በሱዳን አሸባሪው ህወሓት ያሰማራቸው ታጣቂዎች እየከዱ ነው

የአሸባሪው ህዋሓት ወቅታዊ አቋምና አካሄድ ግራ ያጋባቸዉና ቡድኑ በሱዳን ያሰማራቸው ታጣቂዎቹ በሚስጥር ያደርጉት የነበረዉን ክህደት በአደባባይ አድርገዉ መክዳታቸውን ቀጥለዋል።
በሱዳን በተለያዩ አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ የህወሓት ታጣቂዎች የሚከዱ አባላት ቁጥራቸው መጨመሩን የገለጹት የኢፕድ ምንጮች፤ በአንድ ቀን በአማካኝ እስከ 200 ታጣቂዎች እየከዱ መሆኑን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ እነዚሁ ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በአንድ ጊዜ ብቻ 180 የሚሆኑ የቡድኑ ታጣቂዎች ከተባሰቡበት አከባቢ በመጥፋት በሱዳን ሀምዳይት ወደሚገኝ የቀይ መሰቀል ካምፕ መግባታቸውን ምንጮች ገልፀዎል።
ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ በኋላ መጨረሻ የሌለውን የህወሃት የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ በመተው ባገኙት አጋጣሚ የእርሻ ስራ፣ የጉልት ስራ፣ ትናንሽ ንግዶች እና ሌሎች ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያስችል ስራ ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን ለመምራት እንቅስቃሴ ጀምረዋል ነው ያሉት የኢፕድ ምንጮች።
(ኢ.ፕ.ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን? - ሸንቁጥ አየለ

2 Comments

  1. ወሬው እውን ከሆነ የትግራይ ልጆች መልካም ነገርን መርጠዋል። ያው በወያኔ ካድሬዎችና ተከፋይ የሱዳን ወታደሮች እንዳይታፈኑና ወደ አልፈለጉት ጦርነት እንዳይላኩ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። በሌላ መልኩ ወደ ትግራይ ተጉዞ የነበረው የነጭ ስብስብ የወያኔን ባህሪ የተረዳ አይመስልም። ወያኔ በጭራሽ ለሰላም ሥፍራ የለውም። ጌታቸው ረዳ በየስፍራው የሚለፈልፈውን ብቻ አስተርጉሞ በመስማት ጉዳዪን መረዳት ይቻል ነበር። ግን የነጮቹ ጋጋታ የራሳቸውም ጉዳይ ስላለበት እንጂ ለትግራይ ህዝብ ወይም ለኢትዪጵያ ሰላም አስበው እንዳልሆነ በተደጋጋሚ በተመድ በኩል የጠሩት ስብሰባ ያሳያል። እኔ የሚገርመኝ ልክ እንደ ተገነጠለ ሃገር እንዲህ ያለ የአስታራቂ ቡድን በአንድ ክፍለ ሃገር አማጽያን ልምምጥ ሲደረግ በታሪክ የመጀመሪያው ነው። ሸዋ ድረስ ዘልቆ ተመትቶ መቀሌ የተመለሰው ወያኔ አፉ እንጂ ጉልበቱ በልዪ ልዪ ምክንያቶች ተመናምኖ የራሱን መኖርና አለመኖር ጥያቄ አስገብቶታል። እንዋጋለን፤ መጣንባችሁ፤ ወዪላችሁ የሚሉት የማስፈራሪያ ቃላቶች ሁሉ ተግባራዊ አይሆኑም። ዛሬ ሰው የክፋታቸውን ልክ ተረድቶ ሴቱ ወንድ ሳይቀር ሆ ብሎ በመነሳት ሰልጥኖ ተዘጋጅቷል። ጦርነቱ ቢጀመር መገዳደል እንጂ እዚህም እዚያም ከበሮ የሚያስደልቅ ድል አይገኝም።
    የዶ/ር አብይ መንግስት የተለጠጠ የሰላም በር ለወያኔ መክፈቱ ለወያኔ የጊዜ መግዣና አልፎ ተርፎም ኡኡታ ማሰሚያ መድረክ ይሰጠዋል እንጂ ወያኔ በጭራሽ ወደ ሰላም አይመጣም፡፡ ይህ ሁሉ ሳይፈጠር ወደ መቀሌ የተጓዙት እናቶችና በጊዜው የሰላም ሚኒስቴር የነበሩትን እንባ የረገጠ ጭፍንና ጨካኝ ድርጅት ነው። ስለዚህ አሁንም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ያቀረበውን የቀድሞውን የናይጀሪያ መሪ እምቢኝ ብሎ ኬኒያታን የመረጠው ለግዜ መግዣ እንጂ ምንም አይነት የሰላም ፍላጎት ወያኔ የለውም። በትግራይ ስለ ሰላም ያነሱ የትግራይ ተወላጆችን ባንዳ ብሎ መረሸኑ ለዚህ ዋንኛ ምስክር ነው።
    የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ ሳይፈታ ሰላም የለም የሚለው ወያኔ በጉልበት እነዚህን ስፍራዎች ቀምቶ ተወላጆችን ባርነት ውስጥ አስገብቶ እንደቆዬ ተረስቶታል። ሲያምራቸው ይቀራል እንጂ ዳግም ወልቃይትንን ጠለምትና ራያን በወያኔ እጅ አሳልፎ የሚሰጥ ሞኝ ህዝብ አይኖርም። ጀጋኑ እያስባሉ እሳት ውስጥ የሚከቷቸው የትግራይ ልጆችም እነርሱ እየሞቱ እነ ጌታቸውና ደብረጽዪን ሲወፍሩና ከቀን ተቀን የውሸት ቱልቱላ ሲነፉ ማየትና መስማት ስልችቷቸዋል። ባጭሩ በግድ ወያኔ ቢያሰለጥናቸውም መዋጋት አይፈልጉም። ወያኔ እነዚህ ስፍራዎች ካልተመለሱልኝ ሞቼ እገኛለሁ ማለቱ የሱዳንን ጉርብትና ናፍቆ እንጂ ከወያኔ በፊት ሥፍራው ሁሉም የሃገሪቱ ዜጋ ሄዶ ሰርቶ የሚኖርባት ምድር ናት። የወያኔ የክልል አፓርታይድ የፈጠረው እኔ ብቻ ልብላ ነው እዚህ ያደረሰን።
    ባጭሩ የሚሻለው ከጦርነት ይልቅ ሰላም፤ የድሃ ልጆችን ከማስጨረስ ይልቅ ነገሮችን ማርገብና ህዝቡ እንዴት አብሮ በሰላም መኖር እንደሚችል መንገድ መፈለግ ነው። ያ ከሆነ ደግሞ ወያኔ በህግ ሊጠየቅ ነው። የትግራይ ህዝብ ይፋረደዋል። ግን በዚህም በዚያም በህዝብ ስም እያጭበረበሩ ለመኖር የሚያረጉት ዋና የወያኔ ዘዴ በመሆኑ ለሰላም ሥፍራ የላቸውም። የነጭ መንጋ መቀሌ ሄደ ተመለሰ ለኢትዪጵያ ህዝብ ጠቃሚነት የለውም። እነርሱም የራሳቸውን ትርፍ ፍለጋ ነው የሚሮጡትና! ስለሆነም በየቦታው የተበተኑት የትግራይ ልጆች እውነቱን መርምረውና ተረድተው ወያኔን አክ እንትፍ እስካላሉት ድረስ የምድራችን ገመና ይቀጥላል። ይህ በሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ የትግራይ ልጆች የወሰድት እርምጃ ጥሩ ጅማሬ ነው እላለሁ። በቃኝ!

  2. The TPLF has stolen tens of billions dollars from loans and aid money it got while in power. This money will be used to destabilize Ethiopia by financing its own foot soldiers and others. It is not in the long term interest of Sudan to shelter the TPLF forces of destabilization.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share