ህች ናት ኢትዮጵያ

የተፈጥሮ ህግ  እና ታሪክ ከምንም በላይ ናቸዉ  

የኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ዳር ድንበር አስቀድሞ ከሶስት ሽ ዘመናት በሚቆጠር ጊዜ ጀግኖች እና የምንጊዜም  የኢትዮጵ መስራቾች እና የትዉልድ ባለዉለታወች የሰሞንኛ ሳይሆኑ ዕድሜ ልክ ምስጉን ባለ ደማቅ ታሪክ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን አይረሴ ዋኖች ናቸዉ ፡፡

ይህችን ኢትዮጵያ በደም እና በአጥንት መስርተዉ ህይወታቸዉን ገብረዉ አስከ ዘመነ የኢትዮጵያ ዉድቀት  ዋዜማ ግንቦት 19 ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ጠብቀዉ አቆይተዋታል፡፡

እንግዲህ ኢትዮጵያ የሁላች መጠጊያ አገር ባህር ባሯን ፣ ጥንታዊ ከብሯን እና ገናናነቷን እንድታጣ ጠላት የዉርደት ማቅ ያለበሳት በዘመነ የጥፋት እና ጥልመት ልደት ግንቦት ፳ ቀን በዚህ ዓመት ነበር ፡፡

ከዚህ በመነሳት ህዝብን ጠላት እና ወዳጂ ብሎ በመፈረጂ ኢትዮጵያን ለማክሰም ኢትዮጵያዉያንን እና ዓማራን በማንነት ፣ በዕምነትእና ኃይማኖት፣ በምጣኔ ሀብት ፣ በፖለቲካ ዉክልና ፣ በአገር ባለቤትነት ፣ በፍትኃዊ ተጠቃሚነት….. ማግለል እና መበደል በይፋ የተጀመረዉ ፡፡

በዚህም በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖሩ ዓማራ -ኢትዮጵያዉያን በጠላትነት እና በባዕድነት ባይተዋር እንዲሆኑ እና እንዲሳደዱ ሲደረግ በመኃል እና የዓማራ ክልል በሚባሉ አካባቢዎች የኢትዮጵያን የቆየ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ገፅታ ለማደብዘዝ እና ለመሰረዝ ሲባል ያለምን ዕዉነት እና ፍትኃዊነት መተከል ከጎጃም ፣ ወልቃይት እና አካባቢዉ ከጎንደር ፣ ራያ ከወሎ በማን አለብኝነት ተወስዶ ተልጥፏል፡፡

ከዚኅም በላይ ለዘመናት በአብሮነት በኢትዮጵያዊነት መተሳሰብ ይኖር የነበርን ህዝብ ሆድ እና ጀርባ በማድረግ በኢትዮጵያ  በዓይነቱ ብቸኛ የልዩ ዞን በቋንቋ በዓማራ ክልል ሲቋቋም በሌሎች ኢትዮጵያ ክልል የሚኖር ዓማራ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የግዛት አስተዳደር ዕድል እንዲሰጠዉ አልሆነም ፤ አይፈለግም ፡፡

ዛሬ የአቦን ቅጠል የበላች ፍየል…… እንዲሉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ዓማራን ወይም ኢትዮጵያዊነትን መንቀል የሚለዉ የፀረ ኢትዮጵያዉያን  ሩጫ ጠፈጥሯዊ መልካ ምድሩን መለወጥ እና ተሸክሞ መሄድ ቢሳናቸዉ  በራሳቸዉ ምኞት የፈጠሩትን የክህደት አገር ምስረታ ካርታ  አስቀድመን በጉልበት እንደወሰድን ዛሬም በጉልበት ካልወድን እያሉ ጦር አምጣ ብለዉ መድር ይደበድባሉ ፡፡

የወልቃይትም ፣የራያም ሆነ የመተከል ግዛት የኢትዮጵያ ሉዑላዊ የግዛት አካል የነበሩት እና የሆኑት የጎንደር ፣ወሎ እና ጎጃም መሆናቸዉን ትናንት በፈጠሩት የተስፋ ካርታ እና ህገ መንግስት ማሰባቸዉ በራሱ ሀሳባቸዉ ኢትዮጵያን የማጥፋት እና የራስ አዲስ ግዛት የማስፋፋት ቅዠት መሆኑ ሆድ ያባዉን ብቅል  እንዲሉ  አንዴ ቅድመ ሁኔታ ሌላ ጊዜ ህገ- ኢሃዴግ ማለታቸዉ ለማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም ፡፡

ኢህዴግ የተፈጠረዉ በኢትዮጵያ ምድር እንጂ ኢህዴግ ኢትዮጵያም ሆኑ ህዝቧ በኢህአዴግ አልተፈጠሩም ፡፡ ይህ ዓይነቱ የበዛ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ሠይታናዊ ብልጠት ለዓማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ኢትዮጵያ ክፉ ምኞት ከመሆኑ አልፎ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም ላይ ያላትን ቦታ በትልቁ የሚጎዳ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ግዛቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ ባለቤት እና ንብረት እንጂ ለአንድ አካባቢ ፣ክልል ፣ ስርዓት እና የፖለቲካ ቡድን ጥቅም በስጦታ የሚበረከቱ ገፀ በረከት አይሆኑም ፡፡

አሁንም በድጋሚ የተፈጥሮ ህግ እና ታሪክ ከጥንት እንደነበሩ ለዝንት ዓለም ይኖራሉ እንጂ ዘመን በመጣ ስርዓት በተቀየረ ቁጥር የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት እና የግዛት አንድነት ከሰማይ በታች በማንኛዉም መንገድ ሊቀየር ሊሻር አይገባዉም ፡፡

ታሪካዊ ፣ጥንታዊ እና የዛሬዎች ጠላቶች ኢትዮጵያን ትናንት አናቷን፣ የባህር በሯን እናዳታጣ ዜጎች በአገራቸዉ ባይተዋር እና ተሳዳጂ እንዳይሆኑ ፣ የአገሪቷን ሉዓላዊነት እና ገናናነት ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ እና ህዝባዊ ብሄራዊ ሠራዊት በወቅቱ በታላቁ መሪ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በሳል እና ቆራጥ  አመራር ከፍተኛ መስዋዕት ተከፍሎበታል ፡፡

ሆኖም በጊዜ እና በታሪክ አጋጣሚ በጠላት የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ መብት የሚያሳጣ የሴራ ገመድ ተሸረበ ፤ ጉድጓድ ተቆፈረ  በዚህም የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ተክዷል፤ የባህር በር እንድታጣ በኢትዮጵያ ጠል ስብስቦች በወረቅ ሳህን ከኤርትራ መለየት ጋር በምርቃት ተበርክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ጠላቶች ጠላት እና ወዳጂ ሆኖ ተፈረጇል፡፡ የኢጥዮጵያ ብሄራዊ ጦር ተበትኖ በትህነግ ጦር ተተክቷል፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳከም በማንነት ፣ በባህል እና ኃይማኖት ከፍተኛ ዘመቻ ተካሂዷል፡፡ ይህም ከሩብ ክፍለ ዘመን ዓመታት  የዉርደት ፣የድህነት እና የሞት ህማም ተመላልሶበታል ፡፡

ይህ እና ከዚህ በላይ የሚቀር የኢትዮጵያ የየብስ በር የነበሩትን መተከል እና ወልቃይት ጠገዴን ከኢትዮጵያ ዕቅፍ ማዉጣት ሌላዉ ኢትዮጵያን ማክሰም የክፋት ጥንስስ ስለነበር በማን አለብኝነት በክልል ስም ተለይተዉ ቆይተዋል ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን የባህር በር ዘግቶ ፤ በየብስ (በምድር) እግረኛ መዉጫ ኣሳጥቶ ኢትዮጵያዉያን ዓማራ ቁም ቅምጥ መንሳት የሚያስችል ጉድጓድ መቆፈር መቆም አለበት፡፡ ለእስካሁኑ ለደረሰዉም የሴረኞች ወጥመድ መበጠስ አለበት ፤ ጉድጓዱም  ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ጉድጓድ ለሚቀፍሩት ፤ ቅጠል ለሚቆርጡት  መቀበሪያ መሆን እና ለክህደታቸዉ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያዉያንን እያታለሉ እና እየገደሉ ፤ኢትዮጵያን እንደ ቁራጭ ጨርቅ እየሸነሸኑ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እንደ ዳቦ መቁረስ ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያዉያን ዓማራ በምንም መንገድ እና ሁኔታ በየትኛዉም ምክነያት ለበገር እና ሊደናገር አይገባም፡፡

 

ስንኖር በታሪክ የምናዉቃት ፤ ዓለም የሚያዉቃት ታላቋ እና ጥንታዊ ኢትዮጵያ ይህች ናት፡-

Ethiopia Map

ጎንደር ፣ ጎጃም እና ወሎ …የኢትዮጵያ ግዛቶች መሆናቸዉን የማይካድ ከሆነ  ሁሉም ለፖለቲካ ጥቅም  ወደ መጣበት መጎተት ኢትዮጵያዊነት ስለማይሆን  ሁሉም የተጠቀሱት ግዛቶች ዉስጥ ለዘመናት የነበሩት አሁንም ወደፊትም በዚሁ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ የግዛት አስተዳደሮች ጥላ ስር መኖር አለባቸዉ ፡፡ ከናቷ የዋለች ዕንቁላል አትሰበርም ይባል የለም ፡፡

ኤርትራን አጣን ፣ አሰብን ጣን……..አስከመ መቸ ነዉ የምኛጣዉን አስክናጣ ….እያጣን እና እየተገፋን የምንኖረዉ ፡፡

ኢትዮጵያን እና አገሩን ለሚወድ እና ከላይ በሚባሉ የግዛት አስተዳደሮች የሚገኙ መተከል፣ ወልቃይት፣ራያ…. የኢትዮጵያ የግዛት አካል መሆናቸዉን ግራ ለሚጋባ ከዚህ በታች የሚታየዉን የቀደመ የኢትዮጵያ ምስል (ገፅ ፪) መመልከት በቂ ነዉ ፡፡ ያለፈ ያገደመ የሚያዛበዉን የተዛባ አደናጋሪ ነገር ይዞ መቀጠል ለምንም ለማንም አይበጂም ፡፡

የማይለወጥ ዕዉነት እና የፈጥሮ ህግ ብቻ ነዉ !

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

NEILOSS –Amber!

 

2 Comments

  1. እንተ ራስ ድንጋይ! ሃይሞኖት የሌለው ሰይጣን! የሙሴ ቤተ-ሰቦች ከግብጹ ፈርኦን ለመዳን ቀይ ባህር ሲሻገሩ፡ ብትእዛዝ ኣምላክ ሙሴ በበትር የኤርትራ ቀይ ባህር በበትር ሲመታው ባህሪ ጸጥ ብሎ ወደ መሬት ሲቀየር፡ የእስራኤል ህዝብ ዚድን መጽሃፍ ቁዱስን ዘምጻት 10/-19 ተጠቅሶ ይገኛል። የኢትዮጵያ ባህር ኣላለም። ኣንተ ደደብ የሳጥናኤል ልጅ! ጂል! የኣባይ ግድብ እንዳትሰራ ፈርኦንን ቀይባህርን እንድትመልከት ኣድርግዋል። የኤርትራ ናጽነት ኢትዮጵያ ወደ ኣባይ ግድብ ተመለከተ። ሃቁ ንሱ ነው።

  2. ኣምላክ ለኢትዮጵያ ባህር ኣልሰጣትም። ለኤርትራም ደግሞ እንደ ኣባይ ውሃ ኣልሰጣትም። ባህር የሌሌው ባህርን ከተመኘ፡ እንደ ኣባይ ውሃ የሌሌው የኤርትራ ህዝብ ኣባይ ይመለከተኛል ካለ ምንም ስህተት የለውም!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ethiopia 1626974390
Previous Story

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

Ezema 1 1
Next Story

በኢዜማ እምነት አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ባለበት እስከቀጠለ ድረስ እንኳን ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን መገንባት ይቅርና እንደ ሀገር የመቀጠል ህልውናችንም ቢሆን አደጋ ላይ የወደቀ ነው!!

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ
Go toTop