August 8, 2022
14 mins read

የኢትዮጵያ ጂዲፒ ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ብር ተመነደገ!!! (122 ቢሊዮን ዶላር!!!) የመደመር ኢኮኖሚክስ!!! ‹‹ምን ቢታለብ በገሌ!

ኢት-ኢኮኖሚ /ET-ECONOMY
(ክፍል 1) ሚሊዮን ዘአማኑኤልና ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ

ETEC78ድመቷ ጥቁር ወይ ነጭ ሆነች አልሆነች ግድ የለም፣ ዓይጥ እስከያዘች ድረስ! ‹‹It doesn’t matter if a cat is black or white, so long as it catches mice.››Deng Xiaoping Quotes

የኢትዩጵያየማክሮኢኮኖሚአፈፅፀምዳሰሳ

ዶክተር አብይ አህመድ የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አፈፅፀምን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት
• የውጭ ንግድ ኤክስፖርት 4.12 (አራት ነጥብ አስራሁለት) ቢሊዮን ዶላር
• የአገልግሎት ወጭ ንግድ 6.3 (ስድስት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር )
• የውጭ ንግድ ኤክስፖርትና የአገልግሎት ወጭ ንግድ በመደመር ቲዬሪው ተጠቅሞ 10.3 (አስር ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር አደረስው በመቀጠልም ከዲያስፖራዎች ለቤተሰብ የሚላክ ሃዋላ (Remittance) እና ቀጥተኛ የውጭ መዋለ-ንዋይ (Foreign Direct Investment) ሲደመሩ 20 (ሃያ) ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የመደመር ፍልስፍናቸውን ኢኮኖሚክሱን እንደማያውቁ አስመስክረዋል፡፡ የአገልግሎት ወጭ ንግድ 6.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ 4.75 ቢሊዮን ዶላር ያልተጣራ ገቢ ያስገኘ ሲሆን ቀሪው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ኢትዮቴሌ ወዘተ የተገኘ ያልተጣራ ገቢ ነው፡፡ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ንግድ፣የአገልግሎት ወጭ ንግድ፣ ሃዋላና ኤፍዲአይን ገቢዎች በአንድ ላይ በመደመር ለማምታታት የተጠቀሙበት ማጭበርበር ትውልድ ያሳስታል፡፡ዶክተር አብይ ወተቱም፣ እርጎውም፣ ቅቤውም ኬኛ በማለት ‹‹ድመቷ ጥቁር ወይ ነጭ ሆነች አልሆነች ግድ የለም፣ ዓይጥ እስከያዘች ድረስ!››ብለውናል፡፡

{1} የኢትዮጵያ ብሄራዊአማካይ ጠቅላላ አመታዊምርት(GDP)

በ1991እኤአ (1983ዓ/ም) ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) 10,535 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በግዜው (አንድ ዶላር በ2.07 ብር እኩሌታ ይመነዘር ነበር) በ2015 እኤአ (2008 አ/ም) ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት 1,300,000,000 (አንድ ትሪሊየን ሦስት መቶ ቢሊዮን) ብር ሲሆን (አንድ ዶላር በ21.83 ብር እኩሌታ ይመነዘር ነበር) የሃገሪቱ ጂዲፒ እድገቱ በ123 እጅ ማለትም አስራ ሁለት ዕጥፍ እንዲደርስ አንዳደረገው ይስተዋላል፡፡ (አንድ ዶላር በ2.07 ብር እኩሌታ ወደ 21.83 ማደግ በ9.5 በመቶ አምስት እጥፍ በላይ የውጪ ምንዛሪው በማደጉ የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ስሌት እንዲጨምር አደረገው፡፡)

የብር መንዛሪ መርከስ ሁኔታ ማለትም በዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ የኢትዩጵያ ብር የመሸጥና የመግዛት አቅም እንደተሸመደመደ ያሳያል፡፡ አገሪቱ በውጪ ንግድ የምትልካቸው ምርቶች ዋጋ መቀነስን አስመዝግቦል፡፡ እንዲሁም አገሪቱ በገቢ ንግድ የምታስገባቸው ካፒታል ጉድስ እቃዎች ዋጋ በመጨመሩ የዶላር የመግዛት አቅም በ9.5 በመቶ ማለትም አምስት እጥፍ በላይ በመጨመሩ ሃገሪቱ በገቢ ንግድ ተጎጂ ሆናለች ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) ከቢሊዩን ብር ወደ ትሪሊዩን ብር እምርታ ማሳየቱ የኢኮኖሚ እድገትን አያመላክትም፣ የብር መርከስንና የመግዛት አቅም መቀነስን ነው የሚያሳየው፡፡

በ2022እኤአ ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) 112,000,000,000 (መቶ አስራ ሁለት) ቢሊዩን ዶለር ሲሆን በኢትዮጵያ ብር 6,222,000,000,000 (ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ) ብር መድረሱ የኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ በመርከሱ የተነሳ የመጣ የቁጥር ግዝፈት (አንድ ዶላር በሃምሳ አንድ ብር) በመመንዘሩ የተገኘ ስሌት ሲሆን ‹‹ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ!!!›› ተብሎለታል፡፡

Ethiopia GDP The Gross Domestic Product (GDP) in Ethiopia was worth111.27 billion US dollarsin 2021, according to official data from the World Bank. The GDP value of Ethiopia represents 0.01 percent of the world economy. source: World Bank

GDP in Ethiopia is expected to reach112.00 USD Billionby the end of 2022, according to Trading Economics global macro models and analysts expectations. In the long-term, the Ethiopia GDP is projected to trend around 115.00 USD Billion in 2023, according to our econometric models.

የውጭ ምንዛሪ ተመን የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከአመት ወደ አመት እየረከሰ መሄድ ማለትም፣ የአንድ ዶላር የብር ተመን በ1991 እኤአ 2.05 ብር የነበረ ሲሆን፣ ከ1992 እስከ 1994 እኤአ ወደ 5 ብር፣ ከ1995 እስከ 1999 እኤአ 5.88 ብር፣ ከ2000 እስከ 2004 እኤአ 8.15ብር፣ ከ2005 እስከ 2008 እኤአ 8.65 እስከ 9.67 ብር አንድ አሃዝ እየረከሰ ሄድ፡፡ ከ2009 እስከ 2015 እኤአ የአንድ ዶላር የብር ተመን ወደ ሁለት አሃዝ እየረከሰ ከ12.39 ብር ወደ 21.83 ብር፣ ከ2016 እስከ 2022 እኤአ የአንድ ዶላር የብር ተመን ወደ ሁለት አሃዝ እየረከሰ ከ22.39 ብር ወደ 51.00 ብር የብራችን የመርከስና የብር የመግዛት አቅም መውደቅ ዋና ምክንት የተደላደለና የረጋ የውጭ ምንዛሪ ተመን አለመኖሩን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል፡፡ በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር ከ82 እስከ 84 ብር ይመነዘራል፡፡

የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) እድገት መገለጫዎች በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች፣በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መረጋገጥ አለበት፡፡የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በግብርና ዘርፍ ላይ ጥገኛ ነው፡፡ ግብርና ዘርፍ አማካይ የሃገር ውስጥ ምርት (GDP) 40 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ግብርና 80 በመቶ ወደ ውጭ የሚላክ ምርቶች ገቢ በማስገኘት የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል፡፡ ግብርና ዘርፍ 75 በመቶ የሰው ኃይል ይሸፍናል፡፡

የኢትዮጵያየማክሮኢኮኖሚአፈፅፀምሁሉን የኢኮኖሚ ዘርፍ የመደመር ቅዥት

{1} የግብርናውዘርፍምርቶች የእህል፣የሰብል፣ካሽ ክሮፕስ፣ብና፣ሰሊጥ፣የቅባት እህሎች፣ አትክልታና ጥራጥሬ፣ የአበባ ምርት የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡ የአንድ ዶለር በ51 ብር እየረከሰ በመሄዱ የግብርና ምርት በተለይ ቡና፣ በርካሽ ተቸብችቦል፣ ቡና አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊሸጥ ችሎል፡፡

{2} የኢንዱስትሪው ዘርፍምርትና ሸቀጦች የማዕድን ምርቶች፣(ወርቅ፣ ታንታለም፣ ብረት፣) የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች (ልብስና አልባሳቶች)፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የስካር፣ የዘይት፣ የዱቄት፣ የወተት፣ የሲሚንቶ ምርቶች፣ አምራች ፋብሪካዎችን ምርቶች ያካትታል፡፡ በ2013 እና 2014ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ 404 (አራት መቶ አራት) ፋብሪካዎች ተዘግተዋል፡፡ ዋና ምክንያቱም በውጭ ምንዛሪ እጦት የተነሳ የፋብሪካዎቹ ግብአት አለማግኘት፣ የስፔር ፓርት (መለዋወጭ) እጦት፣ ወዘተ ናቸው፡፡ የብሔራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽም አላለ፡፡ ማዕድን ሚኒስቴር ተከለ ዑማ የ900 (ዘጠኝ መቶ) ማዕድን ላኪዎችን በመሠረዝ ማዕድን ሚኒስቴር ተዘግቶል ማለት ይቻላል፡፡ የአጉዋ ጉዳይ ተከድኖ ይብሰል፡፡ አዲዬስ ኢኮኖሚ!!! …..አልታይህ አለኝ ያገሬ ሠማይ፣

{3} የአገልግሎት ዘርፍየአየር፣የየብስና ባህር ትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ የቱሪዝምና ሆቴሎች፣ የቴሌኮም፣ የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎቶች ሽያጭ በየአመቱ በምን ያህል አደገ? ምን ያህል የውጭ መንዛሪ አስገኙ?

  • 1‹‹ኤክስፖርት ኦፍ ስርቪስ›› የአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን በውስጡ የሚካተቱት (1ኛ) ቱሪዝም (2ኛ) የኢትዩጵያ አየር መንገድ (3ኛ) የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ (4ኛ) የኢትዩጵያ ቴሌኮም (5ኛ) የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ወዘተ የአገልግሎትዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡
  • 2 የቱሪዝምና ሆቴሎች፣ አገልግሎቶች ይካተታሉ
    3.3 ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ቀጥተኛ የውጭ መዋለ-ንዋይ ፍሰት የሃገሪቱን መሠረተ ልማቶች እድገት በማሳለጥ፣ ምርታማነትን በመጨመር፣ እና የሰው ኃይል ልማትን በማሳደግ አዲስ ሥራ በመፍጠር ኢኮኖሚውን ያሳድጋል፡፡ በተጨማሪም አዲስ ቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግርና ክህሎት በማዘመን የውጭ ምንዛሪ ኃብት ያስገኛል፡፡‹‹Foreign direct investment (FDI) is critical to a country’s economic development. The entry of foreign cash has allowed Ethiopia toimprove its infrastructure, increase productivity, and increase employment. FDI also serves as a vehicle for acquiring sophisticated technology and mobilizing foreign exchange reserves.Jun 18, 2022››
  • 4 ብድር
  • 5 ዕርዳታ በሰለጠኑትዓለም ያሉ ሌሎች የአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ (1ኛ) ሴክስ ቱሪዝም (2ኛ) የህክምና አገልግሎት (3ኛ) የትምህርት አገልግሎት (4ኛ) የፊልም ኢንዱስትሪ (5ኛ) የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ምርት ሽያጭ (6ኛ) ጌምና ልዩ ልዩ ሶፍት ዌሮች ምርቶች ሽያጭ (7ኛ) የመጽኃፍትና የኤሌክትሮኒክስ መፅሃፍት ሽያጭ (8ኛ) የኢንተርኔት ኢኮኖሚ አገልግሎት (9ኛ) የጠፈር ቱሪዝም (ለአንድ ሰው በመንኮራኩር ወደ ጠፈር ጉብኝት ለማድረግ 20 ሚሊዩን ዶላር በማስከፈል አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ምንጭ

(1) Ethiopia Imports, percent of GDP – data, chart | TheGlobalEconomy.com

(2) Ethiopia External debt – data, chart | TheGlobalEconomy.com

(3) Ethiopia Remittances – data, chart | TheGlobalEconomy.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop