነው፣ በምንም አይን እየው አቶ ኤፍሬም በዚህኛው ጽሁፉ ላይ የሚለው አማራው ኢትዮጵያ ውስጥ መጫወት የሚገባውን ሚና አንድም መሪ ስለሌለው አንድም 30 አመት በተሰራበት ሴራ መጫወት አልቻለም ነው። ይህ አባባል ስህተቱ ምን ላይ ነው? እንዲህ አይነት ምክንያታዊ፣ ትልቅና አሰተዋይ እይታ ካንተና አማራን አትንኩ ከምትሉ ሰዎችም አላየንም። ለምንድነው የወረድክበት? ሌላ ቂም አላችሁ ወይስ በዚህ ጽሁፉ ነው? እስኪ ጽሁፉን እንደገና ደጋግመህ አንብበው። በኔ በኩል ይህ የአቶ ኤፍሬም ጽሁፍ ብዙ አማራዎችን ማንቃት አለበት ባይ ነኝ

  4. አቶ ጌታቸው መስፍን አቶ ሳይሆን ፕሮፌሰር ነው ለዛውም የፊዚክስ በዚህ ለቀቱ ሳትወድ በግድ እንድታደርገው ያደርግሃል ነገሮችን ካንተ ቀድሞ ለመረዳት ችሎታውን አዳብሯል አንተን የገባህ ለእሱ በጣም ያንሰዋል፡፡ በተረፈ መስፍን እርሶ በሉኝ አይልም የደረሰበት በራሱ ስለሚናገር ኤፍሬምን መስፍን ከሚገባው በላይ የሚያውቀው መሰለኝ ያለፈው እውቀቱ መሰለኝ ይህን አስተያየት እንዲሰጥ የገፋው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Amhara
Previous Story

አማራ ሆይ በድርድር ስም እዳትሸወድ!! – ተዘራ አሰጉ

bayisa wak woya `
Next Story

የዛሬው ያገራችን ሁኔታ ከዲፕሎማሲ አንጻር ሲታይ – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop