August 9, 2022
17 mins read

የሳኦል በሽታ – አስቻለው ከበደ

minsterረፈድፈድ ሲል ነው ሰዎቹ ወደ ቤተ መንግስት ይዘውት የደረሱት፡፡ ሰውዬውን የመለመሉት በታላቅ ጥንቃቄ ነበር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ለሶስት ወር ያህል ከማንም ገር ሳይገናኝ በተዘጋጀለት ማረፊያ እንደሚቆይ አግባብተው ነው ያመጡት፡፡

ሰውዬው የሳይኮሎጂ፣ሰፒች ቴራፒና ኮሚኒኬሽን ባለሙያ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የብልጽግና ፓርቲ አርማ እንዲቀየር ለጠ/ሚሩና የቀርብ ሰዎቻቸው ባቀረበው ጽሁፍ ከላይ ያሉ ሰዎች ያውቁታል፡፡ አርማው በውስጡ በጠቁር አምላክ እጅ የሚባረኩ ልጆች፣ የፒኮክ ምስልና ሲገለበጥ ደግሞ የቫይኪነገ ዘውድ የደፋ ከፊቱ ጨረር የሚወጣ ንጉስ መሆኑን አትቶ ነበር የጻፈው፡፡

በኢትዮጵያ ካለው ተጨባጭ የሐይሞኖትና ፖለቲካ ሁኔታ ጋር አርማው እንደማይሄድ ገልጾ የግዜ ጉዳይ እንጂ ብልጽግና በዚህ አርማ ምክንያት ውግዝ ከመ አርዮስ እነደሚባልም ተንብዩል፡፡ በተለይም አርማውን ገልብጠው ሲያዩት ዘውድ የደፋና ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚያንጸባርቅ የዶ/ር አብይን ክባዊ የፊት ምሰል የያዘ መሆኑ ብልጽግናን ከፓርቲነት ወደ አምልኮ ከልትነት እነደሚሳንሰው በግልጽ ነበር ያብራራው፡፡

የጽሑፉ ሁኔታ ገንቢ ሂስን የተከተለ መሆኑ ቤተመንግስት ያሉ ሰዎች በጠላትነት እንዳያዩት አድርጎታል፡፡ እንደያውም ጠ/ሚ አብይ አግኘተውት ግዜ ወስደው አንዳናገሩት ይነገራል፡፡ ከዚያ ቧኃላ ደጋግመው አግኝተውት ህዝብና መንግስት፣ ብሔርና ሰውን የሚገናኘውን ንቃተ ህሊና ከድንበር ተሸጋሪ ብሔሮች ኢሪዴንትዚም ፖለቲካ አንጻር ለሳምንታት የቆየ ገለጻ አድርጎላቸዋል የሚባል ነገርም አለ፡፡

ጠ/ሚ ለአንድ ወር ያህል በጠፉበት ግዜ ነበር ይህን ሰው በእግር በፈረስ ተፈልጎ የሃገር አድን ተልኮ የተሰጠው፡፡ ለዚህ ተልኮ ያሰማራው ሰው እራሱን ´ያየህ´ ብሎ ነው ያስተዋወቀው፡፡ ደጋግሞ አግኝቶታል፡፡ ጠ/ሚ ችግር እንዳጋጠማቸው ነግሮት ለአንተ ባለቸው መልካም አመለካከት እንድትረዳን እንፈልጋለን አለው፡፡

ከብዙ ውይይት ቧኃላ ተሰማሙ፡፡ ከዚያም ያየህ እሰውዬው ጆሮ ውስጥ ምስር የምታክል ትንሽ ነገር በስምምነት ጨመረ፡፡ እሏም እንደ ኩክ ሆና ተለጠፈች፡፡ እንግዲህ ለሶስት ወር ያህል ግዜ ሰውዬው የሚሰማውና የሚናገረው ሁሉ ያየህ ደባል ሆኖ ያዳምጣል ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ሲያስብ በቋንቋ ስለሆነ የሰውዬውንም ሃሳብ ሳይቀር ይህች ትንሽ  መሳሪያ ለያየህ ተስተላልፋለች፡፡ እንዲህ ያለውን ኤሊያን ቴክኖሎጂ ተጭኖ ነበር ሰውዬው ቤተመንግስት የደረሰው፡፡

ሰባተኛው ቀን

የጠ/ሚ የቅርብ ሰዎች ተረብሸዋል፡፡ ጠ/ሚሩ አጠገባቸው ካሉ ሰዎች ጋር መግባባት አቅቷቸዋል፡፡ አስር ደቂቃ ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከአንድ እርእስ ወደሌላ እየዘለሉ ስለ ስድስትወይንም ሰባት ነገሮች ያወራሉ፡፡ ገፋ ገፋ የገርጋቸዋል፡፡አጠገባቸው ያሉትን ሁሉ ይጠረጥራሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያሸማቅቃሉ፡፡ ያን መንፈሳዊ አማካሪያቸው እንኳን በጥያቄ በደንብ ነው ያሸማቀቁት፡፡

“ሴይጣን የት እንደሚኖር ታውቃለህ?” አሉት፡፡ ተረጋግተው እንዲመልሱለት በመጠየቅ አለማወቁን ነገራቸው፡፡ “መነኩሴ ቆብ ስር ነው፡፡ ወይም የቄስ፣ የፓሰተር የውስጥ ኪስ ውስጥ፡፡” ብለውት አረፉ፡፡ ይሄኔ ይህ ወዳጃቸው ወቼ ጉድ ነገሩ ብሶል ሲል አሰበ፡፡ ይህ መነኮሳቱ እርስ በእርስ ሲጣሉ የሚባባሉት ነገር ነው፡፡ ከጠ/ሚሩ አፍ ወጣ ተብሎ ቢነገር ግን ሰባ ሚሊዮን የሚሆነው ኦርቶዶክሳዊ ይነሳባቸዋል አለ ለእራሱ፡፡

ጠ/ሚ ለሶስት ቀናት እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይናቸው ሳይዞር ከሃሳብ ወደ ሃሳብ ሲዘሉ፣ ስለ ብዙ ነገሮች በክፍላቸው ውስጥ ሆነው ከወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ ሲወሩና አቅጣጫ ሲሰቀምጡ የሰሟቸው የቅርብ ሰዎቻቸው በየግላቸው ቀርበው ጠ/ሚ ሊያረጋጉ ከሞከሩ ቧኃላ አልሆን ሲላቸው ነው ሰውየውን ወደ ቤተ መንግስት ለመጋበዝ የወሰኑት፡፡

ጠ/ሚ ገለል ተደርገው በተቀመጡበት አንድ ትልቅ የቤተመንግስት ክፍል ውስጥ የደረሰው ሰውዬ የበገና ድርድር ሲያዳምጡ ነው ያገኛቸው፡፡ ነጭበነጭ የለብሰች የለበሰችው ነጠላ ቀይ፣ ነጭና ጥቁር ጥለት የለው አንዲት ሴት በገና ትደረድራለች፡፡

“እኔ መዩ፣ ግብጽ ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ…” ትዘምራለች የጠ/ሚሩ ልብ ትንሽ አረፍ ብሏል፡፡ ከዚያም  ግን ድንገት ተነሱና የጥለሁን ገሰሰን “ሰላም መካ ያገኔ፣ ሰላም መካ ሃርካፉኔ…” እያሉ ዘፈኑ፡፡ ድንገት ጠ/ሚሩ በጉልበታቸው ተንበርክከው “አምላኬ አምላኬ ሆይ አሁንም በታላቅ ምስጋና ስምህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፡፡በዚያ በባድሜ ጦርነት ላይ ያሁሉ በዙሪያዬ የነበረ ሰው ሲያልቅ እኔን አትርፈክኛልና፡፡” አሉ፡፡ በሃሳባቸው ንጉስ ሳኦል ዳዊትን ሊገድል ጦር ሲወረውር ታያቸውና “ምድረ ሰኦል ሁሉ ያንተ ጦር እኔን አያገኘንም፡፡” ብለው ጮሁ፡፡ ሃሳባቸው ተገላብጦ እሳቸው ቀስት እየወረወሩ አጠገባቸው ያሉትን ሁሉ ሲነድፉ ይታያቸው ጀመር፡፡ በወታደርነትና በሰላይነት ዘመናቸው የሰሩትን ብዙ ጀብዶች ለሰውዬው አወጉት፡፡

ድንገት ተነስተው ወደ ቁምሳጥኑ በመሄድ ከረባትና ቆንጆ ሙሉ ልብስ ቀይረው ይናገሩ ጀመር፡፡ “በአስራ አምስት ቀን ጦርነት መቀሌ መግባት ችያለሁ፡፡ ወያኔ አስራ አምስት አመት የፈጀበትን የደደቢት ጉዞ ወደ ቀናት መቀየር ችዬ ነበር፡፡ ጀነራል አሳምነው ጽጌን በሁለት ሰአት ከምናምን ደቂቃ በሆነ ውጊያ ሙሉ ኦፕሬሽኑን ፀጥ ረጭ አድርጌለሁ፡፡ ኢንሻ አላህ የሰሜኑን ማጅራት ገትር በሁለት ሶስት ሳምነት ወይም አመታት ልክ አስገባዋለሁ፡፡”

ድንገት ጮሁ “እኔ የለሊት ወፍ አይደለሁም፡፡ እዩት ጥርሏን ስትባል ይኸው ክንፌን እንዳለቸው ክንፏን ሲላት ደግሞ እዩት ጥርሴን እንዳለቸው፡፡ አልፋና ኦሜጋ በእኔ ውስጥ አለ፣ እኔም ደግሞ በእሱ ውስጥ…”

ሰውዬው ይህን ግዜ በለሆሳስ ተናገረ፣ ከመዝሙረ ዳዊት 71 ላይ ጠቅሶ አነበነበ በፊቱም ኢትዬጰያ ይሰግዳሉ፡፡ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ፡፡…የዓረብና የሳባ ነገስታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ…

ጠ/ሚሩ ወደ ሰውዬው መጥተው ሰላም ወንድሜ መቼ መጣህ ብለው ግንባሩን ሳሙት፡፡ እሱም ከልቡ አቀፋቸው፡፡ ጥሎባቸው ይህን ሰው ይወዱታል፡፡ ትልልቅ አይኑንና ክብ ፊቱን እያዩ አንተ እኮ አንድ ወንድሜን ትመስለኛለህ አሉት ፡፡

“እንዴት እኔ መርቼው የተጠናቀቀ ጦርነት ወያኔን ወደ መቀሌ ከተመለሰ ቧኃላ አይረባም እባላለሁ? ያሁሉ የህዝብ ድጋፍ የት አለ?” ዞር ብለው ግድግዳው ላይ የተሰቀለውን የባለቤታቸውን ፎቶ እየተመለከቱ “እኔን ሌባ ሌባ ማለት አሁን ፋሽን ሆኗል፡፡”ሰውዬው በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ “ለነበር ለነበርማ ሴይጣንም መልአክ ነበር፡፡”

”ተመልከት አዱ ገነትን አስዋብናት፡፡ ፓርክ በፓርክ አደረግናት፡፡ ገና ችግኝ እንተክላለን፡፡በሐይማኖትም ቢሆን ኦረቶዶክሱን አስታራቅን፡፡ ለፐሮትሰታንቱም አቅጣጫ ሰጠን፡፡ ገና ብዙ ሃሳብ አለን፡፡ በወለጋ በሌላ ቦታ ለሚሞቱ ሰዎችም ጥላ ይሆን ዘንድ ሚሊዮን የሚቆጠር ዛፍ ተከልን፡፡“ ሰውዬውም “ሰባ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ደረግ በኮሚኒዝም ስም የቀማኝን አደባብይ አንተ በራስህ ፈረስ ጋለብከው እንደሚልህ አልሰማህም ወይ? ደግሞስ ገና በምተክለው የዛፍ ቁጥር ልክ ሰው እንዲሞትልህ ታስባለህ?” ሲል አሰበ፡፡

አስራዘጠነኛው ቀን

ጠ/ሚ ጅቡንቡን ብለው ለብሰዋል፡፡ ጺማቸውም አድጎል፡፡ እንዲህ ሆነው ሲታዩ  ሀዘን ላይ የከረሙ ነው የሚመስሉት፡፡ ያየህ ሰውዬውን ለሰባተኛ ግዜ ወደ ቤተመንግስት  ሲልከው ጠ/ሚ ከሰው ጋር መነጋገር እንዳሰጠላቸው ላያናግሩት እንደሚችሉ አስጠንቅቆታል፡፡

ሁለቱ ኮመፒዩተሮች ተደራርበው ተቀምጠዋል፡፡ ጠረጴዛው ጥግ ላይ ከግድግዳዎቹ ጋር ገጥሞ ተቀምጦል፡፡ ሰውዬው ወደ ክፍላቸው ሲገባ ጠ/ሚሩ ወደ ግድግዳው ዞረው ተቀመጡ፡፡ እሱም ዙሪውን ካማተረ ቧኃላ አንዲት ትንሽ ወንበር ሰቦ ወደ መሰኮቱ ጋር በመሄድ ተቀመጠ፡፡

ለአንድ ሰዓት ይህል እሳቸውም ግድግዳው ላይ እንዳፈጠጡ እሱም ከመሰኮቱ ማዶ ያለው ግድግዳ ላይ እንዳፈጠጠ በትልቁ ክፍል ውስጥ በጸጥታ ተቀመጡ፡፡  ሰውዬው አንድ ግጥም በሃሳቡ መጣለት፣ ያየህ ይህን ግዜ በለው መልከም ነው ሲል ሹክ አለው፡፡ ይሄኔ የደበበ ሰይፉን ግጥም  ሰውዬው ጮክ ብሎ አሰማ፡፡

ለአንዲት ውብ ሙዚቃ ሀሣቤን ሰውቼ ለአንዲት መልካም ቅኔ ባርነት ገብቼ ህሊናዬን፣ ቀልቤን አካሌን  ሰጥቼ…ጠ/ሚ በፍጥነት ወንበራቸው ላይ ተሸከርክረው ወደ ሰውየው ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ሰውዬው ፊቱን ሳያዞር ማዶ ማዶ ግድግዳውን እያየ ግማሽ ፊቱን እንደሰጣቸው በዚያው አቀማመጥ ቆየ፡፡ለአስር ደቂቃ ያህል ሰውዬውን እያዩ ከቆዘሙ ቧኃላ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡

“ለምን? ለምን? አምላኬ ሆይ ለምን አሳሳትከኝ? ለምንስ እናቴን?” ብለው ጮሁ፡፡ እዚህ ግድግዳው ላይ እነደፊልም ሆኖ ይታየኘ ነበር፡፡ እኔና አነተ በአንድ መኪና ተሳፍረን እኔ እያሸከረከረኩት ስንሄድ ነበር፡፡ እድሌ ሆኖ ጨለማ በሆነ የጦርነት ወረዳ ውስጥ ነበር መኪናውን የምነዳው፡፡ ኋላ ግን አንድ የለጠበቅኩት ድንክ ሰው እንደ ቫምፓየር አንገቴ ላይ ነከሰኝ፡፡ አንተም መኪናዬን ጥለህ ወጣህ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የአባይን ነገር ሳላሳካ አልሄድም!” አሉ፡፡ ይህን ግዜ ሰውዬው ወንበሩን ወደ እሳቸው እያንፋቀቀ ቀርብ ብሎ“ ይሆናል!” አላቸው፡፡ ከዚያም ጠ/ሚሩ ዙሪያ ገባቸውን ካዩ ቧኃላ ቆይ መጣሁ ብለው ወደ ሌላ ክፍል ገቡ፡፡

ከአስር ደቂቃ ቧኃላ ተመልሰው መጥተው ”ወደጄ እንኳን ደህና መጣህ አሁን ወደ ስራችን እንመለሳለን፡፡“ አሉት፡፡ ወጥቶ ሊሄድ ሲል ያዝ አድርገው አይን አይኑን እያዩት ”አየህ ያለግዜው ከተወረወረ ወርቅ ይልቅ በግዜው የተወረወረ ድንጋይ ትርጉም አለው፡፡ እውነቱን ነው መንግስቱ ወርቅ ሲያነጥፉለት ፋንድያ የሚል ህዝብ…“ ንግግራቸውን አልጨረሱትም፣ ሰውዬውን አሰናበቱት፡፡

የሃያ ስምንተኛው ቀን ሪፖርት

ጠ/ሚሩ የመሲሁ ዝብርቅርቆሽ (Meshanic Complex ) ሰለባ ሆነዋል፡፡ የዚህ ኮምፕሌክስ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የሚያሳዩትን ባይፖላር  ዲሶኦርደር በማኒክና ዲፐርሽን ማለትም በምርቃናና ድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው የሚያሳዩትን ባህሪ በእሳቸው ላይ አይቻለሁ፡፡ አሁን ከድብርት ሰሜት ወጥተዋል፡፡

ይኼኔ ያየህ አቋርጦት “ጠ/ሚሩ ወደ ቢሮ መመለስ ይችላሉ?“ ሲል ጠየቀው፡፡ ጆሮው ውስጥ የተለጠፈችውን በኩክ ማውጪያ እያወጣ “እስከነምርቃናቸው” አለ፡፡ ከዚያም በሁለቱም በኩል ፀጥታ ሰፈነ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop