July 29, 2022
4 mins read

የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪነት መታወቂያ ማግኘት የገነት መግቢያ ቁልፍ እንደመቀበል በሚቆጠርባት አገር ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ለማን ናት ?

adanech abebeኢትዮጵያ የተለያዩ አገራት ዜጎች የዜግነት(ኗሪነት) ወረቀት -መታወቂያ ሰጠች ፣ አደለች ልትሰጥ መረጃ አጠናቀቀች ሲባል መስማት አዲስ ነገር አይደለም ፡፡

ከዚህም በላይ እንግዳ ተቀባይታችን ለወሬ ፍጆታ ስናዉል ባለቤት አቅላይ እና ፈንጋይ መሆናችንን እናለባብሳለን ፡፡ ከዓረብ አገር ስደተኞችን ወደ አገራቸዉ የመመለስ ስራ እና መልሶ ማቋቋም ይባላል ለመሆኑ ለምን እና በምን ተሰደዉ ነዉ ወደ አገር ሲመለሱ ይስተዋላል ፡፡ የዉስጥጡ እያረረ በላይ ጥሬዉን መጨመር ማገዶ እና ዉኃ እንደሚጨርስ ንፍሮ ጥሬ እና ብስል ማድረግ መሆኑን እያወቅን ጭጭ ሆኗል ፡፡

አሁን ደግሞ እንደ አዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪነት መታወቂያ ማግኘት የገነት መግቢያ ቁልፍ እንደመቀበል በሚቆጠርባት አገር ኢትዮጵያ መታወቂያ መስጠት እንደታገደ ከሁለት ዓመታ በላይ መሆኑን የምናዉቅ እና ይህም ለምን እንደሆነ በምክነያት የሚጠይቅ አካል ነበር ወይ ስንል ዛሬ ላይ አዲስ አበባ ግቡ አትግቡ የሚባለዉ በማን እና ለምን እንደሆነ እንዴት ሊገባን ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ምድር በየብሱም ፣በባህሩም ሆነ በሰማይ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ ባለመብት መሆኑ እየታወቀ በዚህ መንገድ ማለፍ ሆነ መጓዝ አይቻልም ብሎ መከልከል ለምን ይገርማል ፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዉያን ያላለ ዛሬ ሁሉን አጥቶ በጥፋት በጎርፍ አስከ አንገት ማሰሪያዉ ሲያዝ ጉድ ማለት ጤነኝነት አይደለም ፡፡

አበዉ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ እንዲሉ….. ህዝብ መቆሚያ፣መቀመጫ በማሳጣት እንግዳ ተቀባይ እያሉ በአኩሪ ኢትዮጵያዊ ባህል እና ትዉፊት የሚያላግጡ ክዶ አደሮች ህዝብ በአገሩ ፍዳዉን ሲያይ ከዚህ በላይ ምን አለማለት የህዝብ እና የአገር ጠላቶች በመንገዶች እና በመታወቂያ ወረቀቶች ላ ብቻ ሳይሆን በሠዉ ልጆች ህይወት ላይ አዛዥ መሆናቸዉ እንደ ድንገት የሆነ አይደለም ፡፡

በኢትዮጵያ የዜጎች የመኖር አለመኖር ተፈጥሯዊ መብት ዕንግዳ ጎርፍ ሲነጥቀዉ እና ኢትዮጵያ ለሞተላት ሳይሆን ለሚገድላት መሆኑን በታሪክ ሳይሆን በዕዉን ለምናይ ኢትዮጵያ የማን ናት ብለን መብት እና ነፃነት በማነብነብ ወይም በስመ መቃወም ሳይሆን በአንድነት እና በህብረት ክንድ አገራችን የእኛ ናት እኛነታችን ከአገራችን ሉዓላዊ ባለቤትነት የማይለያይ ነዉ ብለን ጠላት ዕንግዳ ሰጪ እና ነሽ ሊሆን እንደማይችል በተባበረ ክንድ ማስረዳት እና ማሳየት ያስፈልጋል፡፡

ዕንግዳ ሲያፍር ባለቤቱን ያጎርሳል እንዲባል የዕንግዳ ጠላት ኢትዮጵያ የዕኛ የኢትዮጵያዉያን ናት አስካላልን የተሰራዉን ቀርቶ ተፈጥሮዉን ከመቀማት እና ከማዛባት ወደ ኋላ እንደማይል መገንዘብ ያለብን ጊዜ ቢያልፍም አሁንም በንቃት እና በትጋት ለራስ እና አገር ዘብ መቆም ያስፈልጋል ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

NEILOSS –Amber.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop