August 9, 2022
1 min read

አታውሩልኝ ሌላ (አሁንገና ዓለማየሁ)

Poem 1

አታውሩ ሌላ

ይልቅ አውሩልኝ/ ስለ መንደሬ/ ስለ ጎጤና/ ስለ ጓሮዬ

ከሱ በስተቀር / ሌላ ሌላ ግን/ ፈጽሞ አይስማ/ ይሄ ጆሮዬ

እስኪ ዙሩልኝ /አንድ ሺህ ጊዜ /ያንኑ ጓይላ

እኔም አዙሮኝ/ ድፍትፍት እስክል/ የ-እን-ግ-ሊ-ላ

እስኪ ውረዱ አስወርዱኛ ያንን ረገዳ

ስብር እስከሚል ስብር-ብር-ብር-ብር ያጥንቴ አገዳ

እስኪ አንዘፍዝፉኝ ተንዘፍዘፉና በዚያ እስክስታ

ወባ እንደያዘው ዝልፍልፍ ብዬ እስክወድቅ ማታ

አትቀይጡብኝ ሌላውን ወሬ ሌላ ጨዋታ

ያችኑ ጎጤን ያሳይ ኢቲቪ ፋና እና ዋልታ

ያንኑ ጥለት ልየው በቀሚስ ልየው በኩታ

ያንኑ ምግብ ልየው በሰፊው ሞልቶ ገበታ

የሌላ ወሬ አይደባለቅ

በሌላ ነገር አይጨማለቅ

የጓሮው ብቻ ያ የመንደሬ

ሲነጋም ሲመሽ ይነገር ወሬ

ደስ ደስ ይበለኝ ትጥበብ ሰፈሬ

ከክልል በታች ክልል ከልሎ ይከለል አጥሬ

ከመቶ ሚልዮን ቅንስንስ ብሎ አንድ ይሁን ቁጥሬ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ETEC78
Previous Story

የኢትዮጵያ ጂዲፒ ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ብር ተመነደገ!!! (122 ቢሊዮን ዶላር!!!) የመደመር ኢኮኖሚክስ!!! ‹‹ምን ቢታለብ በገሌ!

minster
Next Story

የሳኦል በሽታ – አስቻለው ከበደ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop